settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ክርስቲያ መሆን?

መልስ፤


ክርስቲያን ለመሆን የመጀመሪያው ነገር ‹‹ክርስቲያን›› ማለት ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ ነው፡፡ ክርስቲያን የሚለው ቃል የተገኘው በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን በአንጾኪያ ነበር (ሥራ 11፡26)፡፡ ለመጀሪያ ጊዜ ክርስቲያን የተባለው ለስድብ ሊሆን ይችላል፡፡ ቃሉ በመሰረቱ ‹‹ትናንሽ ክርስቶሶች›› ማለት ነው፡፡ ሆኖም ከጊዜ በኃላ በክርስቶስ ያሉ አማኞች ‹‹ክርስቲያን›› የሚለው ቃል ወስደው ራሳቸውን የክርስቶስ ተከታዮች ብለው ለመለየት ተጠቀሙበት፡፡ ቀላል የሆነ ክርስቲያን የሚለው ትርጉም የኢየሱስ ተከታይ ማለት ነው፡፡

ለምንድን ነው ክርስቲያን መሆን ያለብኝ?
ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ አውጆአል፡ ‹‹እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።›› (ማር 10፡45)፡፡ ከዚያም ጥያቄ ተነሳ፤ ለምንድን ነው ዋጋ ሊከፈልልን ያስፈለገው? ‹‹ ransom›› ዋጋ መከፈል የሚለው ቃል ሃሳብ የሚያመለክተው አንድን ሰው ለማስፈታት የሚደረግ ልውውጥን ነው፡፡ ይህ ቃል በመደጋገም ጥቅም ላይ የዋለው ተጠልፎ የተያዘን ልጅ ለልዋጭ የሚሆነው እስከሚከፈል ድረስ መያዝ ከሚለው ጋር የተገናኘ ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶሰ እኛን ከእስራት ለማስፈታት ‹‹ ransom ›› ዋጋን ከፈለልን፡፡ ከምን እስራት? ከኃጢያትና ተከትሎ ከሚመጣው፤ አካላዊ ሞት እና ተከትሎ የሚመጣው ለዘልአለም ከእግዚአብሔር መለየት፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ዋጋውን ‹‹ ransom ›› ምክፈል አስፈለገው? ሁላችንም በሃጢያት ተበከልን (ሮሜ 3፡23)፤ የዘለአለም ሞትም የተገባን ሆንን (ሮሜ 6፡23)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ነው እዳችንን የከፈለው? የኃጢያታችንን እዳ ለመከፈል በመስቀል ላይ በመሞት፡፡ (1 ቆሮ 15:3? 2 ቆሮ 5:21). የኢየሱስ ክረስቶስ ሞት እንዴት የኃጢያታችንን እዳ ሊከፍል ይችላል? ኢየሱስ በአካል የተገለጠ መለኮት ነበር፤ መለኮት እግዚአብሔር ከእኛ እንደ አንዱ ለመሆን ውደ ምድር መጣ ስለዚህ እኛን መሰለ ለኃጢያታችንም ሞተ (ዮሐ 1:1,14). መለኮት የሆነው ኢየሱስ ሞት ዋጋው ወሰን የሌለው ከሆነ የአለምን ሁሉ ኃጢያት ለመክፈል በቂ ነው(1 ዮሐ 2:2)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በኋላ መነሳቱ የእርሱ ሞት በቂ መስዋዕት እንደሆነና ሞትንና ኃጢያትን በትክክል እንዳሸነፈ ይገልጻል፡፡

እንዴት ክርስቲያን መሆን እችላለሁ?
ይህ የተመረጠ ሃሳብ የያዘ ክፍል ነው፡፡ ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሳ እግዚአብሔር ክርስቲያን የምንሆንበትን መንገድ ቀላል አደረገው፡፡ ማድረግ ያለብን ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝ መቀበል ነው፤ ሙሉ በሙሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለሰራናቸው ኃጢያት በሙሉ በቂ እንደሆነ ማመን (ዮሐ 3፡16) እርሱ አዳኛችን እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ማመን (ዮሐ 14፡16፣ ሥራ 4፡12) ክርስቲያን መሆን በጠቅላላው መንፈሳዊ ስርዓቶችን መፈጸም ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ወይንም የተወሰኑ ነገሮችን ማድረግ እና ሌላውንም ከማድረግ መቁጠብ አይደለም፡፡ ክርስቲያን መሆን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ህብረት ማድረግ ነው፡፡ በእምነት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የግል ግንኙነት ማድረግ እርሱ ነው አንድን ሰው ክርስቲያን የሚያስብለው፡፡

ክርስቲያን ለመሆን ዝግጁ ነህ?
ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኝ አድርገህ በመቀበል ክርስቲያን ለመሆን ዝግጁ ከሆንክ ማድረግ የሚጠበቅብህ ማመን ብቻ ነው፡፡ ኃጢያተኛ እንደሆንክ እና የእግዚአብሔር ፍርድ እንዳለብህ ታምናለህ? ኢየሱስ ክርስቶስ ቅጣትህን እንደ እንደወሰደልህ እና ባንተ ቦታ እንደሞተል ተረድተሃል? የእርሱ መስዋዕትነት የኃጢያትህን እዳ ለመክፈል በቂ እነደሆነ ተረድተሃል? ለእነዚህ ሶስት ጥያቄዎች መልስህ አዎን ከሆነ እምነትህን በኢየሱስ በአዳኝህ ላይ አድርግ፤ በእምነት እርሱን ብቻ በማመን ተቀበለው፡፡ ክርስቲያን የሚያደርግህ ይህው ነው፡፡

English


ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ
ክርስቲያ መሆን?
© Copyright Got Questions Ministries