settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ ለኃጢአታችን ከመሞቱ በፊት ሰዎች እንዴት ይድኑ ነበር?

መልስ፤


ከሰው ውድቀት ወዲህ፣ የመዳን መሠረቱ ዘወትር የክርስቶስ ሞት ነው። ማንም ቢሆን፣ ከመስቀል ቀደም ሲልም ሆነ ከመስቀል ወዲህ፣ ከዚያ ወሳኝ ሁነት በቀር በዓለም ታሪክ ውስጥ ማንም ሊድን አይችልም፣ ። የክርስቶስ ሞት የአለፈውን የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ኃጢአት እና የወደፊቱን የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ኃጢአት ቅጣት ዋጋ ከፍሏል።

ለመዳን ዘወትር የሚያስፈልገው እምነት ነው። ለደኅነት የሆነ የማንም እምነት ባለቤቱ ዘወትር እግዚአብሔር ነው። መዝሙረኛው፣ “በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተባረኩ ናቸው” ብሏል (መዝሙር 2፡12)። ዘፍጥረት 15፡6 የሚነግረን አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፣ ያም ለእግዚአብሔር በቂ ነበር፣ ጽድቅ አድርጎ ሊቆጥርለት (ሮሜ 4፡3-8ንም ተመልከት)። የብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት ሥርዓት ኃጢአትን ሊያስተሰርይ አልቻለም፣ ዕብራውያን 10፡1-10 በግልጽ እንደሚያስተምረው። እሱ ሆኖም፣ ያደረገው፣ የእግዚአብሔር ልጅ ለኃጢአተኛ የሰው ዘር ደሙን ማፍሰሱን ማመላከት ነው።

በዘመናት የተቀየረው ነገር ቢኖር የአማኞች እምነት ይዘት ነው። ምን መታመን እንዳለበት፣ የእግዚአብሔር መስፈርት የሚመሠረተው፣ እስከዛ ጊዜ ድረስ ለሰው ልጆች የሰጠው የራዕይ መጠን ነው። ይህም ቀጣይነት ያለው ራዕይ ይባላል። አዳም በዘፍጥረት 3፡15 እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ አምኗል፣ ይህም የሴቲቱ ዘር ሰይጣንን እንደሚያሸንፍ። አዳም አመነው፣ ለሔዋን በሰጠው ስም (ቁ. 20) እንዲሁም ጌታ እንደተቀበላቸው ወዲያውኑ አመላከተ፣ በቆዳ በመሸፈን (ቁ.21)። በዛን ጊዜ አዳም የሚያውቀው ያንን ነበር፣ ነገር ግን አመነው።

አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፣ በተሰጠው የተስፋ ቃልና፣ በዘፍጥረት 12 እና 15 እግዚአብሔር በሰጠው አዲስ መገለጥ። ከሙሴ በፊት ምንም ቃል አልተጻፈም፣ ነገር ግን የሰው ልጅ እግዚአብሔር ለገለጠው ኃላፊነት ነበረበት። በሞላው ብሉይ ኪዳን፣ አማኞች ወደ ደኅንነት የሚመጡበት ምክንያት፣ አንድ ቀን እግዚአብሔር የኃጢአት ችግራቸውን እንደሚያቃልልላቸው በማመን ነበር። ዛሬ፣ ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት፣ እሱ ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ መውሰዱን እናምናለን (ዮሐንስ 3፡16፤ ዕብራውያን 9፡28)።

በክርስቶስ ጊዜ ስላሉት አማኞችስ፣ ከመስቀሉና ከትንሣኤ በፊት ስለነበሩት? ምንድነው ያመኑት? ክርስቶስ በመስቀል ላይ ለኃጢአታቸው መሞቱን በተሟላ መልኩ ተረድተውታልን? በአገልግሎቱ ኋላ ላይ፣ “ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር” (ማቴዎስ 16፡21-22)። ለዚህ መልእክት የደቀ መዛሙርቱ ምላሽ ምን ነበር? “ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ። አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።” ጴጥሮስና ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ሙሉውን እውነት አላወቁትም፣ ሆኖም ድነዋል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የኃጢአት ችግራቸውን እንደሚያቃልልላቸው በማመናቸው ነው። እነሱ በትክክል እንዴት እንደሚያደርገው አላወቁትም፤ ከአዳም፣ አብርሃም፣ ሙሴ፣ ወይም ዳዊት ባልተሻለ ሁኔታ፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን አምነዋል።

ዛሬ እኛ ከክርስቶስ ትንሣኤ በፊት ከነበሩት ሰዎች ይልቅ የተሻለ መገለጥ አለን፤ ሙሉውን ገጽታ አይተነዋል። “ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን” (ዕብራውያን 1፡1-2)። ደኅንነታችን አሁንም የተመሠረተው በክርስቶስ ሞት ላይ ነው፣ ለደኅንነታችን አስፈላጊው ነገር አሁንም እምነታችን ነው፣ እናም የእምነታችን ባለቤት አሁንም እግዚአብሔር ነው። ዛሬ፣ ለእኛ፣ የእምነታችን ይዘት የሚሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢአታችን የሞተው፣ የተቀበረው፣ እንዲሁም በሦስተኛው ቀን የተነሣው ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡3-4)።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ ለኃጢአታችን ከመሞቱ በፊት ሰዎች እንዴት ይድኑ ነበር?
© Copyright Got Questions Ministries