settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መፍጠርና የዝገመት ለውጥ ምን ይላል?

መልስ፤


ስለ መፍጠርና እና ስለ ዝግመተ ለውጥ ሳይንሳዊ ክርክር ማቅረብ የዚህ የጥያቄ መልስ አላማ አይደለም ፡፡ ስለ መፍጠርና ስለ ዝግመተ ለውጥ ተቃርኖ ሳይንሳዊ ክርክር የዘፍጥረት መጽሐፍንና ስለ ስነ ፍጥረት ጥናት የሚያደርጉ ተቋማት አበክረን እንጠቁማለን፡፡ የዚህ ጽሁፍ አለማ እንደ እግዚአብሔር ቃል የመፍጠርና የዝግመተ ለውጥ ሃሳብ ክርክር ልምን እንደኖረ ለመግለጸ ነው፡፡ ሮሜ 1፡25 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን።››

በክርክሩ ውስጥ ዋናው ጉዳይ አብዛኛዎቹ በዝግመተ ለውጥ የሚያምኑ ሳይንቲስቶች ራሳቸው በእግዚአብሔር የማያምኑ ወይንም ከህይወት በኋላ ሌላ ህይወት የለም የአምላክንም መኖር አላውቅም ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡ ሌሎች ጥቂቶች ደገሞ አሉ አምላክ አለ ብለው የሚያምኑ ዝግመተ ለውጥ አንደሚል አይነት ሃሳብ የያዙና ሌሎች ዴይስቲክ አመለካከት የያዙ አሉ፡፡ ( እግአብሔር አለ ግን በዓለም ውስጥ ጣልቃ አይገባም የሚሆነው ነገር ሁሉ በራሱ የተፍጥሮውን ስርዓት ተከትሎ የሚሆን ነው፡፡) ሌሎች ጥቂቶች በእውነት እና በታማኝነት መረጃዎችን የሚመለከቱ እና ዝግመተ ለውጥ የበለጠ ከመረጃው ይስማማል ወደሚል ድምዳሜ የደረሱ አሉ፡፡ ይሁን እንጂ ይህ የሚወክለው በጣም አነስተኛ መጠን ያላቸው የዝግመተ ለውጥን የሚያስተጋቡ ሳይነቲስቶች ነው፡፡ አብዘኛዎቹ የዝግመተ ለውጥ ሳይንቲስቶች ህይወት በአጠቃላይ ያለ ምንም ከፍ ያለ ኃይል ጣልቃ ገብነት የሚንቀሳቀስበትን ሃሳብ ይይዛሉ ፡፡ ዝግመተ ለውጥ ትርጓሜው በተፈጥሮ የሚያምን ሳይንስ ማለት ነው፡፡

አምላክ የለሽ ከሃዲ ለሆነ ሰው አለም ህይወት ከየት እንደመጣ ከፈጠረው እግዚአብሔር ውጪ ሌላ አማራጭ ማብራሪያ ያስፈልገዋል፡፡ እንደ ዝግመተ ለውጥ ያለ ሃሳብ የሚያምኑ ከቻርለስ ዳርዊን አስቀድሞ የነበረ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ አሳማኝ የሚመስል ከተፈጥሮ የተመረጠ የዝግመተ ለውጥ ሂደት ሞዴል ጽፎ ያዘጋጀው እርሱ ነው፡፡

ዳርዊን አንድ ወቅት ክርስቲያን ነኝ ይል ነበር ግን በአንዳንድ አሳዛኝ ሁኔታዎች በህይወቱ በመከሰታቸው የክርስትና እምነት እና የእግዚብሔርን ህልውና ካደ፡፡ ዝግመተ ለውጥ የተፈጠረው እግዚአብሔርን በካደ ሰው ነው፡፡ የዳርዊን አላማ የእግዚአብሔር መኖር ህልውና ውሸት መሆኑን ማሳመን አልነበረም አርሱ የዝግመተ ለውጥ የመጨረሻው ውጤት አንዱነው፡፡ ዝግመተ ለውጥ እግዚአብሔርን ህልውና መካድን ያስገኘ ነው፡፡

የዝግመተ ለውጥ ተመራማሪዎች አላማቸው ህይወት ከየት እንደተገኘ አማራጭ ማብራሪያ መስጠት እንደሆነ ማመን አይፈልጉም፤ እና በፈቃዳቸው ለክህደት መሰረት ሆኑ ግን እንደ እግዚአብሔር ቃል የዝግመተ ለውጥ ሃሳብ መኖር ምክንያቱ በትክክል እሱ ነው፡

መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፡-‹‹ ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። ›› (መዝ 14:1; 53:1). መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በፈጠራቸው በእግዚአብሔር ባለማመናቸው ይቅርታን እንደማያገኙ ይናገራል፡፡ ‹‹የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ›› (ሮሜ 1:20). አንደ እግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን ህልውና የሚክድ ማንኛውም ሰው ሞኝ ነው፡፡ ግን ታዲያ ለምንድን ነው ብዙ ሰዎች ክርስቲያኖችም ሳይቀር ዝግመተ ለውጥን መረጃዎችን ሳይንቲስቶች ሲተረጉሙ እንዳላዳሉ የሚቀበሉት? አንደ እግዚአብሔር ቃል ሆሉም ሞኝ ናቸው! ሞኝ መሆን የማሰብ ችሎታ እጥረትን አያመለክትም፡፡ ሳይንቲስቶች በዘመናት ውስጥ ጥሩ የማሰብ ችሎታ ያላቸው ናቸው፡፡ ሞኝነት የሚያሳየው እውቀት በትክክል ተግባራዊ ማድረግ አለመቻልን ነው፡፡ ምሳ 1፡7 እንደሚነግረን፡- ‹‹የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ››

የዝግመተ ለውጥ ተመራማረዎች የመፍጠርን እና ወይም በስርዓት የተደራጀ ንድፍ ላይ ሳይሳዊ ያልሆነ እና ላሳይንሳዊ ምርምር ወጋ የሌለው በማለት ይሳለቃሉ፡፡ አነንድ ነገር ሳይነሳዊ እነዲሆን አንድ ነገር የሚጨበጥ ሊመረመር የሚችል ተፈጥሮአዊ ምክንያት የሚሰጥ መሆን አለበት ብለው ይከራከራሉ፡፡ መፍጠር ትርጓሜው ከሰው አቅምና ባህሪ ውጪ የሆነ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሰው አቅም በላይ የሆነ ነገርም ተጨባጭና ሊመረመር የሚችል አይደለም ብለው ክርክሩን ይቀጥላሉ፡፡ የመፍጠር ስራ እና በስርዓት የተደራጀ ንድፍ ሳይንሳዊ አድርገን መውሰድ አንችልም፡፡ እውነት ነው የዝግመተ ለውጥ እሳቤም ቢሆን ተጨባጭ ሊሆንና ሊመረመር አይችልም፤ ነገር ግን ይህ ለዝግመተ ለውጥ አሳብ አራማጆች ጉዳያቸው የሆነ አይመስልም፡፡ በውጤቱም ሆሉም መረጃዎች ያለ በቂ እውቀት አስቀድመው የተሰሩ የተፈጠሩ ሃሳቦች፤ ቀድመው የተገመቱ ተብለው በማጣሪያ ማጥለያ ሲያልፉ ቀድሞ ተቀባይነት ያገኘው የዝግመተ ለውጥ እሳቤ ያለምንም ተጨማሪ አማራጭ ማብራሪያ ከግምት ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡

ሆኖም ግን የፍጥረት አለም መገኛና የህይወት መገኛን ለመመርመርና ለመመልከት የማይቻል ነው፡፡ ሁለቱም የመፍጠር ስራም ሆነ ዝግመተ ለውጥ ስለ ነገሮች መገኛ (origin) መገኛን በሚመለከት በእምነት ላይ የተመሰረተ ስርዓት ነው ያለቸው፡፡ ሁለቱንም ልንመረምራቸው አንችልም መክንያቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አመታት ወደ ኋላ ሄደን ስለ ነገሮች መገኛ (origin) በፍጥረተ አለም የነበረውን ነገር ማስተዋል አንችልም፡፡

የዝግመተ ለውጥ የመፍጠርን ስራ ተቃውሞታል ከዚህም በመነሳት እነርሱም ዝገመተ ለውጥን የነገሮች መገኛ (origin) መገኛነት ሳይንሳዊ ማብራረያ ለመቃውም ተገደው እንደነበር ማሰብ ይቻላል፡፡ የዝግመተ ለውጥ ቢያንስ ስለ የነገሮች መገኛ (origin) የመፍጠር ስራ ሳይንሳዊ ትርጓሜ ጋር እንደማይስማማ እንዲሁ የዝግመተ ለውጥም አይስማማም፡፡ ዝግመተ ለውጥ ለምናልባቱ ስለ ነገረ መሰረት ሊመረመር የሚችል በቸኛው ማብራሪያ ነው፤ የዝግመተ ለውጥ ነገሮች መገኛ( origin) ‹‹ብቸኛው ሳይንሳዊ›› ብለን ልንወስደው የምንችለው ፅንሰ ሃሳብ ነው፡፡ ይህ ሞኝነት ነው! ዝግመተ ለውጥን የሚያራምዱ ተመራማሪዎች ተክክለኛውን የነገሮች መገኛ ፅንሰ ሃሳብ (origin) እወነታን በተክክል በታማኝነት ፈተሸው ሳይረዱ ከእነሱን ጠባብ ከትክክለኛው አስተሳሰብ የወጣ የሳይንስ ምርምር ትርጓሜ ጋር ስላልገጠመላቸው ብቻ ይቃወማሉ፡፡

የመፍጠር ስራ እውነት ከሆነ እኛ ተጠያቂ የምንሆንለት ፈጣሪ አለ ማለት ነው፡፡ ዝግመተ ለውጥ ክህደትን አምላክ የለሽ መሆንን ያስገኘ ነው፡፡ ዝግመተ ለውጥ በክህደት ለሚኖሩ ህይወት እንዴት ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር ውጪ መኖር እንደቻለ የመነሻ ሃሳብ ይሰጣቸዋል፡፡ ዝግመተ ለውጥ በምድር ላይ ለመኖር የእግዚአብሔርን አስፈላጊነት ይክዳል፡፡ ዝግመተ ለውጥ አምላክ የለሽ ለሆኑ በክህደት ለሚያምኑ የመፍጠረ ጽንሰ ሃሳብ “creation theory” ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር ቃል ምርጫው ግልጽ ነው፡፡ ሆሉን የሚችል እና ሁሉን የሚያውቅ የአምላካችንን የእግዚአብሔር ቃል ወይንም ተቀባይነት የሌለውን የተምታታ የሞኞችን ሳይንስ ማመን እንችላለን፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መፍጠርና የዝገመት ለውጥ ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries