settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የጌታ ራት ጠቀሜታ ምንድነው / የክርስቲያን ቁርባን?

መልስ፤


የጌታ ራት ጥናት ነፍስን የሚያነሣሣ ልምምድ ነው፣ በያዘው ጥልቅ ትርጉም ምክንያት። በድሮ በፋሲካ አከባበር ወቅት፣ በሞቱ ዋዜማ፣ ኢየሱስ ጠቃሚ የሆነ የአዲሱን ኅብረት ማዕድ አቋቋመ፣ እስከ አሁን ጊዜ የምንጠብቀውን። እሱ የክርስቲያን አምልኮ አንደኛው ሁነኛ ክፍል ነው። እሱ የጌታችንን ሞት እና ትንሣኤ ብሎም በቀጣይ በክብር መመለሱን እንድናስታውስ ያደርገናል።

ፋሲካ እጅግ የተቀደሰ በዓል ነበር፣ በአይሁድ ሃይማኖታዊ ዓመት። እሱም በግብፅ የተደረገውን የመጨረሻውን መቅሠፍት ያስታውሳል፣ የግብፃውያን የበኵር ልጆች በሞቱበት ጊዜ፣ እንዲሁም እስራኤላውያን በተረፉበት ጊዜ፣ በበራቸው መቃን ላይ በተረጨው በበጉ ደም ምክንያት። ከዚያም በጉ ይጠበስና በቂጣ እንጀራ ይበላል። የእግዚአብሔር ትእዛዝም የሚመጣው ትውልድ ሁሉ በዓሉን እንዲያከብረው ተሰጥቷል። ታሪኩ ዘጸአት 12 ላይ ሰፍሯል።

በመጨረሻው ራት ጊዜ— የፋሲካ ክብረ-በዓል— ኢየሱስ እንጀራውን አንሥቶ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀረበ። ቆርሶም ለደቀ-መዛሙርቱ አንደሰጣቸው፣ እንዲህ አለ፣ “ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት። እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው” (ሉቃስ 22:19-21)። እሱም የራት ግብዣውን መዝሙር በመዘመር አጠናቀቀ (ማቴዎስ 26፡30)፣ እናም ወደ ጨለማው ወጡ ወደ ደብረ ዘይት(የዘይት ተራራ)። እዛጋ ነው ኢየሱስ በይሁዳ የተካደው፣ እንደተነበየው። በቀጣዩ ዕለት ተሰቀለ።

የጌታ ራት ፍሬ ነገሮች በወንጌላት ይገኛሉ (ማቴዎስ 26:26-29፤ ማርቆስ 14:17-25፤ ሉቃስ 22:7-22፤ እና ዮሐንስ 13:21-30)። ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ጌታ ራት በ1ቆሮንቶስ 11፡23-29 ላይ ጽፏል። ጳውሎስ በወንጌላት የሌለ መግለጫም አክሎበታል፡ “ስለዚህ ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት። ሰው ግን ራሱን ይፈትን፥ እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ፤ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና፥ ይጠጣልምና” (1ቆሮንቶስ 11:27-29)። እንጀራና ጽዋውን መካፈል ላይ “በማይገባ አኳኋን” የሚለው ምን አንደሆነ እንጠይቅ ይሆናል። እሱ ምናልባት ሊሆን የሚችለው የእንጀራውንና የጽዋውን አውነተኛ ትርጉም ማቃለልና አዳኛችን ለእና ደኅንነት የከፈለውን እጅግ ትልቅ ዋጋ መርሳት ነው። ወይም እሱ ሊሆን የሚችለው ስሜት የሌለውና መደበኛ የአምልኮ ሥርዓት አከባበር እንዲኖር መፍቀድ ወይም ወደ ጌታ ራት ካልተናዘዙት ኃጢአት ጋር መምጣት ይሆናል። የጳውሎስን መመሪያ በመቀበል ረገድ፣ እንጀራውን ከመቁረሳችንና ጽዋውን ከመጠጣታችን በፊት ራሳችንን ልንመረምር ይገባል።

ሌለኛው የጳውሎስ መግለጫ እሱም በወንጌላት ያልተካተተው ፍሬ-ነገር “ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና” (1ቆሮንቶስ 11፡26)። ይህም ለሥነ-ሥርዓቱ የጊዜ ገደብ ያስቀምጣል— ጌታ እስኪመጣ ድረስ። ከእነዚህ አጫጭር ይዘቶች የምንማረው ኢየሱስ እነዚህን ሁለት አነስተኛ ነገሮች እንደ ተምሳሌት ለሥጋውና ለደሙ ተጠቅሞ ለሞቱ ሐውልት እንዳደረጋቸው ነው። እሱም የተጠረበ ዕብነ-በረድ ሐውልት ወይም የተሸለመ ናስ አይደለም፣ ነገር ግን እንጀራና ወይን ነው።

እሱ እንዳወጀው፣ እንጀራው ስለ ተቆረሰው ሥጋው ይናገራል። የተሰበረ አጥንት የለም፣ ነገር ግን አካሉ ክፉኛ ተሣቀይቷል፣ መለየት እስከሚያስቸግር ድረስ (መዝሙር 22:12-17፤ ኢሳይያስ 53:4-7)። ወይኑ ስለ ደሙ ነው የሚናገረው፣ ወዲያው የተቀበለውን አስፈሪ ሞት የሚያመለክት። እሱ፣ ፍጹሙ የእግዚአብሔር ልጅ፣ ስለ ተቤዢ የተነገሩትን ቁጥር የሌላቸው የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ፍጻሜ ሆነ (ዘፍጥረት 3፡15፤ መዝሙር 22፤ ኢሳይያስ 53)። እሱ እንዲህ ባለ ጊዜ፣ “ይሄንን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፣” ለወደፊትም የግድ መቀጠል ያለበት ሥርዓት መሆኑን ሲጠቁም ነው። እሱም ደግሞ የሚጠቁመው፣ ፋሲካ፣ የበግን እርድ የሚጠይቀው፣ ወደፊት የሚመለከት ነው የሚመጣውን የእግዚአብሔር በግ፣ እሱም የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደውን፣ በጌታ ራት ፍጻሜ አገኘ። አዲስ ኪዳን ብሉይ ኪዳንን ተካው፣ ክርስቶስ የፋሲካው በግ (1 ቆሮንቶስ 5፡7)፣ ተሠውቷልና (ዕብራውያን 8፡8-13)። የመሥዋዕት ሥርዓቱ ከዚያን በኋላ አያስፈልግም (ዕብራውያን 9:25-28)። የጌታ ራት/የክርስቲያን ቁርባን ክርስቶስ ስላደረገልን መታሰቢያ ነው፣ እንዲሁም በእሱ መሥዋዕትነት ስለተቀበልነው ደስታ መግለጫ ነው።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የጌታ ራት ጠቀሜታ ምንድነው / የክርስቲያን ቁርባን?
© Copyright Got Questions Ministries