settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ለምንድን ነው አይሁድ አረብ እና ሙስሊሞች እርስ በእርሳቸው የሚጠላሉት?

መልስ፤


በመጀመሪያ ሁሉም አረቦች ሙስሊም ሁሉም ሙስሊሞች አረብ እንዳይደሉ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ አብዛኛዎቹ አረቦች ሙስሊም ቢሆኑም ሌሎች አረብ ያልሆኑ ብዙ ሙስሊሞች አሉ፡፡ በተጨማሪም አረብ ያልሆኑ በጣም ብዙ ሙስሊሞች በኢነዶኔዥያ እና ማሌዢያ አካባቢ አረብ ሙስሊም ከሆኑት በላይ አሉ፡፡ ሁለተኛ ሁሉም አረቦች አይሁዶችን እነደማይጠሉ ማስታወስ በጣም አስፈላጊ ነው፤ ሀሉም አይሁዶች አረቦችንና ሙስሊሞችን አይጠሉም:: አእምሮአቸው በክፉ ነገር የተያዘባቸውን ሰዎች ልንጠነቀቃቸው ይገባላ፡፡ ሆኖም በአጠቃላይ ለመናገር አረብና ሙስሊሞች አይዋደዱም እንዲሁም አይተማመኑም በተገላቢጦሹም እንደዚያው፡፡

ግልጽ የሆነን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንታኔን በዚህ ጉዳይ ብንፈልግ ወደ ኋላ አብርሃም ጋር ይወስደናል፡፡ አይሁዶች የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ዘር ናቸው፡፡ አረቦች ደግሞ የአብርሃም ልጅ የእስማኤል ዘር ናቸው፡፡ አስሜኤል የባሪያይቱ ልጅ ስለነበር (ዘፍ 16፡1-16) ይሰሃቅ ደግሞ የአብርሃምን በረከት እንዲወርስ ተስፋ የተገባለት ስለነበር(ዘፍ 21፡1-13) እርግጥ በሁለቱ ልጆች መካከል ጠላትነት ሊኖር ይችላል፡፡ እስማኤል በይስሐቅ ላይ በመሳቁ ምክንያት (ዘፍ 21:9), ሳራ አብርሃምን አጋርን እና አስመኤልን እንዲያባርራቸው ነገረችው፡፡ (ዘፍ 21:11-21). በተመሳሳይ ይህ በእስማኤል ልብ አለመቀበልን አሰከተለ፡፡ መልአክ ለአጋር ትንቢትን ነገራት እስማኤል እንደሚሆን ‹‹… እጁ በሁሉ ላይ ይሆናል፥ የሁሉም እጅ ደግሞ በእርሱ ላይ ይሆናል እርሱም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ይኖራል።›› (ዘፍ 16:11-12)፡፡

የእስልምና ኃይማኖት አብዛኛዎቹ አረቦች አጥባቂዎች በመሆናቸው ይህንን ጠላትነት አሰፉት፡፡ ቁርአን የሚጋጭ መመሪያዎችን ለሙስሊሙ ስለ አይሁዶች ይሰጣል፡፡ በአንድ በኩል ሙስሊሞች አይሁዶችን እንደውንድም እንዲቀበሉአቸው ያዛል በሌላ በኩል አይሁዶች እስልምናን ካልተቀበሉ እንዲያጠቋቸው ያዛል፡፡ ቁርአን ራሱሰ የተስፋ ቃል ያለው ልጁ የአብርሃም ልጁ እንዳልሆነ የግጭት ሃሳብ ያነሳል፡፡ የዕብራዊያን መጽሐፍ ይስሐቅ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ቁርአን ደግሞ እስማኤል ነው ይለናል፡፡ ቁራን አብርሃም ለእግዚአብሔር ሊሰዋው የነበረው እስማኤል እንደነበር ይስሐቅ እንዳልነበር ያስተምራል (ከዘፍጥረት 22 ጋር በሚጋጭ መልኩ)፡፡የተስፋ ቃሉ ልጅ የተኛው ነው የሚለው ክርክር ዛሬ ላለው የጠላትነት ስሜት አስተዋዕጾ አድርጎአል፡፡

ይሁን እንጂ በይስሐቅና በእስማኤል ከጥንት የነበረው ጥል አሁን በአይሁድና በአረብ መካከል ያለውን ጠላትነት በሙሉ አይገልጸውም፡፡ እውነት ነው ለብዙ ሺ አመታት የመካከለኛው ምስራቅ ታሪክ በተሻለ አንጻራዊ ሰላም እና ልዩነቶች ኖረዋል፡፡ በመጀመሪያ የነበረው የጠላትነት ምክንያት ሌላ ከጊዜ ጋር የመጣ ምንጭ አለው፡፡ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ የተባበሩት መንግስታት የተወሰነ መሬት ለአይሁድ እስራኤል ህዝቦች ሲሰጥ መሬቱ ቀደም ብሎ በአረቦች ተወሮ ነበር (በፓለስትኔናውያን)፡፡ አብዛኛው አረቦች በኃይል ያን መሬት በያዙ ጊዜ ተቃውመው ነበር፡፡ የአረብ ሃገራት ህዝቦች ህብረት ፈጥረው አይሁዶቹ ከምድሩ ሊያስወጧቸው ተዋግተዋቸው ነበር ነገር ግን ተሸነፉ፡፡ አሁንም እስከዛሬ ድረስ በእስራኤልና በአረቦች ወዳጆች መካከል ትልቅ ጠላትነት አለ፡፡ እስራኤላዊያን በትንሽ ምድር ውስጥ በአረቦች ተከበው ይኖሉ ለምሳሌ፡- ዮርዳኖስ ሲሪያ ሰውዲአረቢያ ኢራቅ እና ግብጽ፡፡ ይህ የእኛ አመለካከት ነው ይህውም እንደ እግዚአብሔር ቃል ለመናገር እስሬኤላውያን እንደ ህዝብ በራሳቸው አግዚአብሔር ለያዕቆብ የአብርሃም የልጅ ልጅ በሰጠው መሬት የመኖር መብት አላቸው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአጽንኦት እናምናለን እስራኤል ሰላምን መፈለግ አክብሮትን ለአረብ ወዳጆቻቸው ማሳየት አለባቸው፡፡ መዝ 122:6 ሲናገር ‹‹ ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ አንተንም ለሚወድዱ ልማት ይሁን።››

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ለምንድን ነው አይሁድ አረብ እና ሙስሊሞች እርስ በእርሳቸው የሚጠላሉት? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries