settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ሞርሞኒዝም ኑፋቄ ነው? ሞርሞኖች የሚያምኑት ምንድን ነው?

መልስ፤


የሞርሞኖች ኃይማኖት ሞርሞኒዝም ተከታዮቹ ከዚህ በፊት የኋለኛው ዘመን ቅዱሳን Latter Day Saints (LDS) ተብለው የሚያወቁ ሲሆን ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ በፊት ጆሴፍ ስሚዝ በተባለ ሰው ተመሰረተ፡፡ በግሉ ከእግዚአብሔር እና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ የግል ጉብኝት እንዳገኘ አብያተክርስቲያናት እና ስርዓተ እምነታቸው ሁሉ በውድቀት ውስጥ እንዳሉ ነገረኝ ይላል፡፡ ስለዚህም ጆሴፍ ስሚዝ አዲስ እምነት በምድር ላይ በቸኛዋ እውነተኛ ቤክርስቲያን “only true church on earth.” ተብለው የሚጠሩትን ለመጀመር ተነሳ፡፡ የሞርሞኒዝም ችግር መጽሐፍ ቅዱስን በሚጋጭ መልኩ ማስፋፋት እና ማሻሻል ነው፡፡ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ እውነት አይደለም እና በቂ አይደለም ብለው ለማመን ምንም ምክንያት የላቸውም፡፡ በእውነት በእግዘአብሔር ማመንና መደገፍ ማለት ባቃሉ ማመን መሉው የእግዚአብሔር ቃል እስትንፋሰ እግዚዚአብሔር ያለበት ይህም ማለት ከእርሱ የመጣ እንደሆነ ማመን ነው፡፡ (2 ጢሞ 3:16).

ሞርሞኖች እስትንፋስ እግዚአብር መገኛ አንድ ብቻ ከመሆኑ ይልቅ አራት ናቸው ብለው ያምናሉ፡ 1) መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በትክክል የተተረጎመ እንደሆነ›› በትክክል እንዳልተተረጎመ የተቆጠረው ክፍል ሁልጊዜ ግልጽ አልተደረገም 2) በስሚዝ የተተረጎመው እና 1830 የታተመው የሞርሞኖች መጽሐፍ፤ ስሚዝ በምድር ላይ ኩሁሉ የሚልቅ ትክክለኛው መጽሐፍ “most correct book” ብሎ የሚጠራው ሲሆን ከየትኛውም መጽሐፍ ይልቅ እንድን ሰው መመሪያዎቹን በመከተል ወደ እግዚአብሔር ይቀርባል ብሏል 3) ስለታደሰችው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮዎችና እና ኪዳኖቹ ዘመናዊው መገለጥ የያዘው ስብስብ 4) በሞርሞኖች በጣም ውድ የሆኑ ትልቅ ዋጋ ያላቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ የጠፉ እምነትና አስተምህሮዎችን ለማብራራት እና በምድር ስላሉ ፍጥረታት የራሱን መረጃ ይጨምራል፡፡

ሞርሞኖች ስለእግዚአብሔር የሚያመኑት ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡ ሁልጊዜም በአለም ላይ ታላቅ የሆነው እሱ አይደለም ነገር ግን ይህን ስፍራ የሚይዘው በመያቋርጥ ጥረት እና በጽድቅ በመኖር ነው፡፡ እግዚአብሔር ‹‹የስጋ አካለ አጥንት እንዳለው እንደ ሰው ተጨባጭ ነው ብለው ያምናሉ›› ሆኖም ግን ከሰለጠኑ የሞርሞን መሪዎች በመለየት ወጣቱ ብሪግሃም አዳም ራሱ እግዚአብሔር ነበር የኢየሱስ ክርስቶስም አባት ነው ብሎ አስተማረ፡፡ ከዚህ በተለየ ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሔር እንዲህ ያምናሉ፡ አውነተኛ የሆነ አንድ አምላክ እግዚአብሔር አለ (ዘዳ 6:4; ኢሳ 43:10; 44:6-8), እርሱ ሁልጊዜም ነበር ሁለጊዜም ይኖራል፡፡ (ዘዳ 33:27; መዝ 90:2; 1 ጢሞ 1:17), አልተፈጠረም ግን ፈጣሪ ነው፡፡ (ዘፍ 1; መዝ 24:1; ኢሳ 37:16). እርሱ ፍጹም እና ከእርሱም ጋር የሚተካከል የለም፡፡ (መዝ 86:8; ኢሳ 40:25). እግዚአብሔር ሰው አይደለም፤ ሆኖም አይውቅም (ዘኁ 23:19; 1 ሳሙ 15:29; ሆሴ 11:9). መንፈስ ነው (ዮሐ 4:24), እና መንፈስ ስጋና አጥንት የለውም፡፡ (ሉቃ 24:39).

ሞርሞኖች ከሞት በኋላ የተለያየ ደረጃ ያለው መንግስት ከሞት በኋላ አለ ብለው ያምናሉ፤ ሰማያዊ መንግስት እና ምድራዊ መንግስት ውጪያዊው መንግስት እና ውጪያዊው ጨለማ የሰው ልጆች መጨረሻ እንደ እምነታቸው እና በዚህ አለም ህይወት እንደሚሰሩት ነው፡፡ ከዚህ በተለየ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ከሞት በኋላ ወደ ሰማይ ወይንም ወደ ሲኦል በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን እምነት መሰረት አንሄዳለን፡፡ እንደ አማኞች ከስጋችን መለየት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ነን (2 ቆር 5:6-8). የማያምኑ ወደ ሲኦል ይሄዳሉ ወይንም ሙታኖች ወደሚኖሩበት (ሉቃ 16:22-23). ኢየሱስ ዳግም ሲመጣ አዲስ አካል እንለብሳለን (1 ቆሮ 15:50-54). ለሚያምኑ አዲስ ሰማይና ምድር ይሆናል (ራዕ 21:1), እና የማያምኑ ለዘለአለም በማይጠፋ እሳት ይጣላሉ (ራዕ 20:11-15). ከሞት በኋላ ለመዳን እድል የለም፡፡ (ዕብ 9:27).

የሞርሞን መሪዎች የኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ መልበስ የእግዚአብሔርና የማርያም አካላዊ ግነኙነት ውጤት ነው ብለው ያስተምራሉ፡፡ ሞርሞኖች ኢየሱስ (god) አማልክት እንደሆነ ያምናሉ ግን ማንኛውም ሰው ዳግሞ አማልክት (god) መሆን ይችላል ብለው ያስተምራሉ፡፡ ሞርሞኖች ደህንነት እምነትንና መልካም ስራን በአንድ ላይ በመፈጸም ይግኛል ብለው ያምናሉ፡፡ ከዚህ በተለየ ክርስቲያኖች በታሪክ ማንም ሰው የእግዚአብሔር ስፍራ ሊኖረው አይችልም ብለው ያምናሉ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡ (1 ሳሙ 2:2). እኛ በእግዚአብሔር ፊት ቅዱስ ልንሆን የምንችለው በእርሱ ባለን እምነት ብቻ ነው፡፡ (1 ቆሮ 1:2). ኢየሱስ የእግዚአብሔር አንድ ልጁ ነው፡፡ (ዮሐ 3:16), ያለ ኃጢያት የኖረ ነውር የሌለበት እርሱ ብቻ ነው፤ አሁን በሰማይ እጅግ ከፍ ያለ ስፍራ አለው፡፡(ዕብ 7:26). ኢየሱስ እና እግዚአብሔር በባሕሪ አንድ ናቸው፡፡ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት የኖረ በመሆኑ ብቸኛ ነው፡፡(ዮሐ 1:1-8; 8:56). ኢየሱስ ራሱን መስዋዕት አድርጎ ሰጥቶናል፤ እግዚአብሔርም ከሞት አስነሳው፤ አንድ ቀን ሁሉም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል፡፡ (ፊሊ 2:6-11). ኢየሱስ በራሳችን ስራ ወደ ሰማይ ልንገባ እንደማይቻል ነግሮናል በእርሱ በማመን ብቻ ነው የሚቻለው፡፡(ማቲ 19:26) ሁላችንም በኃጢያታችን ምክንያት ዘለአለማዊ ሞት ይገባናል፤ ግን የእግዚአብሔር ወሰን የሌለው ፍቅር እንድናመልጥ አደረገን፡፡ “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6:23).

በግልጽ ደኅነትን ለማግኘት ያለወ አንድ ብቸኛው መንገድ ነው እርሱም እግዚአብሔርን ልጁንም ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ነው (ዮሐ 17:3). በስራ አይደለም በእምነት እንጂ (ሮሜ 1:17; 3:28). ማንም ብንሆን ብንም ብንሰራ ይህንን ስጦታ መቀበል እንችላለን፡፡ (ሮሜ 3:22). “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (ሥራ 4:12). ሆኖም ሞርሞኖች በተለምዶ ጓደኝነት የሚያውቁ ተወዳጅ እና ለጋስ ሰዎች ናቸው ስለእግዚአብሔር ማንነት ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ደህንነት የሚገኝበትን መንገድ በተዛባ በሐሰት ኃይማኖት ተታለዋል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ሞርሞኒዝም ኑፋቄ ነው? ሞርሞኖች የሚያምኑት ምንድን ነው?
© Copyright Got Questions Ministries