settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር / መጽሐፍ ቅዱስ የጾታ ጠበቃ ነው?

መልስ፤


ሴክስቲዝም አንድ ጾታ ነው፡፡ በአብዛኛው ወንድ ነው በሌላው ጾታ ላይ የበላይነት ያለው፤ በአብዛኛው ወንድ በሴት ላይ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዘመኑ ለሴቶች ባለው አስተሳሰብ አድልዎ ፈጣሪ እንደሆነ የሚመስሉ ብዙ ማስረጃዎችን ይዟል፡፡ ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ድርጊት ሲገልጽ መጽሐፍ ቅዱስ ያንን ድርጊት የሚደግፍ ነው ማለት አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ወንድ ሴቶችን ከአንድ ንብረት ትንሽ ከፍ እንዳለች አድርገው ብቻ የሚያስተናግዱ እንደነበሩ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፤ ግን ያንን ድርጊትን እግዚአብሔር ይደግፋል ማለት አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከኛ ህብረተሰብ ይልቅ ነብሳችንን በመለወጥ በማደስ ላይ ያተኩራል፡፡ እግዚአብሔር የተቀየረ ልብ የሚቀየር ባህሪን እንደሚያስከትል ያውቃል፡፡

በብሉይ ኪዳን ዘመናት በአጠቃላይ ባህሎች በመላው ዓለም ሁሉ የዘር ሐረጋት ስርዓት የሚከተሉ ናቸው፡፡ ያ የታሪክ ሁኔታ በጣም ግልጽ ነው፤ በቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ ሳይሆን በማህበረሰቦች ላይ በሚተገበረው ሕግ ውስጥም ጭምር፡፡ በዘመናዊ እሴት ስርዓቶች እና በአለማዊው የሰዎች አመለካከት "ያጾታ አድሎ" "sexist." ይባላል፡፡ ሰዎች ሳይሆኑ እግዚአብሔር በኅብረተሰቡ ውስጥ ትዕዛዝ ደንግጎአል፡፡ እሱ ደግሞ የአስተዳደሩ መርሆዎች ደራሲ ይሁን እንጂ ልክ እንደ ሌሎቹ ነገሮች የወደቀው ሰው ይህን ትእዛዝ አላከበረውም፡፡ ይህም በታሪክ ውስጥ የወንድና የሴቶች ሁኔታ እኩልነት እንዳይኖር አድርጓል፡፡ በዓለም ላይ የምናገኘው መገለልና አድልዎ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ የሰዎች መበላሸት እና የኃጢአት መግቢያ ውጤት ነው፡፡ ስለዚህ የጾታ አድሎ "sexism" ቃል እና ልምምድ የኃጢአት ውጤት ነው ማለት ትክክል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደረጃ በደረጃ የሚገለጠው እና የሚመራን ለጾታዊ ግንኙነት አድሎ እና በእርግጥ የሰው ዘር ኃጢአተኛ ድርጊቶች ፈውስ እንድንሆን ነው፡፡

በእግዚአብሔር የሥልጣን ሹመቶች መካከል ያለውን መንፈሳዊ ሚዛን ለማግኘት እና ለመንከባከብ ወደ ቅዱሳት መጻሕፍት መመልከት አለብን፡፡ አዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳን ፍፃሜ ነው፤ ስለዚህ ትክክለኛውን የሥልጣን ተዋረድ እና ሁሉም ሰው የታመመበትን የኃጢያት ፈውስ የሰው ዘር ሁሉ ችግር እና በፆታ ላይ የተመሰረተ መድልዎን መርሆዎችን እናገኝበታለን፡፡

የክርስቶስ መስቀል ታላቁ እኩል አድራጊ ነው ዮሐንስ 3:16 እንዲህ ይላል "ማንም ሰው የሚያምን" ይላል ማንንም ሳይተው ሁሉንም የሚያጠቃልል ቃል ነው፤ በማኅበረሰቡ ውስጥ በአዕምሮአዊ ችሎታ ወይም በጾታ ላይ በመመስረት ማንም ሳይቀር ሁሉንም የሚያጠቃልል መግለጫ ነው፡፡ በተጨማሪም ለመዳን ያለንን እኩል የሆነ እድላችንን በገላትያ ያለ ምንባብ ይናገራል፡፡ ‹‹በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።››. "(ገላ 3: 26-28) በመስቀል ላይ የጾታ ልዩነት አድሎ የለም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በሁለቱም ጾታዎች ወንዶች እና ሴቶች የኃጢአት ውጤትን በትክክል በሚገልጸው መልኩ የጾታ አድሎ ያለበት ‹‹Sexis›› አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉንም አይነት የኃጢአት አይነቶች ይዘግባል፤ ባርነት እና እስራት እና የታላላቅ ጀግኖችን ውድቀቶችን ይዘረዝራል፡፡ ሆኖም ግን በእግዚአብሄር ላይ እና ባስቀመጠው ስርዓት ላይ ለተደረገው ኃጢአት እና ለድነት የተሰጠው መፍትሄ ከእግዚአብሔር ጋር ስለሚሆን ትክክለኛ ግንኙነት ሁሉ ነው፡፡ብሉይ ኪዳን እጅግ የላቀውን መሥዋዕት በጉጉት ይጠባበቅ ነበር፤ ለኃጢአትም በየትኛውም ጊዜ መስዋዕት ይደረግ ነበር ከእግዚአብሔር ጋር የማስታረቅን አስፈላጊነትን እያስተማረ ነበር፡፡ በአዲስ ኪዳን "የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው በግ" ተወለደ፤ ሞተ ተቀበረ እና እንደገናም ተነሣ ከዚያም ወደ እርሱ ወደ ሰማይ አረገ እና በዚያም ለእኛ ይማልዳል፡፡ ከኃጢያት መዳን የተገኘው በእርሱ በማመን ነው፤ እሱም የጾታ አድሎ ድርጊትን ያካትታል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የጾታ አድሎ ‹‹sexism›› ክስ የሚመሰረተው በቅዱሳት መጻህፍት እውቀት ማጣት ላይ ነው፡፡ በሁሉም እድሜ ያሉ ወንዶችና ሴቶች እግዚአብሔር የሰጣቸውን ቦታቸውን ይዘው << ጌታ እንደሚላቸው >> በሚኖሩበት ጊዜ በጾታ መካከል አስገራሚ ሚዛን ይሆናል፡፡ ያ ሚዛን እግዚሐብሔር የጀመረበት ነው እናም የሚያበቃውም እሱ ነው፡፡ ለተለያዩ የኃጢአት ውጤቶች አላስፈላጊ የሆነ ትኩረት አለ እንጂ ለስሩ ለዋናው ችግር አይደለም፡፡ እውነተኛ እኩልነት ከእግዚአብሔር ጋር በክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር በሚሆን የግል መታረቅ ብቻ ነው፡፡ "እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል" (ዮሐንስ 8:32).

በተጨማሪም ለወንዶች እና ለሴቶች የተለያዩ የሥራ ድርሻዎችን እንዳሉአቸው መጽሐፍ ቅዱስ ማሳሰቡ የፆታዊ አድሎአዊነት አያስከትልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ወንዶች በአብያተ ክርስቲያናትና በቤት የመሪነት ሚና እንዲጫወቱ እግዚአብሔር እንደሚጠብቅባቸው በግልጽ ይናገራል፡፡ ይህ ሴቶችን ዝቅተኛ ያደርገዋል? በፍፁም አይደለም፡፡ ይህ ማለት ሴቶቹ እምብዛም ብልጥ አይደሉም ችሎታ የሌላቸው ወይም በእግዚአብሔር ፊት እንደ ጥቂቶች ይታያሉ ማለት ነው? በፍፁም አይደለም! ይህ ምን ማለት ነው በአለም በኃጢአት በተበላሸ አለም ውስጥ መዋቅር እና ስልጣን መኖር አለበት፡፡ እግዚአብሔር የሥልጣንን ተወረድ ለእኛው ጥቅም አስቀምጦአል፡፡ የጾታ አድሎ የእነዚህን ተግባሮች መኖር ሳይሆን የእነዚህን ተግባሮች አላግባብ መጠቀምን ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር / መጽሐፍ ቅዱስ የጾታ ጠበቃ ነው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries