settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ለምን እግዚአብሔር ቀናተኛ ነው?

መልስ፤


<ቅናት> የሚለውን ቃል እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋለ መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ እሱን ለመግለጽ በዘፀአት 20፡5 ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው የቅንአት ኃጢያትን ለመግለፅ ከተጠቀሙበት የተለየ ነው፡፡ (ገላትያ 5 20) "ቅናት" የሚለውን ቃል ስንጠቀምበት እኛ የሌለን የሆነ ነገር ባለው ሰው ላይ የምንቀናበት ነው፡፡ አንድ ሰው ሌላው ሰው ጥሩ መኪና ወይም ቤት (ንብረቶች) ስላለው ሊቅናበት ወይም ሊመቀኝ ይችላል፡፡ ወይም አንድ ሰው በሌላው ሰው ችሎታ ለምሳሌ የአትሌቲክቲክስ ችሎታ ስላለው በሌላው ሰው ላይ ሊቀና ወይም ምቀኝ ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላው ምሳሌ ደግሞ አንድ ሰው በሌላው ሰው ውበት ምቀኛ ሊሆን ወይም ሊቀና ይችላል፡፡

በዘጸአት 20 5 ውስጥ እግዚአብሔር የሚቀናው አንድ ሰው አንድ የሚፈልገው ወይም የሚያስፈልገውን ስላለው አይደለም፡፡. ዘጸአት 20፡4-5 እንዲህይላል ‹‹በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። "እግዚአብሔር አንድ ሰው ለእሱ ትክክለኛ የሆነ ነገር ለሌላ ሲሰጥ ቀናተኛ መሆኑን ልብ በል፡፡

እነዚህ ጥቅሶች የሚናገሩት ለእግዚአብሔር ለርሱ ብቻ አምልኮ ከማድረግ ይልቅ ለእነዚያ ጣዖታት አድርገው ስለ መስገድ እና እነዚያ ጣዖታትን በማምለክ ላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር የእርሱ የሆነውን የአምልኮና የአገልግሎት ባለቤትነት አለው፡፡ እሱ (እግዚአብሔር በዚህ ትዕዛዝ እንደገለጸው) ከእግዚአብሔር ሌላ ማንኛውንም ነገር ማምለክ ወይም ማገልገል ኃጢአት ነው፡፡ እኛ የሌለንን ነገር ሌላው ሰው ሲኖረው ያንን ስንመኝ እና ስንቀና እርሱ ቅንአት ነው፡፡ ቅንአት የሚለውን ቃል እግዚአብሔር ቀናተኛ ነኝ ሲል በተለየ መንገድ ነው፡፡ እርሱን የሚቀናው ለእርሱ ብቻ የተገባው አምልኮ እና አገልግሎት ለሌላው ሲሰጥ ነው፡፡

ምናልባት አንድ ልዩ ምሳሌ ልዩነቱን እንድንረዳ ያስችለናል፡፡ አንድ ባል አንድ ሰው ከሚስቱ ጋር እንደማለለ ከተሰማው ለመቅናት መብት አለው፤ ሚስቱን ለማሽኮርመም መብት ያለው እሱ ብቻ ነው፤ ይህ ዓይነቱ ቅንዓት ኃጢአት አይደለም፡፡፡ ይልቁንስ ሙሉ በሙሉ ተገቢ ነው፡፡ አምላክ ለአንተ ነው ባለው ነገር መቅናት ተገቢ ነው፡፡ ቅናት የእኛ ያለሀነውን ነገር መፈለግ መመኘት ነው፡፡ አምልኮ ምስጋና ክብር እና ውዳሴ የእርሱ ብቻ ነው ምክንያቱም በእውነትም ለእርሱ ብቻ ነውና፡፡ ስለዚህ, እግዚአብሔር አምልኮ ምስጋና ክብር ለጣዖታት ሲሰጥ ቀናተኛ ነው፡፡ ይህም ሐዋርያው ጳውሎስ በ2 ኛ ቆሮንቶስ 11፡2 ውስጥ የገለጠው ዓይነት ቅንዓት ነው "በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁ…"

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ለምን እግዚአብሔር ቀናተኛ ነው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries