settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለወርጃ ምን ይላል?

መልስ፤


መጸሐፍ ቅዱስ በግልጽ ስለውርጃ አይናገርም፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ስለውርጃ ያለውን አመለካከት ግልጽ የሚያደርጉ ቡዙ ትምህርቶች በቃሉ ውስጥ አሉ፡፡ ኤር 1፡5 አግዚአብሔር በሆድ ሳንሰራ እንደሚያቀን ይናገራል፡፡ መዝ 139፡13-16 ሲናገር እግዚአብሔር በመፈጠራችን እና በማህጸን ስንሰራ ያለውን ተጨማጭ ድርሻ ያስረዳል፡፡ ዘጽ 21፡22-25 ተመሳሳይ የሆነ ቅጣት በማህጸን ውስጥ ያለን ህጻንን እንዲገደል ያደረገና እና የሞት ወንጀልን የፈጸመ ላይ እንደሚሆን ይገልጻል፡፡ ይህ በግልጽ የሚያሳየን እግዚአብሔር በማህጸን ያለ ህጻንን የሚቆጥረው ሙሉ እድገቱን እደጨረሰ ሰው ነው፡፡ ለክርስቲያን ውርጃ ሴት ልጅ በምርጫ የምትወስንበት የመብት ጥያቄ አይደለም፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረን ሰው ሞትና ህይወት የመወሰን ጉዳይ ነው፡፡ (ዘጽ 1፡26-27፤9፡6)

ሌሳው የመጀመሪያው ውርጃን በሚመለከት የክርስቲያኖች የመከራከሪያ ሃሳብ የሚነሳው ‹‹የተረገዘው በመደፈር ቢሆንስ›› የሚል ነው፡፡ አንዲት ሴት ያረገዘችው በአሰቃቂ ሁኔታ በመደፈር ምክንያት ወይንም በዘመዶች መካከል በተፈጸመ ግንኙነት ቢሆንስ ህጻኑን መግደል መልስ መሆን ይችላል? ሁለት ስህተቶች አንድ ትክክለኛ ነገር ሊፈጥሩ አይችሉም፡፡ በመደፈር ምክንያት የተወለደ ህጻን በፍቅር የሚኖሩ ነገር ግን ልጅ መውለድ ላላቻሉ ቤተሰብ ሊሰጥ ይችላል ወይም እናቱ ልታሳድገው ትችላለች፡፡ እንደገና ምንም ያላጠፋው ህጻን በአባቱ ክፉ ስራ መቀጣት የለበትም፡፡

ሁለተኛ የክርስቲያኖች የተለመደ ውርጃን በሚመለከት የክርክር ሃሳብ የሚነሳው ‹‹የእናትየው ህይወት አደጋ ውስጥ በሆንስ;›› የሚል ነው፡፡ ስለእውነቱ ወርጃን በሚመለከት ይህን ጥያቄ መመለስ ከባድ ነው፡፡ በመጀመሪያ ማስታወስ የሚኖርብን ይህን በሚለከት አሁን በዓለም ላይ ከሚፈጸመው ወርጃ 1/10 ይህ አንድ አስረኛውን ብቻ የሚይዝ ነው፡፡ በቁጥር ለሚበልጡ ሴቶች ወርጃ ከአሳማኝነቱ ይልቅ የራሳቸውን ህይወት ለማድረግ የሚፈጸም ነው፡፡ ሁለተኛ እግዚአብሔር የተአምራት አምላክ እንደሆነ እንወቅ፤ እግዚአብሔር የእናቱንም የልጁንም ህይወት በህክምና የለውን ችግሮች አልፎ በመጠበቅ ይችላል፡፡ ሆኖም በመጨረሻ ይህ ወሳኔ መወሰን ያለበት በባልና ሚስት ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው ነው፡፡ አንደዚህ አይነት አጣብቂኝ የሚገጥማቸው ጥንዶች ማድረግ ያለባቸውን ለማወቅ የእግዚአብሔርን ጥበብ መለመን አለባቸው (ያዕ 1፡5)

95% በመቶ የሚሆነው ውርጃ በአሁን ጊዜ የሚፈጸመው ልጅ መውለድ በማይፈልጉ ሴቶች ምክንያት ብቻ ነው፡፡ በመደፈር ወይንም በቤተሰብ መካከለስ በተፈጸመ ግንኙነት፡ በእናት የጤና እክል ምክንያት የሚፈጸመው ከ5 በመቶ በታች ነው፡፡ ከ5 በመቶ በቻች በሆነው አስቸጋሪ የጤና እክል ምክንያትም እንኳ ቢሆን ውርጃ የመጀመሪያው ምርጫ ሊሆን አይችልም፡፡ በማህን ውስጥ ያለ የሰው ህይወት የተኛውም ልጁ እንዲወለድ ሊደረግ የሚችል ጥረት ሁሉ ይገባዋል፡፡

ወርጃን ለፈጸሙ ሰዎች የወርጃ ኃጢያት ከሌሎች ኃጢያቶች በተለየ ሁኔታ ይቅር ሊባል የማይቻል አንዳልሆነ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ሁሉም ኃጢያት ይቅር ይባላል፡፡ (ዮሐ 3:16; ሮሜ 8:1; ቆላ 1:14). ወርጃን የፈጸመች ሴት እንዲሆም ያባረታታ የደገፈ ወንድ ወይንም ይህን የፈጸመ ዶክተር ሁሉም በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው እምነት ይቅርታን መቀበል ይችላሉ፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለወርጃ ምን ይላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries