settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እንዴት ክርስቲያን ሆኜ መለወጥ እችላለሁ?

መልስ፤


በፊሊፒንስ በግሪክ ከተማ የነበረው ሰው ተማሳሳይ ጥያቄ ጳውሎስንና ሲላስን ጠይቆ ነበር፡፡ ስለዚህ ሰው ቢያንስ ሦስት ነገር እናውቃለን፡ የእስር ቤት አለቃ ነበር አምላክ የሌለው ሰው ነበር ፈርቶ ነበር፡፡ ጳውሎስ ባያስቆመው ራሱን ሊያጠፋ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ነበር ይህን ጥያቄ የጠየቀው፡ ‹‹እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?›› ሥራ 16፡30

እርግጠኛ የምንሆንበት ነገር ሰውየው ድኅነት እንደሚያስፈልገው በመረዳቱ ጥያቄን መጠየቁን ነው፤ ስለራሱ ሞት ብቻ ነበር የታየው ስለዚህም እርዳታ እንደሚያስፈልገው ተገነዘበ፡፡ ጳውሎስና ሲላስ መልስ እንዳላቸው ስለተገነዘበ ጥያቄውን ጠየቀ፡፡

መልሱን ወዲያው አገኘ፤ ቀላልም ነበር ‹‹በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን ትድናለህ››ቁ.31 ክፍሉ አንዴት እንዳመነ እና እንደተለወጠ ይነግረናል፡፡ ህይወቱ ስርዓት ያለው ሆኖ ካመነበት ጊዜ ጀምሮ ተለወጠ፡፡

ልብ እንበል የሰውየው ለውጥ የተመሰረተው በእምነቱ ላይ ነው(እመን)፡፡ ኢየሱስን ብቻ ማመን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አመነ (አምላክ) በቃሉ የተጻፈውን የፈጸመ መሲህ (‹‹መሲህ››)፡፡ እምነቱ በተጨማሪ ኢየሱስ ስለ ኃጢያቱ እንደሞተ እና እንደገና አንደተነሳ ነበር ምክንያቱም ጳውሎስና ሲላስ እየሰበኩ ነበር (ተመልከቱ ሮሜ 10:9-10 and 1 ቆሮ 15:1-4).

‹‹መለወጥ›› ቃል በቃል መዞር መንገድ መቀየረ ነው፡፡ ወደ አንድ ነገር ስንዞር ለአንድ ነገር ደግሞ ራሳችንን መከልከል ጀርባ መስጠታችን ነው፡፡ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንዞር ከኃጢያትም ዘወር እንላለን፡፡ ከኃጢያት ዘወር ማለትን መጽሐፍ ቅዱስ ነስሐ ይለዋል በክርስቶስ ወደ ‹‹ማመን››፡፡ እንግዲያው ንስሐ እና ማመን የተቆራኙ ናቸው፡፡ ንስሐ እና እምነት በዚህ ክፍል ተጠቅሰዋል 1ተሰ 1፡9 ‹‹ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ።›› ክርስቲያን ያለፈውን በስህተት ሃይማኖት መንገድ ስህተት የሆነውን ሁሉ ወደ ኋላ ጥሎ በውጤቱም ክርስቲያን በመሆን እውነተኛ ለውጥ ያደርጋል፡፡

በቀላሉ ለማስቀመጥ ወደ ክርስትያንነት ለመለወጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢያትህ እንሞተ እና ከሞት እንደተነሳ ማመን አለብህ፡፡ ኃጢያተኛ እንደሆንክ ድኅነት እንደመሚያስፈልግህ በእግዚአብሔር ፊት ማመን ኢየሱስ ክርስቶስም ብቻ ሊያደንህ እንደሚ መቀበል አለብህ፡፡ ከኃጢያት ውደ ኢየሱስ ክርስቶስ ስትመለስ እገዚአብሔር አንደሚያድንህ እና መንፈስ ቅዱስንም ኢዲስ ፍጥረት የሚያደርግህን እንደሚሰጥህ ቃል ገብቶአል፡፡

ክርስትና በትክክለኛው መልኩ ኃይማኖት አይደለም፡፡ ክርስትና እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ህብረት ማድረግ ነው፡፡ ክርስትና እገዚአብሔር ድኅነትን በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ስራ ለሚያምኑ ሁሉ እንደሰጠ መቀበል ነው፡፡ ወደ ክርስትና የተለወጠ ሰው አንድን ኃይማኖት ትቶ ወደ ሌላ ኃይማኖት የመጣ ሰው አይደለም፡፡ ውደ ክርስትና መለወጥ የእግዚአብሔርን ስጦታ በመቀበል የኃጢያትን ይቅርታ በማግኘት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ግላዊ ህብረትን ማደረግ መጀመር ከሞት በኋላ በሰማይ ለዘላለም መኖር ነው፡፡

በዚህ ባነበብከው መልዕክት ምክንያት ወደ ክርስትና መለወጥ ትፈልጋለህ? መልስህ አዎን ከሆነ መጸለይ የሚኖርብህ አጭር ጸሎት ከዚህ በታች ቀርቦልሃል፡፡ ይህን ጸሎት ማለት ወይም ሌላ ጸሎት አያድንህም፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንህ ነው ከኃጢያት ሊያድንህ የሚችለው፡፡ ይህ ጸሎት ለእግዚአብሔር እምነትህን ለመግለጽ እና ስላዘጋጀልህ ድኅነት ለማመስገን ነው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አንተን በድያለሁ ፍርድም ይገባኛል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ልቀበለው የሚገባኝን ፍርድ ስለወሰደልኝ በእርሱ በማመን ይቅር ትለኛለህ፡፡ ስለ ደኅንነት እምነቴን በአንተ ላይ አደርጋለሁ፡፡ ታላቅ ስለሆነው ምህረትህና ፀጋህ ስለዘለአለም ህይወት አመሰግንሃለሁ አሜን!

English


ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ
እንዴት ክርስቲያን ሆኜ መለወጥ እችላለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries