settings icon
share icon
ጥያቄ፤

አናይሌይሽን /የኃጢያተኞች ከሞት በኋላ መጥፋት/ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?

መልስ፤


አናይሌይሽን /annihilationism/ የማያምኑ ሰዎች ለዘለአለም በሲኦል አይሰቃዩም ግን በዚህ ፈንታ ከሞት በኃላ ይለያያሉ “extinguished”. ብለው ያምናሉ፡፡ ለብዙዎች አናይሌይሺኒዚም /annihilationism/ የሚማረክ የሚስብ እምነት ነው ምክንያቱም ሰዎች በሲኦል ለዘለአለም ከሚሰቃዩበትን መጥፎ ነገር የተነሳ ነው፡፡ ለነገሩ አንዳንድ አናይሌይሺኒዚም /annihilationism/ ክርክር የሚደግፉ የሚመስሉ ጥቅሶች አሉ፤ በአጠቃላይ መጸሐፍ ቅዱስ ስለ ክፉዎች መጨረሻ ስንመለከት የሚገልጽልን እውነት በሲኦል ዘለአለማዊ ቅጣት እንደሆነ ነው፡፡ የአናይሌይሺኒዚም /annihilationism/ እምነት ከሚከተሉት ትምህርቶች ውስጥ አንዱን ውይም ከዚያ በላይ በትክክል ካለመረዳት የመጣ ነው፡፡ 1/የኃጢያት ውጤት 2/ የእግዚአብሔር ፍርድ 3/የሲኦል ምንነት

የሲኦልን ምንነት በሚመለከት አናይሌይሺኒዚም /annihilationism/ የእሳት ባህርን ትርጉም ምንነት ተሳስቶአል፡፡ እንደሚታወቀው ሰዎች በሚያቃጥል በቀለጠ የመሬት አለት ውስጥ ቢጣሉ በእሳቱ ውስጥ ተበልተው ይጠፋሉ፡፡ ሆኖም ግን የእሳት ባሕር ግን መንፈሳዊም በአይን የሚታየው አካላዊ physical ገጽታ አለው፡፡ ዝም ብሎ የሰው አካል በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል አይደለም፤ ይህ የሰው አካል ነፍስ እና መንፈስ ነው፡፡ መንፈሳዊ ማንነት በአይን በሚታየው እሳት ሊበላ እና ሊጠፋ አይችልም፡፡ ሊሆን የሚችለው የመኑ ሰዎች እንደሚሆኑት ያላመኑ ሰዎችም ለዘለአለማዊነት በተዘጋጀ አካል ይነሳሉ፡፡ (ራዕ 20:13; ሥራ 24:15). እንዚህ አካላት ለዘለአለማዊ እጣ የተዘጋጁ ናቸው፡፡

ዘላለማዊነት አናይሌይሺኒዚም /annihilationism/ ሙሉ በሙሉ በትክክል ሊረዳው ያልቻለው ሌላው አመለካከት ነው፡፡ አናይሌይሺኒዚም የግሪኩን ቃል "aionion" በትጓሜው "eternal" ዘልአለም የሚለውን ቃል ሲያርሙ eternal መሚለው ቃል ትርጓሜ አይደለም በትክክል የሚያመለክተው “age” እድሜ or “eon,” አንድ የተወሰነ የጊዜ ገደብን የሚያመለክት ነው፡፡ ሆኖም ግን በአዲስ ኪዳን በግልጽ aionion የሚለው ቃል አንዳንድ ጊዜ የሚያመለክተው በዘለአለምን ያለውን ጊዜ ነው፡፡ ራዕ 20፡10 ሲናገር፡- ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ። እነዚህ ሶስቱ የተለዩት “extinguished” ግልጽ በሆነ መልኩ በእሳት ባሕር በመጣላቸው አይደለም፡፡ ያላመኑ ሰዎች ዕጣ ለምን ከዚህ የተለየ አልሆነም፡፡(ራዕ 20:14-15)? የሲኦል ዘላለማዊነት ጥሩ ማስረጃ ማቲ 25፡46፡- ‹‹እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።›› በዚህ ጥቅስ ውስጥ የጻድቃንን እና የክፉዎችን መጨረሻ ለመግለጽ ተመሳሳይ ቃል ጥቅም ላይ ውሎአል፡፡ ክፈዎች የሚሰቃዩት ለተወሰነ ጊዜ ቢሆን “age” ቢሆን ጻድቃንም ሰማያዊውን ኑሮ የሚለማመዱት ለተወሰነ ጊዜ ይሆን “age” ነበር፡፡ አማኞች ለዘለአለም በሰማይ የሚሆኑ ከሆነ ክፉዎችም በሲኦል ለዘላለም ይሆናሉ፡፡

ሌላው የተደጋገመ ተቃውሞ አናይሌይሺኒዚም /annihilationism/ ስለ ሲኦል ዘላለማዊነት እግዚአብሔር ክፉዎችን ለዘለአለም በሲኦል የተወሰነ መጠን ላለው ኃጢያት መቅጣት ከጽድቅ መጉደል አይሆንበትም የሚል ነው፡፡ 70 ሰባ ዓመት የኖረን ኃጢያተኛ እንዴት እግዚአብሔር ለዘለአለም ይቀጣዋል? መልሱ የእኛ ኃጢያት የሚያስከትለው ቅጣት ዘለአለማዊ ነው ምክንያቱም ዘለአለማዊውን አምላክ በመቃወም የተደረገ ነው፡፡ ንጉስ ዳዊት ዝሙት በመፈጸምና ሰው ከገደለ በኋላ እንዲህ ነው ያለው መዝ 51፡4፡- ‹‹እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። 4 አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ …›› ዳዊት የበደለው አቢጊያንና ኦሪዮንን ነው፡፡ ዳዊት እንዴት እግዚአብሔርን ብቻ እንደበደለ ሊናገር ይችላል? ዳዊት ያውቃል የተኛውም ኃጢያት እግዚአብሔርን መቃወም መበደል ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘላለማዊና ወሰን የሌለው አምላክ ነው፡፡ በውጤቱም ሁሉም በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ ኃጥያት ዘለአለማዊ ፍርድ ይገባዋል፡፡ ገዳዩ ኃጢያት የምናደርግበት ጊዜ ርዝመት አይደለም፤ ግን ኃጢያትን አድርገን ከምንበድለው ከእግዚአብሔር ባሕሪ ጋር ነው፡፡

የበለጠ ከግል ማንነታችን በተያያዘ ሁኔታ አናይሌይሺኒዚም/annihilationism/ ምናልባት በሰማይ ሆነን የምንወዳቸው ሰዎች በሲኦል እየተሰቃዩ እንዳለ ስናስብ ደስተኛ ላንሆን እንችላለን የሚል ሃሳብ ነው፡፡ ሆኖም ግን በሰማይ ስንሆን ምንም የምናዝንበትና የምናማርርበት ነገር አይኖርም፡፡ ራዕ 21፡4፡- ‹‹እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።›› የምንወዳቸው ሰዎቸ በሰማይ ባይሆኑ 100% ሙሉ በሙሉ እንስማማለን በዚያ የሌሉትና የተፈረደባቸው ኢየሱስ ክርስቶስን ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው፡፡ (ዮሐ 3:16; 14:6). ይህን መረዳት ከባድ ነው፤ ነገር ግን እንርሱን በዚያ ባለማግኘታችን አናዝንም፡፡ ትኩረታችን መሆን ያለበት እንዴት በሰማይ የምንወዳቸው ሰዎች በሌሎበት ልንደሰት እንችላለን መሆን የለበትም ግን እዴት የምንወዳቸውን ሰዎች በከርስቶስ ወዳለው እምነት ልናመጣቸው እንደምንችል መሆን አለበት እናም በዚያ ይሆናሉ፡፡

ሲኦል እግዚአበሔር ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልከውና የኃጢያታችንን ዋጋ እንዲከፍል ያደረገበት ቀዳሚ ምክንያት ነው፡፡ ከሞት በኋላ መለየት “extinguished” የምንሰጋበት እጣ አይደለም ግን ለዘለአለም በሲኦል መሆን ግን በትክክል ነው፡፡ የኢየሱስ ገደብ የሌለወ ሞት ነው የእኛን ገደብ የሌለውን ኃጢያት የከፈለው፤ ስለሆነም በሲኦል ለዘላለም መክፈል አይኖርብንም (2 ቆሮ 5:21). እምነታችንን በእርሱ ስናደርግ ድነናል ይቅርታን አግኝተናል ነጽተናል እናም በሰማይ ዘላለማዊ ቤት ይጠባቀናል፡፡ ግን የኢየሱሰን ዘላለማዊ ህይወት ብንቃወም የውሳኔያችንን ዘላለማዊ ቅጣት እንቀበላለን፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

አናይሌይሽን /የኃጢያተኞች ከሞት በኋላ መጥፋት/ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?
© Copyright Got Questions Ministries