settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መንፈስ ቅዱስ ከአማኝ ፈጽሞ ሊለይ ይችላልን?

መልስ፤


በቀላሉ ሲቀመጥ፣ አይደለም፣ መንፈስ ቅዱስ እውነተኛ አማኝን ፈጽሞ አይተውም። ይህም በተለያዩ በርካታ ምንባቦች አዲስ ኪዳን ላይ ተገልጧል። ለምሳሌ፣ ሮሜ 8፡9 ይነግረናል “…የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም።” ይህ ቁጥር እጅግ ግልጽ በሆነ መልኩ እንደሚያመለክተው፣ አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መገኘት ከሌለው፣ እንግዲያውስ ያ ሰው አልዳነም ማለት ነው። ስለዚህ፣ መንፈስ ቅዱስ አማኙን የሚተወው ከሆነ፣ ያ ሰው ከክርስቶስ ጋር ያለውን የመዳን ግንኙነት አጥቷል ማለት ነው። ይህም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክርስቲያኖች ዘላለማዊ ደኅንነት ከሚያስተምረው ጋር ይቃረናል። ሌለኛው ቁጥር፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሕይወት ቋሚ ማደሪያ መገኘት የሚናገረው የሐንስ 14፡16 ነው። እዚህጋ ኢየሱስ የሚያስቀምጠው፣ አብ ሌላ ረድኤት ይሰጣችኋል፣ “ለዘላለም ከእናንተ ጋር ይሆን ዘንድ” በሚል ነው።

መንፈስ ቅዱስ አማኝን ፈጽሞ እንደማይተወው የሚናገረው ሐቅ ደግሞ ኤፌሶን 1፡13-14 ላይ ተመልክቷል፣ እዚያም አማኞች በመንፈስ ቅዱስ “የታተሙበት” የተባለው፣ “እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።” በመንፈስ የመታተሙ የሚለው ስዕል አንደኛው ባለቤትነት እና ባለመብትነት ነው። እግዚአብሔር የዘላለም ሕይወትን ቃል ገብቷል፣ በክርስቶስ ለሚያምኑት ሁሉ፣ እናም እንደ ዋስትና እሱ ተስፋውን ይጠብቃል፣ እሱ መንፈስ ቅዱስን ልኳል፣ እስከ መቤዠት ቀን ድረስ በአማኝ ላይ ይድር ዘንድ። ለመኪና ወይም ለቤት ግዢ ቅድሚያ ክፍያ እንደሚደረግ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ለሁሉም አማኞች ቅድሚያ ክፍያ ሰጥቷል፣ በቀጣይ ከእርሱ ጋር ለሚኖራቸው ግንኙነት፣ በእነርሱ ላይ ያድር ዘንድ መንፈስ ቅዱስን በመላክ። አማኞች ሁሉ በመንፈስ ለመታተማቸው የሚገልጸው ሐቅ ደግሞ 2 ቆሮንቶስ 1፡22 እና ኤፌሶን 4፡30 ላይ ይገኛል።

በቀዳሚው የክርስቶስ ሞት፣ ትንሣኤ፣ እና ወደ ሰማይ ዕርገት፣ መንፈስ ቅዱስ ከሰዎች ጋር “የና እና ሂድ” ግንኙነት አለው። መንፈስ ቅዱስ በንጕሥ ሳኦል ላይ አድሮበት ነበር፣ ነገር ግን ከዚያም ከእርሱ ራቀ (1 ሳሙኤል 16፡14)። በምትኩም መንፈስ በዳዊት ላይ መጣ (1 ሳሙኤል 16፡13)። ከቤርሳቤህ ጋር ከፈጸመው ዝሙት በኋላ፣ ዳዊት መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ እንዳይወሰድ ፈርቶ ነበር (መዝሙር 51፡11)። መንፈስ ቅዱስ ባስልኤልን እንዲያበቃው ሞልቶት ነበር፣ ለማደሪያው ድንኳን የሚሆኑትን ነገሮች ያበጅ ዘንድ (ዘጸአት 31፡2-5)፣ ነገር ግን ይህ ስለ ቋሚ ግንኙነት የተገለጸ አይደለም። ይህ ሁሉ ተለውጧል፣ ከኢየሱስ ወደ ሰማይ ዕርገት በኋላ። ከበዓለ ሃምሳ ቀን ጀምሮ፣ መንፈስ ቅዱስ በቋሚነት በአማኞች ላይ ማደር ጀመረ (ሐዋ. 2)። የመንፈስ ቅዱስ በቋሚነት ማደሩ እግዚአብሔር ዘወትር ከእኛ ጋር የመሆኑ ተስፋ ፍጻሜ እና ፈጽሞ እንደማይተወንም የሚያሳይ ነው።

መንፈስ ቅዱስ አማኝን ፈጽሞ እንደማይተወው ሁሉ፣ በኃጢአታችን ምክንያት ግን ሊሆን ይችላል “መንፈስ ቅስዱስን የምናጠፋው” (1 ተሰሎንቄ 5፡19) ወይም “መንፈስ ቅዱስን የምናሳዝነው” (ኤፌሶን 4፡30)። ኃጢአት ዘወትር ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን ግንኙነት ላይ መዘዝ/ውጤት አለው። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት በክርስቶስ እንደተጠበቀ ሁሉ፣ በሕይወታችን ያለ ያልተናዘዝነው ኃጢአት ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ኅብረት ወደ ኋላ ይጎትተዋል፣ እናም መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የሚሠራውን ሥራ ፈጽሞ ሊያጠፋው ይችላል። በዚያን ምክንያት ነው ኃጢአታችንን መናዘዝ እጅግ ጠቃሚ የሚሆነው፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር “ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው” (1 ዮሐንስ 1፡9)። ስለዚህ፣ መንፈስ ቅዱስ ፈጽሞ እንደማይተወን ሁሉ፣ የእርሱ መገኘት ያለው ጠቀሜታና ደስታ ሊርቀን ይችላል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መንፈስ ቅዱስ ከአማኝ ፈጽሞ ሊለይ ይችላልን?
© Copyright Got Questions Ministries