settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የኑፋቄ ትርጉም ምንድን ነው?

መልስ፤


ኑፋቄ የሚለውን ቃል ሰዎች ሲሰሙ በአብዛኛው ጊዜ የሚያስቡት ሰይጣንን ለማምለክ የተሰበሰቡትን፤ እንስሳትን የሚሰዉ፤ በክፉ ስራ የሚሳተፉ፤ ግራ የተጋቡ ጣኦት አምላኪዎችን ነው፡፡ ሆነም ግን እውነታው ኑፋቄ እነዚህን ሁሉ ሊያካትት ይችላል፡፡ በትክክል በአለም በስፋት ባለው ትርጉም የራሱ የሆነ የአምልኮ ልምምድ ያለው ኃይማኖታዊ ስርዓት ማለት ነው፡፡

በአብዛኛው ጊዜ ግን ኑፋቄ የሚተረጎመው በጠባቡ ነው እና ቃሉ የሚያመለክተው ከኦርቶዶክስ እምነት ውጪ የሆኑ የመጀመሪያውን ትክክለኛ እምነት ትምህርት የሚያዛቡትን ነው፡፡ በክርስቲያናዊ አውድ የኑፋቄ ትርጉም ‹‹ አንድ ወይንም ከዚያ በላይ የሆኑ መሰረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ትምህርቶችን የሚክድ እምነት ቡድን ነው፡፡›› ኑፋቄ እስተምህሮ ያለው ቡድን ነው፤ ስለማመን ቢሆን ያን ሰው ደኅነትን ሳያገኝ ይተወዋል፡፡ ኑፋቄ የእምነት ቡድን ነኝ ይላል ሆኖም ግን የዛን እምነት አስፈላጊ እውነቶችን ይክዳል፡፡ እንግዲያው ክርስቲያናዊ ኑፋቄ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ የክርስትና መሰረታዊ እውነቶችን ይክዳል ግን ክርስቲያነኝ ብሎ ያውጃል፡፡

በአሁን ጊዙ ሁለት በጣም የታወቁ የኑፋቄ ትምህርት ምስሌ ሊሆኑ የሚችሉት የይህዋ ምስክር እና ሞርሞን ናቸው፡፡ ሁለቱም ክርስቲያን ነን ይላሉ ግን ሁለቱም የኢየሱስ ክርስቶስን መለኮትነት ድኅነት በእምነት እንደሆነ ይክዳሉ፡፡የይህዋ ምስክር እና ሞርሞኖች በዙ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ጋር የሚስማማ ወይም የሚመሳሰል ያምናሉ፡፡ ሆኖም ግን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት ይክዳሉ ድኅነት በስራ እንደሆነ ያምናሉ ይህም ኑፋቄ ተብለው እንዲመደቡ ያደርጋቸዋል፡፡ ብዙ የይህዋ ምስክሮች ሞርሞኖችና የሌሎች ኑፋቄ አስተማሪዎች ሞራል ያላቸውና በትክክል አውነትን ይዘናል ብለው የሚያስቡ ሰዎች ናቸው፡፡ እንደ ክርስቲያን የእኛ ተስፋ እና ጸሎት መሆን ያለበት በዙ በኑፋቄ ውስጥ ያሉ ስህተቱን እንዲመለከቱ እና ወደ እውነት በክርስቶስ ኢየሱስ ወዳለው ደህንንነት እዲመጡ ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የኑፋቄ ትርጉም ምንድን ነው?
© Copyright Got Questions Ministries