settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ፍጹም እውነት እና አለማቀፋዊ እውነት የተባለ ነገር ሊኖር ይችላል?

መልስ፤


ፍጹም እውነት ወይንም አለማቀፋዊ እውነትን ለመረዳት እውነት እንደሆነ በመተርጎም መጀምር አለብን፡፡ እውነት በመዝገበ ቃላት ‹‹እውነትን ማረጋገጥ ትክክለኛነት፤ አንድን አረፍተ ነገር እወነት እንደሆነ ማረጋገጥ ›› አንዳንድ ሰዎች እውነት የሆነ ተጨባጭ ነገር የለም መላምት እና አመለካከት ብቻ ነው ያለው ሊሉ ይችላሉ፡፡ ሌሎች የሆነ እውነት ወይም ተጨባጭ ነገር አለ ብለው ሊከራከሩ ይችላሉ፡፡

አንድ አመለካከት እውነታን ሊተረጉም የሚቻልበት መንገድ የለም ይላል፡፡ ይህንን አመለካከት የሚቀበሉ ሁሉም ነገር አንጻራዊ ነው የሚል አመለካከት ይይዛሉ፤ ለእነሱ ትክክለኛ እውነት የለም፡፡ በዚህም ምክንያት ፍጹም የሆነ የሞራል ህግ የለም አንድ ተግባር ትክክል ነው ወይም አይደለም መጥፎ ወይም ስህተት ነው ብሎ የሚወስን ሥልጣን የለም፡፡ ይህ አመለካከት ‹‹ከሁኔታ ጋር የተያያዘ ስነ ምግባር›› “situational ethics,” ይመራናል ይህም ትክክል ወይም ስህተት የሆነው ነገር ከሁኔታ ጋር ተለዋዋጭ ነው ብሎ ማመን ነው፡፡ ትክክል ወይም ስህተት የሆነ ነገር የለም ስለዚህ በጊዜው ባለው ሁኔታ ትክክል ነው ብሎ እንደሆነ የሚሰማን እርሱ ትክክል ነው፡፡ በትክክል ከሁኔታ ጋር የተያያዘ ስነምግባር ከግል ስሜት ጋር ወደ ተያያዘ ‹‹ማንኛውም የሚሰማን ትክክል ነው›› የሚል አመለካከትና በግልና በጋራ ትልቅ ጥፋት ወዳለው አመለካከት የህይወት ዘይቤ ይወስደናል፡፡ ይህ ሁሉም እሴቶች እምነት የህይወት ዘይቤ እና እውነት ሁሉ እኩል ዋጋ አላቸው የሚል ማህበረሰብ የሚፈጥር ድህረ ዘመናዊነት ነው፡፡

ሌላኛው አመለካከት የሚይዘው በትክክል ፍጹም የሆነ እውነታ እና ትክክል ያልሆነው መለኪያው አለ የሚል ነው፡፡ እንግዲያውስ ተግባር ትክክል ወይንም ስህተት እንደሆነ እነዚያን ፍጹም የሆኑ መለከያዎችን እንደሚተረጉሙበት ሊወሰን ይችላል፡፡ ፍጹም እውነት እውነታና ሃቅ የማይኖር ከሆነ ትርምስምስ ይከተላል፡፡ የስበት ህግን ለምሳሌ እንውሰድ ፍጹም የተረጋገጠ ባይሆን በአንድ ስፍራ መቆምና መቀመጥ መቻላችንን እስካልተንቀሳቀስን እንርግጠኛ መሆን ጨርሶውኑ አንችልም ነበር፡፡ ወይንም ሁለት እና ሁለት ሁልጊዜ አራት ባይሆን በስልጣኔ ላይ የሚኖረው ጥፋት አስከፊ ይሆን ነበር፡፡ የሳይንስና የፊዚክስ ህጎች ምንም ዋጋ የሌላቸው ይሆኑ ነበር የንግድ ልውውጥ የማይቻል ይሆን ነበር፡፡ ምን አይነት መስቅቅል ይሆን ነበር! ደስ በሚል ሁኔታ ሁለት እና ሁለት አራት ነው፡፡ ፍጹም የሆነ እውነት አለ ማረዳት እና ማግኘትም ይቻላል፡፡

ፍጹም የሆነ እውነት እንደሌለ መናገር ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ ሆኖም ዛሬ ብዙ ሰዎች የትኛውንም አይነት ፍጹም እውነት የሚክደውን ልማዳዊ አንጻራዊነትን ይዘዋል፡፡ ‹‹ፍጹም የሆነ እውነት የለም ለሚሉ›› ጥሩ የሆነው ጥያቄ ‹‹እናንተስ ፍጹም እርግጠኛ ናችሁ;›› የሚል ነው፡፡ አዎን ካሉ እነርሱ ፍጹም የሆነ አረፍተነገር እየተናገሩ ነው ይህው ንግግራቸው ፍጹም የሚባል እንዳለ እያረጋገጡ ነው፡፡ እያሉ ያሉት ፍጹም እውነት የለም በአንድ መልክ ሲሉ በሌላው መልክ ደግሞ ፍጹም እውነት አለ እያሉ ነው፡፡

ከእራስ ጋር ከሚደረግ ግጭት ባሻገር አንድ ሰው ፍጹም እና አለማቀፋዊ እውነት የለም ብሎ ለማለት ሌሎች አሳማኝ የሆኑ ችግሮችን አንድ ሰው ማሸነፍ አለበት፡፡ አንደኛው ሁሉም ሰዎች ወሱን እውቀት እና ውሱን አይምሮ እና አላቸው ስለዚህ ተቀባይነት ሊኖረው በሚችል መልኩ ፍጹም የሆነ አሉታዊ አረፍተ ነገር ቃል ሊሰሩ አይችሉም፡፡ አንድ ሰው በተቀባይነት መልኩ ‹‹እግዚአብሔር የለም›› ሊል አይችልም (ምንም እንኳ ሌሎች ቢችሉም) ምክንያቱም እንደዚህ አይነት ቃል ለማቅረብ ፍጹም የሆነ እውነት ስለ ጠቅላላው አልም ዩኒቨርስ ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከመጨረሳ ያስፈልገዋል፡፡ በሳይንስ የማይቻል ነው፤ ማንኛውም ሰው በአብዛኛው ሊል የሚችለው ‹‹ባለኝ ውስን በሆነ እውቀት እግዚአብሔር አለ ብዬ አላምንም››

ሎላኛው ችግር ፍጹም አለማቀፋዊ እውነትን በመካድ ለመኖር የማይቻለው እውነት እንደሆነ በአእምሮአችን በልምምዳችን የምናውቀው በዚህ አለም የምንመለከተው የምናውቀው ጋር አብሮ ሊሄድ ስለማይችል ነው፡፡ እንደዚህ እንድ ፍጹም እውነት የሆነ ነገር ከሌለ ስለማንኛውም ነገር ትክክለኛ እና ትክክለኛ ያልሆነ ነገር አይኖርም፡፡ ላንተ ትክክል ያልሆነ ነገር ለኔ ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡ በትንሹ በዚህ አይነቱ አንጻራዊነት መነሻነት የሚያጓጓ በሚመስል ሁኔታ ምን እንደ ማለት ነው እያንዳንዱ ሰው የራሱን የሚኖርባቸውን መመሪያዎች ያወጣል እና ትክክል የሚመስለውን ደግሞ ያደርጋል፡፡ የአንድ ሰው የትክክለኛው ነገር መረዳት ከሌላው ሰው ጋር የሚጋጭ እንዲሆን የሚጋብዝ ይሆናል፡፡ ለእኔ የትራፊክ በብራትን ቀይ እየበራ ቢሆንም መጣስ ትክክል በሆን ምን ይፈጠራል? ብዙ ሰዎችን በአደጋ ውስጥ ይከታል፡፡ ወይም ከአንተ መስረቅ ትክክል ቢመስለኝ ለአንተ ደግሞ ትክክል ባይመስል፤ በግልጽ ትክክል ስለሆነውና ስላልሆነው ያለን አመለካከታችን የሚጋጭ ይሆናል፡፡ ፍጹም የሆነ እውነት ከሌለ ሁላችን ተጠያቂ የምንሆንበት መለኪያ አይኖርም እናም ስለምንም ነገር እርግጠኞች አንሆንም፡፡ ሰዎች የፈለጉትን ሁሉ ለማድረግ ነጻ ይሆናሉ፤ መግደል፤ አስገድዶ መድፈር፤ መስረቅ፤ መዋሸት ማታለል …የመሳሰሉት እና ፍትህ አይኖርም ምክንያቱም አንድ ሰው አብዛኛው ህዝብ በአናሳው ላይ መለኪያን ለማስቀመጥና እና ጫና ለመፍጠር መብት አላቸው ላይል እንኳ ይችላል፡፡ ፍጹሙ የሌላትን አለም ለማሰብ በጣም ያስፈራል፡፡

ለመንፈሳዊ አቋም እንዲህ ያለው አንጻራዊነት ውጤቱ ሃይማኖታዊ ግራ መጋባት እውነተኛ የሆነ ሃይማኖት የሌለበት እና እግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ የግንኙነት መንገድ የሌለው ነው፡፡ እንገዲያውስ ሁሉም ሃይማኖቶች ስህተት ሊሆኑ ይችላሉ ምክንያቱም ሁሉም ከዚህ ህይወት ባኋላ ስላለው ነገር ሁሉም ፍጹም እውነት አለን ይላሉ፡፡ በአሁን ጊዜ ለሰዎች ሁለት በትክክል የሚጋጩ ኃይማኖቶች በእኩል ‹‹እውነት›› ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ ለማመን ፤ ሁለቱም ኃይማኖቶች ምንም እንኳ ወደ ሰማይ የሚያስገባ በቸኛ መንገድ አለን ቢሉም ወይም ሁለት ፈጸሞ የሚቃረኑ ‹‹እውነታዎች›› ቢሆኑም ብሎ ማመን ያልተለመደ አይደለም፡፡ በፍጹም እውነት መኖር የማያምኑ ሰዎች እንዲህ ማለትን ይቃወማሉ እና መቻቻል የነገሰበትንዩኑቨርሳሊዝም ሁሉም ኃይማኖቶች እኩል ናቸው ሁሉም እምነት ወደ መንግስተ ሰማይ ይወስዳሉ የሚለውን ሃሳብ ይይዛሉ፡፡ ይህንን አለም አቀፋዊ ሃሳብ የሚይዙ ሰዎች በአጽንኦት መቻቻል አሁን ለሰለጠነው ማህበረሰብ አብይ ህብረተሰብ የሚኮራበት ብቸኛው ፍጹሙ ሲሆን አለመቻቻል ደግሞ ብቸኛው ክፉ እየሆነ መጥቶአል፡፡ ማንኛውም ግትር ቀኖናዊ እምነት በተለይ ደግሞ በፍጹም እውነት ማመን አንደ አለመቻቻል ይቆጠራል ይህውም ደግሞ ፍጹሙ ኃጠያት፡፡ ፍጹም እውነትን የሚቃወሙ ሰዎች በአብዘኛው ጊዜ የሚሉት የፈለከውን ማመንህ ችግር የለውም እምነትህን ሌሎች ሰዎች ላይ ጫና እንዲፈጥር የማተደርግ ከሆነ ነው ይላሉ፡፡ ግን ይህ አመለካከት ራሱ ትክክሉ ወይንም ስህተቱ የቱ ነው የሚል እምነት ነው፤ እና በአብዛኛው ይህን አመለካከት የሚይዙ ራሳቸው አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጫና ለመፍጠር ይሞክራሉ፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲከተሉአቸው የሚፈልጉት የባህሪ መለኪያዎች ያስቀምጣሉ እነርሰ ራሳቸው በሌላው ላይ ላይ ጫና አትፍጠር በሚለው እርስ በራሳቸው በመጋጨት ውስጥ በመግባት ይጥሱታል፡፡ እንደዚህ አይነት እምነት ያላቸው ሰዎች ስለሚያደርጉት ነገር ስለተግባራቸው ኃላፊነት መውሰድ አይፈልጉም፡፡ ፍጹም የሆነ እምነት ካል ፍጹም ትክክል እና ስህተት የሆና መለኪያ አለ እና እኛ ለእነዚያ መለኪያዎች ተጠያዎች ነን፡፡ ይህ ተጠያቂነት ሰዎች ፍጹም የሆነውን መለኪያ ሲቃወሙ የሚቃወሙአቸው ናቸው፡፡

ፍጹሙን አለማቀፈዊውን እውነት መቃወም ከዛ ባህላዊ አንጻራዊነት ጋር ተያይዞ የሚመጣው የማህበረሰብ አስተሳሰብ ውጤት ስለ ህይወት ምንነት የዝግመተ ለውጥ አስተሳሰብ የያዘ ነው፡፡ ተፈጥሮአዊው ዝግመተ ለውጥ እውነት ቢሆን ከዛ ህይወት ትርጉም አይኖረውም፤ እኛ አላማ አይኖረንም፤ እና ፍጹም የሆነ ትክክለኛ እና ስህተት የሆነ ነገር አይኖርም ነበር፡፡ ሰዎችም ደስ እነዳለቸው ለሞኖር ነጻ ይሆኑ ነበር በተግባራቸውም ለማንም ተጠያቂ አይኖራቸውም ነበር፡፡ ሆኖም ግን ምንም ያህል ኃጢያተኛ ሰው የእግዚአብሔርን ህልውና እና ፍጹም እምነትን ቢክድ አንድ ቀን በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ለፍርድ ይቆማሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ይናገራል፡ ‹‹…እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና።የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥›› (ሮሜ 1፡19-22)፡፡

ፍፁም የሆነ እውነት ስለመኖሩ ማረጋገጫ አለ? አዎን፡፡ አንደኛው የሰው ህሊና አለ ያም ‹‹አንድ ነገር›› እርግጠኛ ያደርገናል፤ አንድ ነገር ትክክል ወይም ስህተት እንደሆነ አለም በሆነ መንገድ መሄድ እንዳለበት በውስጣችን ይነግረናል፡፡ ህሊናችን ስህተት የሆነ ነገር እንዳለ በችግር፣ በረሃ፣ በአስገድኖ መድፈር፣ በህመም፣ በክፉ ስራ እንዳለ ይነገረናል እንዲሁም ፍቅር፣ መልካም ማድረግ፣ ምሕረት፣ ሰላምልንጋደልላቸው የሚገባ መልካም ነገር እንደሆነም እንደዚሁ፡፡ ይህ በሁሉም ባህል ልማድ ምንጊዜም ሁል ጊዜም እውነት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የህሊናን ተግባር ይነግረናል (ሮሜ 2፡14-16)፡-‹‹ ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ።ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ በሰው ዘንድ የተሰወረውን በሚፈርድበት ቀን ይሆናል።››፡፡

ሁለተኛው የፍጹም እውነት መኖር ማረጋገጫው ሳይንስ ነው፡፡ ሳይንስ ማለት በቀላሉ እውነትን መፈለግ ነው፤ የምናቀውን ነገር ማጥናት እና ለማወቅ የበለጠ መጠየቅ፡፡ እንግዲያውስ ሁሉም ሳይንሳዊ ጥናቶች ተጨባች እውነታዎች በአለም ላይ አሉ እንዚህም እውነተታዎች መረጋገጥ ይችላሉ በሚል እምነት የተመሰረቱ ለመሆን አስፈላጊ ናቸው፡፡ ከፍጹም እውነት ወጪ ምን የምናጠናው ነገር ይኖራል? አንድ ሰው ሳይንስ እውነት መሆኑን እንዴት ሊያገረጋግጥ ይችላል፡፡ በትክክል የሳይንስ መሰረታዊ ህጎች የተመሰረቱት በፍጹም እውነት መኖር ላይ ነው፡፡

ሦስተኛው የፍጹም እውነት አለማቀፋዊ እውነት መኖር ማረጋገጫው ሃይማኖት ነው፡፡ ሁለም አይማኖቶች ስለ ህይወት ምንነት ላመናገር ለመተርጎም ይሞክራሉ፡፡ እነዚህ ከሰው ልጅ ዝም ብሎ ቀላል ተራ ህይወት ከሞኖር ያለፈ ፍላጎት የሚወለዱ ናቸው፡፡ በሀይማኖት ሰዎች እግዚአብሔርን ይፈልጋሉ፣ መጪውን ጊዜ ተስፋ ያደርጋሉ፣ የኃጢያት ይቅርታን፣ በአዕምሮ ትግላቸው ውስጥ ሰላምን፣ ለጠለቀ ጥያቄያቸው መልስ ይፈልጋሉ፡፡ ሃይማኖት የሰው ዘር የተሻሻለ እንስሳ እንዳልሆነ ማረጋገጫ ነው፡፡ ከፍ ያለ ትልቅ አላማ እንዳለና እና በቸኛ በአላማ የፈጣረው ፈጣሪ እንዳለ እርሱን የማወቅ ጥማትም በውስጡ እንዳስቀመጠ ማረጋገጫ ነው፡፡ በትክክል ፈጣሪ ካለ እርሱ የፍጹሙ እውነት መለኪያ ነው፤ እውነትንም መስጠት ማቆም የእርሱ ስልጣን ነው፡፡

በትክክል ፈጣሪ አለ፤ እርሱንም የእርሱን እውነት በቃሉ ገልጾልናል፤ ይህው መጽሐፍ ቅዱስ፡፡ ፍጹሙን እውነት አለማቀፋዊውን እውነት ማወቅ የሚቻልበት ብቸው መንገድ እውነት የሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በግል ግንኙነት በማድረግ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው እውነትም መንገድም ነኝ ብሎአል፤ እውነተኛው ህይወት እና ብቸኛው የእግዚአብሔር መንገድ (ዮሐ 14፡6)፡፡ እውነታ ፍጹም እውነት አለ፤ ሉዐላዊ የሆነ አምላክ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ እና ራሱን ለእኛ ብግላችን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንድናውቀው የገለጸ እንዳለ ይህን እውነት ይጠቅሳል፡፡ ያ ደግሞ ፍጹም እውነት ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ፍጹም እውነት እና አለማቀፋዊ እውነት የተባለ ነገር ሊኖር ይችላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries