settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር ወንድ ወይም ሴት ነው?

መልስ፤


ቅዱስ ቃሉን ስንመረምር ሁለት እውነታዎች ግልፅ ናቸው፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔር መንፈስ ነው እናም የሰብዓዊ ባህሪያት ወይም ገደቦች የለውም፡፡ ሁለተኛ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙት ማስረጃዎች በሙሉ እግዚአብሔር ራሱን ለሠው ልጅ በወንድ ጾታእንደገለፀ ይስማማሉ፡፡ በመጀመር የእግዚአብሔርን እውነተኛ ተፈጥሮ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር አካል ‹‹Person›› ነው፤ በግልጽ እንደሚታየው እግዚአብሔር ሁሉንም የአካልን ባህርያት ስለሚያሳይ እግዚአብሔር ፍቃድ እውቀት እና ስሜቶች አለው፡፡ እግዚአብሔር ተግባቦት እና ህብረት አለው፡፡ የእግዚአብሔር አካላዊ ተግባራት ሁሉ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ተረጋግጠዋል፡፡

ዮሐንስ 4፡24 እንደሚለው፡- ‹‹እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።›› እግዚአብሔር መንፈሳዊ አካል እንደመሆኑ መጠን እሱም ሰብዓዊ ቁስ አካል የለውም፡፡ ሆኖም ግን አንዳንዴ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው ዘይቤያዊ አነጋገር ሰው ስለ እግዚአብሔር ዕውቀት እንዲኖረው ለማድረግ ነው፡፡ ይህ በሰዎች ባህሪያት እግዚአብሔርን መግለጽ "አንትሮፖሞርፊዝም" ይባላል፡፡ አንትሮፖሞርፊዝም በቀላሉ ስለ እግዚአብሔር (መንፈሳዊ አካል) ስለ ማንነቱ ለሰው ልጆች ስለ ቁሳዊ አካላት ለመነጋገር ነው፡፡ ሰውነት አካላዊ ስለሆነ ከቁሳዊው ዓለም ውጪ ስለነዚያ ነገሮች ባለን መረዳት ላይ ውስን ነን፡፡ ስለዚህ አንትሮፖሞርፊዝም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ለመረዳት ይረዳናል፡፡

አስቸጋሪነቱ አንዳንድ ነገሮች የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ መሆኑን ለመመርመር ነው፡፡ ዘፍጥረት 1፡26-27 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።››

ወንዶችም ሆኑ ሴቶች እንደ እግዚአብሔር የተፈጠሩ ናቸው፤ ምክንያቱም እንደ እግዚአብሔር አእምሮ ፍቃድ ስሜት ስሜትና የሞራል ጥንካሬ ያላቸው ከመሆናቸውም በላይ ከሌሎቹ ፍጥረቶች ሁሉ ይበልጣሉ፡፡ እንስሳት የሞራል ስብዕና አቅም የላቸውም እንዲሁም እንደ ሰው ልጅ ቁስ አካልነት የሌላቸው አካላት የላቸውም፡፡ የሰው ልጅ ብቻ የእግዚአብሔር አምሳል ያለው መንፈሳዊ አካል ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ከፈጠረው ጋር ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንዲኖረው አድርጓል፡፡ ለዚህ ዓላማ የተነደፈው ብቸኛው ፍጥረት ሰብአዊ ፍጡር ነው፡፡ያ በመሆኑም ወንድ እና ሴት ከእግዚአብሔር አምሳል የተቀረጹ ናቸዉ፡፡ እነሱም የእግዚአብሔር ትንሽ «ቅጂዎች» አይደሉም፡፡ እውነታው ወንድ እና ሴት መኖሩ እግዚአብሔር ወንድና ሴት መለያዎች እንዲኖረው አይጠይቅም፡፡ አስታውስ በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠር ከቁሳዊ አካል ጠባዮች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡.

እግዚአብሔር መንፈሳዊ አካል መሆኑን እና ቁስ አካላዊ ባህሪያት እንደሌለው እናውቃለን፡፡ ይህ እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጆች ሊገልጥ ስለሚችልበት መንገድ ገደብ የለውም፡፡ ቃሉ እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጆ ያሳወቀበትን መገለጥ ሁሉ ይዞአል፤ ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር የሚገልፅ ብቸኛ ዋና ምንጭ ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚነግሩንን ጥቅስ ስንመለከት እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ዘር እንደገለጠ የሚያሳዩ በርካታ ማስረጃዎች አሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር "አባት" በማለት ወደ 170 የሚጠቅሱ ማጣቀሻዎች አሉት፡፡ አስፈላጊ ከሆነ አንድ ሰው ወንድ ካልሆነ አባት ሊሆን አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ራሱን ለሰው በሴት መልክ ሊገልጥ ቢፈልግ "እናት" የሚለው ቃል በእነዚህ ስፍራዎች ይሆናል እንጂ "አባት" የሚለው አይሆንም ነበር፡፡ በብሉይ እና አዲስ ኪዳናት ውስጥ የወንድ ጾታ ተውሳኮች በተደጋጋሚ ጊዜ እግዚአብሔር በሚመለከት ጥቅም ላይ ውሎአል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን እንደ አባት በብዙ ጊዜያት ጠቅሶታል እንዲሁም በሌሎች አጋጣሚዎች ስለ እግዚአብሔር የወንድ ጾታን ተጠቅሞአል፡፡ በወንጌላት ውስጥ ብቻ ክርስቶስ "አባ" የሚለውን ቃል ወደ 160 ጊዜ ያህል በቀጥታ ተጠቅሞበታል፡፡ ክርስቶስ በዮሐንስ 10፡30 ላይ "እኔና አብ አንድ ነን" በማለት የተናገረው ሐሳብ ትኩረት የሚስብ ነው፡፡ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው አምሳል በመገለጥ የአለምን የኃጢያት ዋጋ ለመክፈል በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ እንደ እግዚአብሔር አብ ኢየሱስም ራሱን በወንድ ጾታ መልክ ራሱን ገልጾአል፡፡ ቃሉ ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር ብዙ የወንድ ተውላጠ ስም የተጠቀመባቸውን ሌሎች በርካታ ማስረጃዎችን ይዘረዝራል፡፡

የአዲስ ኪዳን መልእክቶች (ከሐዋሪያት ሥራ አንስቶ እስከ ራእይ) ወደ 900 የሚጠጉ ጥቅሶችን የያዘ ሲሆን ቴኦስ (በግሪክኛ ተባዕታይ) የሚለው ስም ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር በቀጥታ የሚጠቀስ ነው፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ስለ እግዚአብሔር በቁጥር ብዙ ማጣቀሻዎች በወንድ መጠሪያ ስሞች ቅጽል ስሞች ተውላጸ ስሞች በግልጽ ተቀምጧል፡፡ አምላክ ሰው ባይሆንም ለሰው ራሱን ለመግለጥ የወንድ መጠሪያን መርጧል፡፡

በተመሳሳይም ኢየሱስ ክርስቶስም በወንዶች መለያ ስሞች እና ተውላጠ ስሞች በምድር ላይ ሲመላለስ በመደጋገም ተጠቅሶአል፡፡ የብሉይ ኪዳኖች ነብያት እና የአዲስ ኪዳን ሐዋርያት እግዚአብሔር እና ኢየሱስ ክርስቶስ በተባዕታይ ስሞች እና ማዕረጎች ይጠቀሳሉ፡፡ ሰው ማንነቱን በቀላሉ እንዲረዱት እግዚአብሔር በዚህ መልክ መገለጡን መረጠ፡፡ለእግአብሔር ማንነት ገደብ ማስቀመጥ ተገቢ ስላይደለ እርሱን ‹‹በሳጥን ውስጥ ለማስገባት ማስገደድ›› እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር ወንድ ወይም ሴት ነው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries