settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ስለ ወሊድ መቆጣጠሪያ ምን ይላል? ክርስቲያን የወሊድ መቆጣጠሪያን መጠቀም አለበት?

መልስ፤


‹‹ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት›› (ዘፍ 1፡28) ተብሎ ሰው በእግዚአብሔር ታዟል፡፡ ጋብቻ በተመቸ በተረጋጋ ሁኔታ ልጆችን ለማፍታት በእግዚአብሔር የተመሰረተ ነው፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ለጆች ግን ዛሬ እንደ ጣጣ እና ሸክም ይቆጠራሉ፡፡ በሰው ህይወት የሥራ መንገድ የኢኮኖሚ ግብ በኑሮ ዘይቤ እና ማህበራዊ ኑሮ ላይ እንደቆሙ የታሰባል፡፡ በአብዛኛው ጊዜ እንዲህ ያለ ራስ ወዳድነት የእርግዝና መከላከያ ለመጠቀም መነሻ ስር ነው፡፡

ራስ ወዳድነትን በመጸራር የወሊድ መቆጣጠሪያን ከመጠቀም ጀርባ መጽሐፍ ቅዱስ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው ብሎ ያቀርባል፡፡ (ዘፍ 4:1; ዘፍ 33:5). ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ሃብት ናቸው፡፡ (መዝ 127:3-5). ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው (ሉቃ 1:42). ለጆች ዘውድ ናቸው፡፡ (ምሳ 17:6). እግዚአብሔር መካን ሴቶችን በልጅ ይባርካል፡፡ (ምሳ 113:9; ዘፍ 21:1-3; 25:21-22; 30:1-2; 1 ሳሙ 1:6-8; ሉቃ 1:7, 24-25). እግዚአብሔር ህጻናት በሆድ ሳለ ይሰራል፡፡ (ምሳ 139:13-16). እግዚአብሔር ልጆች ሳይወለዱ በፊት ያወቃቸዋል፡፡(ኤር 1:5; ገላ 1:15).

በቅርብ የምናገኘው የወሊድ መቆጣጠሪያን የሚቃወም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የምናገኘው በዘፍ 38 የይሁዳ ልጅ ዔር እና አውናን ታሪክ ነው፡፡ ዔር. ትዕማር የተባለችን ሴት አገባ፡፡ ክፉ ሰው ነበርና ሞተ፤ ትዕማር ያለ በልና ልጅ ቀረች፡፡ ለወንድሙም አውናን በዘኍልቍ25፡5-6 በጋብቻ ተሰጠች፡፡ አውናን ያለውን ርስቱን በወንድሙ ፈንታ ለሚወልዳቸው ማካፈል ስላልፈለገ በዚያን ጊዜ በነበረው ልምምድ ዘሩን በማስወገድ ተከላከለ፡፡ ዘፍ 38፡10 ‹‹ይህም ሥራው በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ ሆነበት፥ እርሱንም ደግሞ ቀሠፈው።›› አውናንን ራስ ወዳድነት በተሞላ ልብ ለስጋዊ ስሜቱ ከትእማር ጋር እየተኛ ለወንድሙ ግን ዘር ሊያስቀርለት አልፈለገም፡፡ ይህ ክፍል ብዙውን ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪያን እግዚአብሔር እንደማይፈልግ ለመጥቀስ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ሆኖም ግን አውናን የሞተው ዘሩን በማቋረጡ ሳይሆን ራስወዳድነት በተሞላው ክፉ ተግባሩ ምክንያት ነው፡፡

ልጆችን አለም እኛ እንድናይ በምትነግረን መንገድ ሳይሆን እግዚአብሔር እንደሚያያቸው ልናይ ያስፈልጋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእርግዝና መከላከያ (contraception) አይከለክልም ስንል የእርግዝና መከላከያ (contraception) የማመንጨት (conception) ተቃራኒ ነው፡፡ የእርግዝና መከላከያን መውሰድ አይደለም ተክክልም ስህተትም የሚያደርገው፡፡ ከአውናን እንደምንማረው እርግዝናን ከመቋረጥ ጀርባ የሚኖረው ሞቲቭ የመነሻ ሃሳብ ነው ስህተት ወይንም ትክክል የሚያደርገው፡፡ ሁለት ባልና ሚስት የወሊድ መቆጣጠሪያን የሚጠቀሙት የበለጠ ብዙ ነገር እንዲኖራቸው ከሆን የተሳሳተ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጠሪያን ግን የሚወስዱት የበለጠ በኢኮኖሚና በመንፈሳዊ ብስለት ለመዘጋጀት ለተወሰነ ጊዜ ለማዘግየት ከሆነ የእርግዝና መከላከያን መውሰድ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ እንደገና ሁሉም ነገር ግን ያለው የመነሻ ሃሳብ ሞቲቭ ላይ ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ሁልጊዜም ልጆችን መውለድ መልካም ነገር ነው፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ባልና ሚስት ሆልጊዜም ልጆች እንዲኖራቸው ይጠበቃል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ልጅ ያለመውለድ ፍላጎትን ማንም በእግዚአብሔር ቃል ሲገልጽ አንመለከትም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ ለተወሰነ ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪያን መጠቀምም የሚያከራክር አይደለም፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ስለ ወሊድ መቆጣጠሪያ ምን ይላል? ክርስቲያን የወሊድ መቆጣጠሪያን መጠቀም አለበት?
© Copyright Got Questions Ministries