settings icon
share icon
ጥያቄ፤

‹‹ኢየሱስ ኃጢያትን ሊያደርግ ይችላል? ኃጢያትን ሊያደርግ የማይችል ከሆነ፤ እንዴት ነው በድካማችን ሊያዝንልን የሚችለው (ዕብ 4፡15)? ኢየሱስ ኃጢያትን ሊያደርግ ካልቻለ፤ በኃጢያት መፈተኑ መንድን ነው ሊያመለክት የሚችለው?

መልስ፤


ለዚህ አስፈላጊ ለሆነ ጥያቄ ሁለት መልኮች አሉ፡፡ ኢየሱስ ኃጢያት አድርጎ ይሆን የሚል ጥያቄ እንዳልሆነ እንዳልሆነ ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ ሁለቱም መልኮች ኢየሱስ ኃጢያትን እንዳለደረገ እንደ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይስማማሉ (2ቆሮ 5፡21፤ 1ጴጥ 2፡22)፡፡ ጥያቄው ኢየሱስ ሊያደርግ ይችላል አይችልም ነው፡፡ የእንከን አልባነትነትን "imp-eccability" ሃሳብ የያዙ ኢየሱስ ኃጢያትን ሊያደርግ አይችልም ብለው ያምናሉ፡፡ የእነከነ የመኖርን ሃሳብ የያዙ "peccability" ደግሞ ኢየሱስ ሊያደርግ ይችላል ግን አላደረገም ብለው ያምናሉ፡፡ የትኛው ሃሳብ ነው ትክክል; ግልጽ የሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ኢየሱስ እንከን ነውር የለበትም፤ ኢየሱስ ኃጢያት ሊያደርግ አይችልም፡፡ ኃጢያትን ሊያደርግ የሚችል ከሆነ አሁንም ኃጢያትን ሊያደርግ ይችላል ምክንያቱም በምድር ለይ በነበረ ጊዜ የነበረውን አካል ስለያዘ፡፡ እርሱ ወደፊትም ቢሆን ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው፤ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክነት በአንድነት በማይነጣጠል መልኩ አለው፡፡ ኢየሱስ ኃጢያት ሊያደርግ ይችደላል ብሎ ማመን መለኮት ኃጢያት ሊያደርግ ይችላል ብሎ ማለት ነው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ ›› (ቆላ 1፡19)፡፡ ቆላ 2፡9 በተጨማሪ ‹‹በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።››

እንዲሁም ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነው፤ እኛ ይዘነው ከተወለድነው የኃጢያተኛ ማንነት ጋር አብሮ አልተወለደም፡፡ በእርግጠኝነት እኛ በተፈተንበት መንገድ ተፈትኖአል፤ በሰይጣን ፈተና በፊቱ ነበር፤ ነገር ግን ምንም አልመለሰም ምክንያቱም መለኮት ኃጢያትን ሊያደርግ አይችልም፡፡ ከማንነቱ ጋር የሚቃረን ነው (ማቲ 4፡11፤ ዕብ 2፡18፡ 4፡15፤ ያዕ 1፡13)፡፡ ኃጢያት ትርጉሙ ህግን መጣስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ነው ህጉን የሰጠው ህጉ በመነሻነት እግዚአብሔር ሊያደርገው የሚችለውና ሊያደርግ የማይችለው ማለት ነው ስለዚህ ኃጢያት እግዚአብሔር በማንነቱ ሊያደርግ የማችለው ነገር ነው፡፡

በፈተና ውስጥ በራሱ በኃጢያት ውስጥ መሆን ወይም አለመሆን አይደለም፡፡ እናንተ ፍላጎት በሌላችሁ ነገር እንድ ሰው በፈተና ውስጥ እንድትሆኑ ሊያደርጋችሁ ይችላል፤ ለምሳሌ ነፍስ እንድታጠፉ እና በሲባዊ ተግባር እንድትፈተኑ፡፡ በእነዚህ ተግባራት እናንተ ምንም አይነት ፍላጎት የሌላችሁ ሊሆን ይችላል ግነ ትፈተናላችሁ ምክንያቱም አንድ ሰው ከእናንተ ፊት እንዲሆ አደርጎታል፡፡ ቢያንስ መፈተን "tempted" ለሚለው ቃል ሁለት ትርጉሞች አሉ፡

1) የኃጢያተኛ አቋም እንዲኖረን በአንድ ሰው ወይንም በሌላ ነገር ከእኛ ውጪ በሆነ አካል ወይንም በራሳችን የኃጢያት ተፈጥሮ ሲቀርብልን

2) በትክክል በኃጢያት ተግባር እንደተሳተፉ መውሰድ እና አስደሳች ሊሆኑ በሚችሉ እና ከእነዚህ ጋር ተያያዥ በሆኑ ተግባራት ልክ እንደተፈጸሙ ሆነው በአይምሮአችን ውሰጥ ሲቀመጡ፡፡

የመጀመሪያው ተርጉም ኃጢያትን በሃሳብ የማድረግ ትርጉም የለውም፤ ሁለተኛው ግን አለው፡፡ በኃጢያት ተግባር ውሰጥ ስናልፍ እና በውስጡ እዴት ልናልፍ እንደምንችል ስናስብ የኃጢያትን መስመር እናልፋለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያው አይነት የፈተና አይነት ተፈትኖአል ከዛ ውጪ በኃጢያተኛ ባህሪ አልተፈተነም ምክንያቱም ይህ በእርሱ ውስጥ የለም፡፡ ሰይጣን ለኢየሱስ የተወሰኑ ኃጢያቶችን አቅርቦለት ነበር ግን በዛ ኃጢያት ውስጥ ለማለፍ በውስጡ ፍላጎት አልነበረውም፡፡ እንግዲያው እኛ በተፈተንባቸው ተፈትኖአል ግን ያለ ኃጢያት ሆኖአል፡፡

የእነከነ የመኖርን ሃሳብ የያዙ "peccability" ኢየሱስ ኃጢያትን ማድረግ የማይችል ከነበረ በእውነት ፈተናን አይፈተንም ነበር እና ለእኛም በእውነት በኃጢያትን በመቃወም ትግላችን ሊራራልን አይችልም ነበር በለው ያምናሉ፡፡ ማስታወስ አለብን ለመረዳት በዛ ነገር ውስጥ ማለፍ አይኖርበትም፡፡ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ስለሁሉም ያውቃል፡፡ እግዚአብሔር ኃጢያትን የማድረግ ፍላጎት ከሌለው እና ፈጽሞ በእርግጠኝነት ኃጢያትን ካላደረገ እግዚአብሔር ኃጢያት ምን እንደሆነ ያውቃል ይረዳል፡፡ እግዚአብሔር መፈተን ምን ሊመስል እንደሚችል ያውቀዋል ይረዳዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በፈተናችን ሊያዝንልን ይችላል ምክንያቱም ያውቀዋል፤ እኛ ባለብን ነገር ውስጥ ስላለፈበት "experienced" አይደለም፡፡

ኢየሱስ መፈተን ማለት ምን ሊሆን እንደሚችል ያውቀዋል፤ ግን ኃጢያት ማድረግን ምን እንደሚመስል አያውቀውም፡፡ ይሄ እኛ ከመርዳት አይከለክለውም፡፡ እኛ በሰው በሚታወቀው ኃጢያት እንፈተናለን (1ቆሮ 10፡13)፡፡ እንዚህ ኃጢያቶች በአጠቃላይ በሶስት ሊመደቡ ይችላሉ፡ ‹‹እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት›› (1ዮሐ 2፡16)፡፡ የሄዋንን የኃጢያት ፈተና ስንመረምር እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስን እያንዳንዱ ፈተና የሚመነጨው ከእነዚህ ከሶስቱ ክፍሎች ነው፡፡ እኛ ባለንባቸው ፈተናዎች ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶ ተፈትኖአል ግን በሁሉም ቅዱስ ሆኖአል፡፡ በኃጢያት የተበከለው ማንነታችን በአንዳንድ ኃጢያቶች ላይ ፍላጎት ሊኖረው ይችላል፤ ልናደርግም እንችላለን፤ በክርስቶ በኩል ኃጢያትን ማሸነፍ እንችላለን ምክንያቱም እኛ የኃጢያት ባሪያዎች አይደለንም ይልቁንም የእግዚአብሔር ባሪያዎች ነን፡፡ (ሮሜ 6፤ በተለይ ቁ. 16-22)፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

‹‹ኢየሱስ ኃጢያትን ሊያደርግ ይችላል? ኃጢያትን ሊያደርግ የማይችል ከሆነ፤ እንዴት ነው በድካማችን ሊያዝንልን የሚችለው (ዕብ 4፡15)? ኢየሱስ ኃጢያትን ሊያደርግ ካልቻለ፤ በኃጢያት መፈተኑ መንድን ነው ሊያመለክት የሚችለው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries