settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ ወንደሞችና እህቶች ነበሩት?

መልስ፤


የኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሞች በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተጠቅሰዋል፡፡ ማቲ 12፡ 46፤ ሉቃ 8፡19፤ እና ማር 3፡31 ማሪያም እና ወንሞቹ ሊያዩት መጡ ይላል፡፡ ኢየሱስ አራት ወንድሞች እንዳሉት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡ ያዕቆብ ዮሴፍ ስምኦን እና ይሁዳ (ማቲ 13፡35)፡፡ በዮሐ 7፡1-10 ወንድሞቹ በደበአሉ እንዴዱ እና እሱ ከኋላቸው እንደቀረ ይነግረናል፡፡ በሥራ 1፡14 እናቱ እና ወንድሞቹ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ሲጸልዩ ተጠቅሰዋል፡፡ ጋለ 1፡19 ያዕቆብ የኢየሱስ ወንድም እንደነበር ተጠቅሶአል፡፡ በጣም ትክክለኛው መደምደሚያ ኢየሱስ ግማሽ የደም ዘር የነበራቸው ወንድሞች ነበሩት፡፡

አንዳንድ ሮማ ካቶሊኮች እነዚህ ወንድማቹ የአጎቶቹ ልጆች እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን በእያንዳንዱ ክፍል ትክክለኛው ወንድም የሚለው የግሪክ ቃል ተጠቅሶአል፡፡ ቃሉ ሌሎች በተሰቦቹን ሊጠቅስ የሚችል ቢሆንም የተለመደውና ቀጥተኛ ትርጉሙ ግን በአካል ወንድሞቹን ነው፡፡ የአጎት ልጅ ለሚለው ቃል የግሪክ ቃል አለው እናም እርሱ ጥቅም ላይ አልዋለም፡፡ በተጨማሪም እነርሱ የኢየሱስ ክርስቶስ የአጎት ለጆች ቢሆኑ ለምንድን ነው ከኢየሱስ እናት ከማሪያም ጋር ደጋግመው የሚጠቀሱት፡፡ በእናቱ እና በወንድሞቹ ሊያዩት በመጡበት አውድ ውሰጥ የእርሱ ቀጥተኛ ግማሽ የደም ዘር ያላቸው ከመሆናቸው ውጪ የሚሰጠው ሌላ ምንም ፍንጭ የለም፡፡

ሁለተኛው የሮማ ካቶሊክ ክርክር የኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሞችና እህቶች የዮሴፍ ከቀድሞው ትዳሩ የተወለዱ ናቸው ነው፡፡ በየትኛውም ዮሴፍ ከማሪያም በእድሜ ይበልጣል የሚል አመለካከት፤ ቀድሞ ጋብቻ ነበረው፤ ቡዙ ልጆች ነበሩት፤ እና ከሚስቶቹ ውጪ ብቻውን ነበር የሚሉት ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ውጪ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር ያለው ችግር ዮሴፍ ከማሪያም በፊት አግብቶ እንደነበር እና ልጆች እንደነበሩት ምንም አይነት ፍንጭ የለም፡፡ ዮሴፍ ማሪያምን ከማግባቱ በፊት ስድስት ልጆች ከነበሩት ለምንድን ነው ማሪያምና ዮሴፍ ወደ ቤተልሄም ሲሄዱ አብረው ያልተጠቀሱት (ሉቃ 2፡4-7) ወይም ወደ ግብጽ ሲሄዱ (ማቲ 2፡13-15) ወይንም ከናዝሬት በተመለሱበት ጉዞ (ማቲ 2፡20-23)?

እንዚህ በተሰቦቹ የማሪያምና የዮሴፍ ትክክለኛ ልጆች ከመሆናቸው ውጪ ምንም አይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ የለም፡፡ ኢየሱስ ግማሽ የደም ዘር ያላቸው ወንደሞች እና እህቶች የሉትም ብለው የሚቃወሙ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ አይደለም ግን ቀደሞ የማሪያምን ያልተገሰሰ ድንግልና እንዲያምኑ የሆኑበት እርሱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ፤‹‹የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ (ማሪያምን) ድረስ አላወቃትም፤ (ዮሴፍ) ስሙንም ኢየሱስ አለው። ››(ማቲ 1፡25)፡፡ ኢየሱስ የማሪያም እና የዮሴፍ ልጀጆች የነበሩ ግማሽ ደም ያላቸው ቤተሰቦች ግማሽ ደም ወንደሞች እና እህቶች ነበሩት፡፡ ይህ ነው ምንም የማያጨቃጭቀው የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ ወንደሞችና እህቶች ነበሩት? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries