settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር ክፉን ፈጥሯልን?

መልስ፤


በመጀመሪያ የሚመስለው፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ከፈጠረ፣ እናም ክፉው በእግዚአብሔር ተፈጥሯል ማለት ነው። ሆኖም ግን፣ ክፉው “ነገር” አይደለም፣ እንደ ዐለት ወይም ኤሌትሪክ። የእንስራ ክፉ ሊኖራችሁ አይችልም። ክፉው የራሱ የሆነ ሕላዌ የለውም፤ እሱ በርግጥ የመልካም አለመኖር ነው። ለምሳሌ፣ ቀዳዳዎች በእርግጥ አሉ፣ ነገር ግን የሚኖሩት በሌላ ነገር ላይ ነው። የቆሻሻ አለመኖርን ባዶ እንለዋለን፣ ዳሩግን ከቆሻሻው ሊለይ አይችልም። ስለዚህ እግዚአብሔር ሲፈጥር፣ የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደነበር እሙን ነው። እግዚአብሔር ከሠራቸው መልካም ነገሮች አንዱ፣ ፍጥረታት መልካምን ለመምረጥ ፍቃድ ያላቸው መሆኑ ነው። ትክክለኛ ምርጫ ለማካሄድ፣ እግዚአብሔር የሚፈቅደው ነገር ነበር፣ መልካምን ከመምረጥ ባሻገር። ስለዚህ፣ እግዚአብሔር እነዚህን መላእክት እና ሰዎችን መልካምን ይመርጡ ዘንድ አልያም መልካምን ይንቁ (ክፉ) ፈቀደላቸው። በሁለት መልካም ነገሮች መካከል መጥፎ ግንኙነት ሲፈጠር፣ ያንን ክፉ ብለን እንጠራዋለን፣ ዳሩግን ያ “ነገር” አይሆንም፣ እግዚአብሔር እንዲፈጥረው የሚፈለግ።

ምናልባት ተጨማሪ መግለጫ ሊረዳ ይችላል። አንድ ሰው፣ “ብርድ አለ ወይ?” ብሎ ቢጠይቅ መልሱ፣ “አዎን” ሊሆን ይችላል። የሆነ ሆኖ፣ ይህ የተሳሳተ ነው። ብርድ ሊኖር አይችልም። ብርድ የሙቀት አለመኖር ነው። በተመሳሳይ፣ ጨለማ አይኖርም፤ እሱ የብርሃን አለመኖር ነው። ክፉ የመልካም አለመኖር ነው፣ ወይም ሻል ባለው፣ ክፉ፣ የእግዚአብሔር አለመኖር ነው። እግዚአብሔር ክፉን ሊፈጥር አይሆንለትም፣ ነገር ግን መልካም እንዳይኖር ሊፈቅድ ይችላል።

እግዚአብሔር ክፉውን አልፈጠረም፣ ነገር ግን ክፉውን ሊፈቅድ ይችላል። እግዚአብሔር ክፉውን ባይፈቅድለት ኖሮ፣ ሰዎችም ሆነ መላእክት እግዚአብሔርን የሚያገለግሉት በምርጫ ሳይሆን በግዴታ ይሆን ነበር። እሱ የፈቀደውን ብቻ የሚደርጉ “የተሞሉ” “ሮቦቶች” እንዲሆኑ አልፈለገም። እግዚአብሔር የክፉውን መኖር ፈቅዶ፣ እኛ እንዳሻን እሱን በፈቃዳችን እናገለግለው ወይም አናገለግለው ዘንድ ነጻ ምርጫ ፈቀደልን።

እንደ ውስን የሰው ልጆች፣ ውስን ያልሆነውን እግዚአብሔርን በሙላት ልንረዳው አንችልም (ሮሜ 11፡33-34)። አንዳንዴ እግዚአብሔር አንድ ነገር ለምን እንዳደረገ ያወቅን ይመስለናል፤ ኋላ ላይ ግን እኛ በመጀመሪያ ካሰብነው ዓላማ የተለየ መሆኑን እንደርስበታለን። እግዚአብሔር ነገሮችን የሚመለከተው ከቅዱስ፣ ዘላለማዊ ሐሳብ አንጻር ነው። እኛ ነገሮችን የምንመለከተው ከኃጢአተኛ፣ ምድራዊ፣ እና ከጊዜያዊ እይታ አኳያ ነው። እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ለምን አስቀመጠ፣ አዳምና ሔዋን ኃጢአት ሠርተው ክፉውን፣ ሞትን፣ እና መከራን በሰው ልጆች ሁሉ ላይ እንደሚያመጡ እያወቀ? እሱስ ለምን ሁላችንንም ፈጥሮ በመንግሥተ ሰማያት አይተወንም ነበር፣ ፍጹማንና ያለ መከራ እንድንሆን አድርጎ? እነዚህ ጥያቄዎች በበቂ ሁኔታ ምላሽ ሊያገኙ አይችሉም፣ በዚህኛው ዘመን። እኛ ለማወቅ የምንችለው እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ቅዱስ እና ፍጹም የሆነና ግቡም እሱን የሚያከብር እንደሆነ ነው። እግዚአብሔር የክፉን መኖር የፈቀደው ለእኛ ትክክለኛ ምርጫ ለመስጠት፣ ይህም እናመልከው እንደሆነ ነው። እግዚአብሔር ክፉን አልፈጠረም፣ ነገር ግን እንዲኖር ፈቅዷል። እሱ ክፉውን ባይፈቅድ ኖሮ፣ እኛ እሱን የምናመልከው በራሳችን ፍቃድና ምርጫ ሳይሆን በግዴታ ይሆን ነበር።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር ክፉን ፈጥሯልን?
© Copyright Got Questions Ministries