settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ በሞቱ እና በትንሳኤው መሐከል ለሦስት ቀናት የት ነበር?

መልስ፤


1ኛ ጴጥሮስ 3፤18-19፤ “ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤” እያለ ይጠቅሳል፡፡ በቁጥር 18 “በመንፈስ” የሚለው ሐረግ በትክክል ልክ “በሥጋ” እንደሚለው ሐረግ ተመሳሳይ አደረጃጀት አለው፡፡ ስለዚህ “መንፈስ” የሚለውን ቃል ልክ እንደ “ሥጋ” ከተመሳሳይ ግዛት ጋር ማዛመዱ ተመራጭ ይመስላል፡፡ ሥጋ እና መንፈስ የክርስቶስ ሥጋ እና መንፈስ ናቸው፡፡ “በመንፈስ ህያው ሆነ” የሚሉት ቃላቶች የክርስቶስን ኃጥአት የመሸከም እና ሰዋዊ የሆነው መንፈሱ ከአብ በመለየቱ ሊመጣ ያለውን የሞት እውነታ ያመለክታል (የማቴዎስ ወንጌል 27፤46)፡፡ በማቴዎስ ወንጌል 27፤46 እና ወደ ሮሜ ሰዎች 1፤3-4 እንዳለው ንጽጽሩ በሥጋ እና በመንፈስ መሐከል ነው እንጂ በክርስቶስ ሥጋ እና በመንፈስ ቅዱስ መሐከል አይደለም፡፡ ክርስቶስ ለኃጥአት መሰዋቱ ባበቃበት ጊዜ መንፈሱ ተቋርጦ የነበረውን ህብረት እንደገና አደሰ፡፡

1ኛ ጴጥሮስ 3፤18-22 በክርስቶስ ሥቃይ እና በክብሩ (ቁጥር 22) መሐከል አስፈላጊ የሆነውን መያያዝ ይገልጻል፡፡ በእነዚህ ሁለት ክስተቶች መሐከል ስለ ተከሰተው ነገር ትክክለኛ መረጃ የሚሰጠው ጴጥሮስ ብቻ ነው፡፡ በቁጥር 19 “ሰበከ” የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን የወንጌልን ስብከት ለመግለጽ የተለመደው ቃል አይደለም፡፡ በትክክለኛው የምሥራቹን መናገር ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ተሰቃይቶ በመስቀል ሞተ፤አካሉም ለሞት ታልፎ ተሰጠ እና ኃጥአት በሆነ ጊዜ መንፈሱ ሞተ፡፡ ነገር ግን መንፈሱ ህያው ሆነ እና ለአብም ሰጠ፡፡ ጴጥሮስ እንደሚለው በሞቱ እና በትንሳኤው መሐከል አንድ ወቅት “በእሥር ላለች ነፍስ” ለየት ያለ አዋጅ አድርጓል፡፡

በእሱ ለመጀመር፤ጴጥሮስ ወደ ሰዎቹ እንደ “መናፍስት” ሳይሆን እንደ “ነፍሳት” አመለከተ (3፤20)፡፡ በአዲስ ኪዳን “መናፍስት” የሚለው ቃል የሰዎች ልጆችን ሳይሆን መላእክትን ወይም ዲያብሎስን ለመግለጽ ጠቅሟል፤ እና ቁጥር 22 ይህንን ትርጉም ያለው ይመስላል፡፡ በተጨማሪም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢየሱስ ገሃነምን እንደ ጎበኘ በየትም ሥፍራ አልተነገረንም፡፡ የሐዋሪያት ሥራ 2፤31 (እንደ አዲሱ የአሜሪካውያን መጽሐፍ ቅዱስ) ወደ "ሄድስ" ሄደ ይላል፤ ነገር ግን "ሄድስ" ገሃነም አይደለም፡፡ "ሄድስ" የሚለው ቃል የሙታን ዓለም፤ትንሳኤን የሚጠባበቁበት ጊዜያዊ የመቆያ ሥፍራን፤ ያመለክታል፡፡ የዮሐንስ ራዕይ 20፤11-15 በ አዲሱ የአሜሪካኖች መጽሐፍ ቅዱስ ወይም በአዲሱ ዓለም አቀፍ ትርጉም ውስጥ በሁለቱ መሐከል ያለውን ግልጽ ልዩነት ይሰጣል፡፡ ለጠፉት ገሃነም ቋሚ እና የመጨረሻ የፍርድ ቦታ ነው፡፡ ሄድስ ጊዜያዊ ሥፍራ ነው፡፡

ጌታችን መንፈሱን ለአብ ሰጠ፤ሞተ፤እናም በተወሰነ ጊዜ በሞት እና በትንሳኤ መሐከል፤ የሙታንን ዓለም፤ ለመናፍስቶች (ምናልባት የወደቁ መላዕክቶችን፤የይሁዳ መልዕክት 6 ተመልከት) በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከጥፋት ውኃው በፊት በኖህ ዘመን ከነበሩት ጋር ከተዛመዱት፤ መልዕክቱን ያደረሰበትን ሥፍራ፤ ጎበኝቷል፡፡ ቁጥር 20 ይህንን ግልጽ ያደርጋል፡፡ ጴጥሮስ ለእነዚህ በእሥራት ውስጥ ለነበሩት መናፍስቶች ያወጀውን ነገር አልነገረንም፤ነገር ግን መላዕክቶች ሊድኑ ስለማይችሉ የሥርየት መልዕክት ሊሆን አይችልም (ወደ ዕብራውያን ሰዎች 2፤16)፡፡ ምናልባት በሰይጣን እና በሠራዊቱ ላይ የተነገረ የድል አዋጅ ነበር (1ኛ ጴጥሮስ 3፤22፤ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፤15)፡፡ በተጨማሪ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤8-10 ክርስቶስ ወደ “ገነት” (የሉቃስ ወንጌል 16፤20, 23፤43) መሄዱን እና ከሞቱ በፊት በእርሱ አምነው የነበሩትን ሁሉ ወደ መንግሥተ-ሰማይ መውሰዱን ለማመልከት ይመስላል፡፡ ምንባቡ ተከስቶ ስለነበረው ነገር በመጠን ሰፊ የሆነ ዝርዝር አይሰጥም፤ነገር ግን ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን የሚስማሙበት ነገር ይህ “ምርኮኛውን ወደ ምርኮ መራ” ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ያ ሁሉ ክርስቶስ በሦስቱ ቀናቶች፤ በሞቱ እና በትንሳኤው መሐከል፤በትክክል ክርስቶስ ምን እንዳደረገ መጽሐፍ ቅዱስ በአጠቃላይ ግልጽ አይደለም ለማለት ነው፡፡ ይመስላል ፤ምንም እንኳን እሱ በወደቁት መላዕክቶች ወይም በማያምኑት ላይ ድልን በመስበክ ላይ የነበረ ቢሆንም፡፡ በእርግጠኝነት ልናውቅ የምንችለው ኢየሱስ ለሰዎች ለድነት ሁለተኛ ዕድል በመስጠት ላይ እንዳልነበረ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሁለተኛ ዕድል ሳይሆን ከሞት በኃላ (ወደ ዕብራውያን ሰዎች 9፤27) ፍርድን እንደምንጋፈጥ ይነግረናል፡፡ በእርግጠኝነት ኢየሱስ በሞቱ እና በትንሳኤው መሐከል፤በትክክል ክርስቶስ ምን በማድረግ ላይ እንደነበር ግልጽ የሆነ መልስ የለም፡፡ ምናልባት አንድ ጊዜ ወደ ክብር ከደረስን የምንገነዘበው ምስጢራቶች ናቸው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ በሞቱ እና በትንሳኤው መሐከል ለሦስት ቀናት የት ነበር?
© Copyright Got Questions Ministries