settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መንፈስ ቃዱስ ማነው?

መልስ፤


ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነት ብዙ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች አሉ፡፡ ጥቂቶች መንፈስ ቅዱስን እንደ ረቂቅ ኃይል ይመለከቱታል፡፡ ሌሎች መንፈስ ቅዱስን እግዚአብሔር ለክርስቶስ ተከታዮች የገለጠው ማንነት የሌለው ኃይል እንደሆነ ይገረዳሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነት ምን ይላል? በቀላሉ ሲቀመጥ መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንደሆነ ያውጃል፡፡ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ አካል፤ አእምሮ ያለው ማንነት ፤ ስሜት እና ፈቃድ ያለው እንደሆነ ይነግረናል፡፡

መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር የመሆኑ እውነታ የሐዋሪያት ሥራ 5፡3-4ን ጨምሮ በብዙ ቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ በግልጽ ታይቷል፡፡ በዚህ ቁጥር ውስጥ ሐናንያ መንፈስ ቅዱስን ለምን እንደዋሸ ሊጠይቀው ጴጥሮስ ተገናኘው እናም “እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን እንዳልዋሸ” ነገረው፡፡ መንፈስ ቅዱስን መዋሸት እግዚአብሔርን መዋሸት እንደሆነ ያ ግልጽ አዋጅ ነው፡፡ በተጨማሪም መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንደሆነ ማወቅ እንችላለን ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ባህሪያት ይዟል፡፡ ለምሳሌ የእሱ በሁሉ ሥፍራ የሚገኝ መሆኑ በመዝሙረ ዳዊት 139፤7-8 ውስጥ ታይቷል “ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።” ከዚያ በ1ኛ ቆሮንቶስ 2፡10-11 የሁሉን አዋቂነቱን ባህርይ በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ እናያለን፡፡ “መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም።”

መንፈስ ቅዱስ በእርግጥ መለኮታዊ ማንነት እንደሆነ ያን ማወቅ እንችላለን ምክንያቱም አዕምሮ፣ ስሜቶችን እና ፈቃድ አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ያስባል፤ያውቃልም (1ኛ ቆሮንቶስ 2፤10)፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሊያዝን ይችላል (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤30)፡፡ መንፈስ ለእኛ ይማልድልናል (ወደ ሮሜ ሰዎች 8፤26-27)፡፡ እንደ ፈቃዱ ውሳኔዎችን ያደርጋል (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡7-11)፡፡ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፤ የሥላሴ ሦስተኛው ሰው ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በእውነተኛው እንደ አጽናኝ እና አማካሪ ይሠራል፤ ኢየሱስ እንደገባው ተስፋ ይሆናል (የዮሐንስ ወንጌል 14፡16፣26፣15፡26)

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መንፈስ ቃዱስ ማነው?
© Copyright Got Questions Ministries