settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ክህደት አምላክ የለሽ ክህደት ምንድን ነው?

መልስ፤


አምላክ የለሽ ክህደት እግዚአብሔር የለም የሚል አመለካከት ነው፡፡ አምላክ የለሽ ክህደት አዲስ ግኝት አይደለም፡፡ በመዝ 14፡1. በዳዊት ከክርስቶስ ልደት በፊት 1000 ዓመት በፊት ተጠቅሶአል ‹‹ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል።›› በቅርቡ አንድ መረጃ አምላክ የለሽ ክህደት የተቀበሉ ሰዎች ቁጥር በምድር ላይ ካሉ ሰዎች 10% ጨምሮአል፡፡ ለምንድን ነው አምላክ የላሽ ከኃዲዎች ቁጥር የጨመረው? እውነት ክህደት አምላክየለሽነት መሆን አሳምኝ ነው?

ለመሆኑ ለምንድን ነው ክህደት ሊኖር እንኳ የቻለው? ለምን እግዚአብሔር ስለመኖሩ በቀላሉ ለሰዎች ራሱን ገልጦ መኖሩን አያረጋግጥም? በእርግጥ እግዚአብሔር ቢገለጥ ሃሳባችን ሊሄድ የሚችለው ሁሉም ሰው ያምንበት ነበር ይሆን የሚል ነው! እዚህ ጋር ነው ችግሩ የእግዘአብሔር ፍላጎት እንዳለ እንሚኖር ብቻ ለማሳመን ራሱን ለሰዎች መግለጥ የእግዚአብሔር ፍላጎት አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ፍላጎት በእምነት በእርሱ እንዲያምኑ (2 ጴጥ 3:9) እና በእምነት የእርሱን የደኅነት ስጦታ እንዲቀበሉ ነው፡፡ (ዮሐ 3:16). እግዚአብሔር በገልጽ መኖሩን በብሉይ ኪዳን ብዙ ጊዜ አሳይቶአል፡፡ (ዘፍ 6-9; ዘጽ 14:21-22; 1 ነገ 18:19-31). ሰዎች መኖሩን አምነው ተቀብለው ነበር? አዎን፤ ነገር ግን ከክፉ መንገዳቸው ተመለሰው እግዚአብሔርን ታዘዙ? አይ ፡፡ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን መኖር በእምነት ካልተቀበለ እንግዲያውስ እሱ ወይም እሷ በትክክል ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸው አድረገው ለመቀበል ዝግጁ አይደሉም፡፡ (ኤፌ 2:8-9). እግዚአብሔር ለሰዎች ያለው እቅድ መኖሩን የሚያምኑ እንዲሆኑ ሳይሆን ክርስቲያኖች እንዲሆኑ ነው፡፡

መጸሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የእግዚአብሔርን መኖር በእምነት መቀበል አለብን፡፡ ዕብ 11፡6፡- ‹‹ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።›› መጸሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን ስናምንና በእርሱ ስንደገፍ የተባረክን እንደሆንን ይነግረናል፡ ‹‹ኢየሱስም፦ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።›› ዮሐ 20፡29

የእግዚአብሔርን መኖር በእምነት የምንቀበለው መሆን አለበት፤ ይህ ማለት ግን በእግዘአብሔር ማመን በአምሮ አስተሳሰብ ተቀባይነት የሌለው ነው ማለት አይደለም፡፡ ስለ እግዚአብሔር ህልውና ብዙ ጥሩ የሆኑ ክርክሮች አሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ህልውና በግኡዙ አለም ላይ በግልጽ እንደሚታይ ይነግረናል፡፡ (መዝ 19:1-4), በተፈጥሮ (ሮሜ 1:18-22), እና በልባችን (መክ 3:11). በዚሁ ሁሉ የእግዚአብሔር መኖር ማረጋገጥ ባይቻል በእምነት ግን የምንቀበለው መሆን አለበት፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በክህደት በአለምላክ የለሽነት /atheism/ ማመንም ብዙ እምነት ይጠይቃል፡፡ ትክክለኛውን አረፍተ ነገር ‹‹እግዚአብሔር የለም›› ብሎ ለማስቀመጥ ያለውን ሁለንም ነገር በትክክል አውቃለሁ ብሎ ስለሁሉም ነገር ማወቅ ይቻላል በአለም ውስጥ ያለውን ሁሉ ለማወቅ እና ለሚታየው ሁሉም ነገር ምስክር መሆን እችላለሁ ብሎ ማወጅ ነው፡፡ እውነት ነው የተኛውም አምላክ የለሽ ኢአማኝ ይህን ሊል አይችልም፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር የለም ብለው ሲሉ ሊሉ የሚችሉት ይህንኑ ነው፡፡ ኢአማኝ ከሃዲዎች /atheism/ ይህን ማረጋገጥ አይችሉም፤ ለምሳሌ፡- በጸሐይ መሃል እንደሚኖር በጁፒተር ያለውን ደመና ማትነን እንደሚችል ወይንም በኔቡላ ትንሽ ርቀት፡፡ እንዚህ ስፍራዎች ለመረዳት ከኛ አቅም ግምት ውጪ ቢሆኑም እግዚአብሔር እንደማይኖርባቸው ማረጋገጥ አይችልም፡፡ አማኝ መሆን እንደሚጠይቀው ሁሉ አምላክ የለሽ ኢአማኝ መሆንም በዙ እምነት ይጠይቃል፡፡

አምላክ የለሽነት/atheism/ ክህደትን ማረጋገጥ አይቻልም፤ የእግዚአብሔር መኖር በእምነት የምንቀበለው ነው፡ ክርስቲያኖቸ የእግዚአብሔርን መኖር በአጽንኦት ያምናሉ እና የእግዚአብሔርን ህልውና መኖር ማመን የእምነት ጉዳይ ነው፡፡ በተማሳሳይ ሁኔታ ደግሞ እግዚአብሔርን ማመን በአዕምሮ ተቀባይነት የሌለው ሃሳብ መሆኑን ደግሞ እንቃወማለን፡፡ የእግዚአብሔር መኖር በግልጽ የሚታይ በደንብ የሚታወቀን አስፈላጊ ከሆነ በፍልስፍና እና በሳይንስም መረጋገጥ ይችላል፡፡ ‹‹ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።›› መዝ 19፡1-4

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ክህደት አምላክ የለሽ ክህደት ምንድን ነው?
© Copyright Got Questions Ministries