settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ ክርስቶስ ለምንድን ነው በብዙ መከራ ውስጥ የማለፍ ልምምድ የነበረው?

መልስ፤


ኢየሱስ በመከራዎቹ ሲያልፍ በከራዎቹና በመገረፍ በመስቀል ላይ በመሰቀል ተሰቃይቶአል (ማቲ 27፤ ማር 15፤ ሉቃ 23፤ ዮሐ 19)፡፡ ስቃዩ አካላዊ ነበር፡ ኢሳ 52፡14 ሲናገር ‹‹ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል›› መከራው የሚረብሽ ነበር፡ ‹‹እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።›› (2ኛ ቆሮ 5፡21)፡፡ ኢየሰስ የአለም ሁሉ ኃጢያት ሸክም በእርሱ ላይ ነበረበት (1ኛ ዮሐ 2፡2)፡፡ ኢየሱስን እያለቀሰ እንዲጮህ ያደረገው ኃጢያት ነው ‹‹አባቴ አባቴ ስለምን ተውከኝ?›› (ማቲ 27፡47)፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ አስከፊ አካላዊ ስቃይ የእኛን ኃጢያት በመሸከሙ ምክንያት ነው፤ የእኛን ቅጣት ለመቀበል ነው (ሮሜ 5፡8)፡፡

ኢሳያስ ስለ ስቃዩ ተንብዮአል፡ ‹‹የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።›› (ኢሳ 53፡3፤5)፡፡ ይህ ክፍል የኢየሱስን የስቃይ ምክንያት በግልጽ ያስቀምጣል ‹‹ስለ መተላለፋችን›› ለፈውሳችን እና ሰላምን ሊሰጠን፡፡

ኢየሱስ የእርሱ መከራ እርግጠኛ እንደነበር ነግሮአቸዋል፡ ‹‹የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል በሽማግሌዎችም በካህናት አለቆችም በጻፎችም ሊጣል ሊገደልም በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ይገባዋል (ሉቃ 9፡22፤ 17፡25)፡፡ የግድ ይገባዋል የሚለውን ቃል አስተውሉ፤ መከራን ሊቀበል ይገባዋል ሊገደል ይገባዋል፡፡ ለአለም ሁሉ ድኅነት የክርስቶስ መከራ የእግዚአብሔር እቅድ ነበር፡፡

መዝ 22፡14-18 የኢየሱስ ከርስቶስን ስቃይ በመጠኑ ይዘረዝራል፡ ‹‹እንደ ውኃ ፈሰስሁ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ።ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጕሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አሸዋ አወረድኸኝ።ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ።አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።›› ይህና ሌሎች ትንቢቶች እንዲፈጸሙ ኢየሱስ መከራን መቀበል ነበረረበት፡፡

ኢየሱስ ለምንድን ነው በመጥፎ ሁኔታ የተሰቃየው? ንጹው ለኃጢያተኛው የሚሞትበት መርህ የተጀመረው በኤደን ገነት ነው፡፡ አዳምና ሔዋን የሞተ እንስሳ ቆዳ ነውራቸውን ለመሸፈን ለበሱ (ዘፍ 3፡21) ያ ደም በኤደን ገነት ፈሰሰ፡፡ ከዛ ይህ መርህ ወደ ሙሴ ህግ ሄደ ‹‹ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው። ›› (ዘሌ 17፡11፤ ዕብ 9፡22)፡፡ መከራው የመስዋዕትነቱ ክፍል ስለነበር ኢየሱስ መከራን መቀበል ነበረበት፤ ኢየሱስም ‹‹እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።›› ነበር፡፡ የኢየሱስ አካላዊ ስቃይ ለእኛ ኃጢያት የሚከፈለው ከፍያ አካል ነበር፡፡ ተዋጅተናል ‹‹በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።›› (1ጴጥ 1፡19)፡፡

የኢየሱስ የመስቀል ላይ ስቃይ የኃጢያትን አስከፊነት ያሳያል፤ የእግዚአብሔር ቁጣ፤ የሰው ልጆች ጭካኔ፤ እና የሰይጣንን ጥላቻ፡፡ በስቃዩ ቦታ የሰው ዘር የከፋውን ነገር በሰው ልጅ ላይ እንዲያደርግበት ተፈቀደ እርሱ የሰው ልጆችን የሚቤዣቸው እንዲሆን፡፡ ሰይጣን ትልቅ ድል እንዳገኘ አስቦ ይሆናል ግን በመስቀሉ በኩል ነበር ሰይጣንን ኃጢያትን እና ሞትን የሚያሸንፈው፡፡ ‹‹ አሁን የዚህ ዓለም ፍርድ ደርሶአል፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዥ ወደ ውጭ ይጣላል፤ ›› (ዮሐ 12፡31፤ ቆላ 2፡15)፡፡

ኢየሱስ ድኅነትን ለሚያምኑ ሁሉ ሊያረጋግጥ ተሰቃየ ሞተ፡፡ የታሰረበት ምሽት ኢየሱስ በጌተሰማኒ ሲጸልይ ሁሉንም ለእርሱ አስረከበው ‹‹ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር።›› የመከራው ጽዋ ከኢየሱስ አልተወሰደም ሁሉንም ስለ እኛ ጠጣው፡፡ የምንድንበት ሌላ መንገድ አልነበረንም፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ ክርስቶስ ለምንድን ነው በብዙ መከራ ውስጥ የማለፍ ልምምድ የነበረው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries