settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር ለምን በብሉይ ኪዳን በጣም የተለየ ሆነ ከአዲስ ኪዳኑ ይልቅ?

መልስ፤


በዚህ ጥያቄ ዋነኛ ነጥብ ላይ መሠረታዊ የሆነ ያለመረዳት ችግር አለ፣ ይህም ብሉይም ሆነ አዲስ ኪዳናት ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ በሚገልጹት ላይ። ሌለኛው የዚህ መሠረታዊ አስተሳሰብ ማሳያ፣ ሰዎች፣ “የብሉይ ኪዳኑ እግዚአብሔር ቁጡ ሲሆን የአዲስ ኪዳኑ እግዚአብሔር ደግሞ የፍቅር አምላክ ነው” ሲሉ ነው። ሐቁ ነገር፣ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቀጣይነት ያለው መገለጥ፣ ስለራሱ ለእኛ የሆነ፣ ይህም በታሪካዊ ሁነቶች እና ከሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት በኩል ነው። በታሪክ ውስጥ የሚነሡትን ስለ እግዚአብሔር የሆኑ የተዛነፉ መረዳቶች፣ እነሱም እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ምን ይመስላል የሚለውን ከአዲስ ኪዳን ጋር በማወዳደር የሚነሡ ናቸው። ሆኖም፣ ማንም ብሉይንም ሆነ አዲስ ኪዳንን ሲያነብ እግዚአብሔር ከአንደኛው ኪዳን ወደ ሌለኛው እንደማይለያይ ይረዳል፤ እናም፣ የእግዚአብሔር ቁጣም ሆነ ፍቅር በሁለቱም ኪዳናት ተገልጸዋል።

ለምሳሌ፣ በሙሉው ብሉይ ኪዳን፣ እግዚአብሔር የሚገለጠው፣ “ርኅሩህና ጸጋን የተሞላ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየ፣ ፍቅርና ታማኝነቱ የበዛ፣” እንደሆነ ነው፣ (ዘጸዓት 34፡6፤ ዘኅልቍ 14፡18፤ ዘዳግም 4፡31፤ ነህምያ 9፡17፤ መዝሙር 86፡5፣ 15፤ 108፡4፤ 145፡8፤ ኢዩኤል 2፡13)። እናም በአዲስ ኪዳንም፣ የእግዚአብሔር ፍቅርና ደግነት እንዲሁም ምሕረት ተገልጿል፣ ይልቁንም ምላት ባለው እውነት፣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወድዷልና” (ዮሐንስ 3፡16) በሞላው ብሉይ ኪዳን፣ በተመሳሳይ መልኩ ከእስራኤል ጋር አባታዊ ፍቅር ለልጅ እንደሚደረገው ይተባበር ነበር። እነሱ በፍቃዳቸው ኃጢአት በሠሩበትና ጣዖታትን ማምለክ ሲጀምሩ እግዚአብሔር ይቀጣቸው ነበር። እናም፣ ባዳናቸው ጊዜ ስለ ጣዖቶቻቸው ይጸጸቱ ነበር። ይኸው እግዚአብሔር ነው ከአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ጋር የሚተባበረው። ለምሳሌ፣ ዕብራውያን 12፡6 እንዲህ ይለናል፣ “ጌታ የሚወዳቸውን ይገሥጻልና፣ የተቀበላቸውን ልጆች ሁሉ ይቀጣቸዋል?”

በተመሳሳይ መልኩ፣ በሞላው ብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ፍርድና ቁጣ በኃጢአት ላይ ሲወርድ እንመለከታለን። በተመሳሳይ፣ በአዲስ ኪዳንም የእግዚአብሔርን ቁጣ አሁንም እንመለከታለን፣ “እውነትን በዐመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ከሰማይ ይገለጣልና” (ሮሜ 1፡18)። ስለዚህ፣ በግልጽ፣ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ከነበረው ይልቅ በአዲስ ኪዳን ልዩነት የለውም። እግዚአብሔር በተለየ ባሕርዩ የሚለዋወጥ አይደለም። እኛም ምናልባት ከሌሎቹ ገጽታዎች ይልቅ በቃሉ ውስጥ በተወሰኑ አንቀጾች የሰፈረውን፣ አንደኛውን የባሕርዩን ገጽታ ተመልክተን ነው እንጂ፣ እግዚአብሔር ራሱ አይለወጥም።

መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብና ስናጠና፣ እግዚአብሔር በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን አንድ እንደሆነ ግልጽ ይሆንልናል። ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ 66 ራሳቸውን የቻሉ፣ በሁለት (ወይም ደግሞ በሦስት) ክፍለ ዓለማት፣ በሦስት የተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉ፣ በግምትም ከ1500 ዓመታት በላይ በፈጀ ጊዜ የተጻፉ፣ ከ40 በላይ በሆኑ ደራሲዎች የተጻፉ፣ እሱም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አንድነቱን ጠብቆ ሳይቃረን የሚሄድ ለመሆን የቻለ ነው። በእሱም ምን ያህል አፍቃሪ፣ መሐሪ፣ እና ጻድቅ አምላክ በሁሉም ዓይነት ሁኔታዎች ከኃጢአተኛ ሰዎች ጋር የሚገናኝ ነው። በእውነቱ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው ልጆች የተጻፈ የእግዚአብሔር የፍቅር ደብዳቤ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር ለፍጥረቱ፣ በተለይም ለሰው ልጆች በቃዱ ሁሉ ተጠቅሷል። በሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በፍቅርና በምሕረት ሰዎችን ይጠራል ከእሱ ጋር ለሚኖር የተለየ ኅብረት፤ ይህም የሚገባቸው ሆኖ አይደለም፤ ነገር ግን እሱ ባለጸጋና መሐሪ አምላክ ስለሆነ፣ ለቁጣ የዘገየ እና ፍቅርና ደግነቱ እውነተኛነቱ የበዛ ስለሆነ ነው። እንዲሁም በተጨማሪ የምንመለከተው ቅዱስና ጻድቅ የሆነው አምላክ እሱም ቃሉን የማይታዘዙት፣ እሱን ለማምለክ ወደ ኋላ የሚሉትንና፣ ሌሎች የራሳቸው ፍጥረት የሆኑ አማልክትን የሚያመልኩትን ሊፈርድባቸው ይችላል። (ሮሜ ምዕራፍ 1)

ከእግዚአብሔር ጻድቅና ቅዱስ ባሕርይ የተነሣ ሁሉም ኃጢአት— ያለፈው፣ የአሁኑ፣ እና የወደፊቱ ሊፈረድበት ይገባል። እግዚአብሔር ግን በብዙ ፍቅሩ የኃጢአትን ዋጋ ከፍሎ የመታረቅን መንገድ አዘጋጀ፤ ስለሆነም ኃጢአተኛው ሰው ከቁጣው ሊያመልጥ ይችላል። ይህንን አስደናቂ እውነት በ1ኛ ዮሐንስ 4፡10 ላይ እናገኛለን፡ “ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” በብሉይ ኪዳን፣ እግዚአብሔር የመሥዋዕት ሥርዓት ሰጥቶ ነበር፣ እሱም ለኃጢአት ሥርየት የሚገኝበት። ሆኖም፣ ይህ የመሥዋዕት ሥርዓት ጊዜያዊ ነበር፣ እሱም ወደሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያመለክት፣ በመስቀል ላይ የሞተው ፍጹም የሆነ የኃጢአት ለውጥ ሥርየት። በብሉይ ኪዳን ተስፋ የተደረገው አዳኝ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ ከዳን ተገለጠ። በብሉይ ኪዳን በራዕይ ብቻ የነበረው፣ የእግዚአብሔር የመጨረሻ የፍቅሩ መግለጫ የሆነው፣ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን በመላክ፣ ሙሉ ክብሩን በአዲስ ኪዳን ገለጠው። ሁለቱም፣ ብሉይም ሆነ አዲስ ኪዳን የተሰጡት “ለደኅንነታችን አስተዋዮች ሊያደርጉን ነው” (2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡15)። ኪዳናቱን ቀረብ ብለን ስናጠና፣ እግዚአብሔር “እንደ ጥላ እንደማይለወጥ” ያስረዱናል (ያዕቆብ 1፡17)።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር ለምን በብሉይ ኪዳን በጣም የተለየ ሆነ ከአዲስ ኪዳኑ ይልቅ?
© Copyright Got Questions Ministries