settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር ሐሳቡን ይለውጠዋል?

መልስ፤


ሚልክያስ 3፡ 6 — ‹‹እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም። ››በተመሳሳይ ያዕቆብ 1:17፡- ‹‹በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።›› ዘኍልቍ 23:19 ግልጽ ነው፡- ‹‹ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?›› በአነዚህ ጥቅሶች መሰረት እግዚአብሔር አይለወጥም፤ እርሱ የማይለወጥ ነው፡፡እርሱ ጥበበኛ ነው፡፡ ስለዚህ ስህተቱን መቀበል ወደ ኋላ መፈተሽ እና አዲስ አካሄድ ለመሞከር ሲል "አእምሮውን መለወጥ" አይችልም፡፡

ታዲያ አምላክ ሐሳቡን እንደሚለውጥ የሚናገሩ የሚመስሉ ጥቅሶችን እንዴት እንገልጻለን? ዘፍጥረት 6፡6 የመሳሰሉትን ጥቅሶች ‹‹እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ።›› ይላል፡፡ በተጨማሪም ዘፀአት 32፡14 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ።›› እነዚህ ጥቅሶች ስለ ጌታ ‹‹በኃዘን ወደኋላ እንደተመለሰ›› ወይም ‹‹እንደተጸጸተ›› ከእግዚአብሔር የአለመለወጥ ባህሪ ጋር የሚጋጭ የሚመስል ነገር ይናገራሉ፡፡

ትዕዛዙን እግዚአብሔር እንደቀየረ ላማሳየት ጥቅም ላይ የሚውለው የዮናስን ታሪክ ነው፡፡ በነቢዩ በኩል እግዚአብሔር ነነዌን በአርባ ቀናት ውስጥ ያጠፋታል ብሎ ነግሮታል (ዮናስ 3፡4)፡፡ ነገር ግን የነነዌ ህዝብ ለኃጢአታቸው ንስሐ ገቡ (ቁጥር 5-9)፡፡ ‹‹እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።›› (ቁጥር 10)፡፡

እግዚአብሔር ሐሳቡን የለወጠባቸው ተደርገው የሚወሰዱ ሁለት ዋና ዋና ምንባቦች አሉ፡፡ በመጀመሪያ "እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ እንዳዘነ" የሚሉ መግለጫዎችን መጥቀስ እንችላለን ማለት ነው (ዘፍጥረት 6 ፡6) እነዚህ የአንተሮፖሞርፊዝም (አንትሮፖሞርፊያኒዝ) ምሳሌዎች ናቸው፡፡ አንተሮፖሞርፊዝም ውስን የሆነው ሰው ወስን የሌለውን እግዚአብሔርን ለመግለጽ የተጠቀመበት የንግግር ዘይቤ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ ከሰው አመለካከት አንፃር ለመረዳት የሚረዳን መንገድ ነው፡፡ በዘፍጥረት ምዕራፍ 6 ቁጥር 6 ውስጥ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ኃጢአት ማዘኑን ተረድተናል፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ለመፍጠር ያደረገውን ውሳኔ አልቀለበሰውም፡፡ ዛሬ በሕይወት እንዳለን መናገራችን ስለ ፍጥረታት እግዚአብሔር "ሐሳቡን ያለወጠ" መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው፡፡

ሁለተኛ በእኛ ሁኔታዊ መግለጫዎች እና በእግዚአብሔር ባልተገደበ ቅድመ ሁኔታ በሌለው ውሳኔዎች መካከል ልዩነት ማድረግ አለብን፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሔር "ነነዌን በአርባ ቀናት ውስጥ አጠፋለሁ" በሚለው ላይ በአሶሪያን ምላሽ ላይ በተወሰነ ሁኔታ ውስጥ እየተናገረ ነበር፡፡ ይህን እናውቃለን ምክንያቱም አሶራውያን ንስሃ በመግባታቸው እግዚአብሔር ፍርድን አልፈጸመም፡፡እግዚአብሔር ሐሳቡን አልለወጠም ይልቁንም መልእክቱ ወደ ነነዌ ለንስሃ የሚቀሰቅስ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ነበር እና ማስጠንቀቂያው ስኬታማ ነበር፡፡

አምላክ ለዳዊት የገባው ቃል ኪዳን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የተገባ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ምሳሌ ነው፡፡ ‹‹ቤትህና መንግሥትህም በፊቴ ለዘላለም ይጠነክራል፥ ዙፋንህም ለዘላለም ይጸናል።›› 2 ኛ ሳሙኤል 7፡16)፡፡ በዚህ መግለጫ ውስጥ የተገለፀ መመዘኛ ወይም የተጠያቂነት ደረጃ የለም፡፡ ምንም እንኳ ዳዊት ምንም አደረገ ወይም አላደረገ የእግዚአብሔር ቃል ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

እግዚአብሔር ስለ አንዳንድ መግለጫዎች ተፈጥሮአዊ ምንነት ይነግረናል እና በምርጫዎቻችንም መሠረት ያደርጋል "ስለ ሕዝብ ስለ መንግሥትም እነቅል አፈርስም አጠፋም ዘንድ በተናገርሁ ጊዜ፥ይህ ስለ እርሱ የተናገርሁበት ሕዝብ ከክፋቱ ቢመለስ፥ እኔ አደርግበት ዘንድ ካሰብሁት ክፉ ነገር እጸጸታለሁ።ስለ ሕዝቡም ስለ መንግሥትም እሠራውና እተክለው ዘንድ በተናገርሁ ጊዜ፥በፊቴ ክፉን ነገር ቢያደርግ ቃሌንም ባይሰማ፥ እኔ አደርግለት ዘንድ ስለ ተናገርሁት መልካም ነገር እጸጸታለሁ።አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፥ አሳብንም አስብባችኋለሁ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው።"(ኤርምያስ 18 7-11)፡፡ ቅድመ ሁኔታ ያለውን ቃል ልብ ይበሉ፡ ‹‹ ህዝቡ ሳስጠነቅቀው ከክፋቱ ቢመለስ ልክ በትንቢተ ዮናሰ በአሶራዊያን እንደሆነው ዮና 3 እኔ እጸጸታለሁ›› በተቃራኒው እግዚአብሔር አንድ ሕዝብ እንደሚባረካቸው ይናገር ይሆናል " ግን በእኔ ፊት [በሚክያስ 1 ውስጥ እንደነበረው እስራኤል] ክፉ ነገር ቢያደርግ .. . እኔ ካሰብኩትን መልካም ነገር እንደገና አጤነዋለሁ"፡፡

ዋናው ነጥብ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ የማይለዋወጥ ነው፡፡ በቅዱስነቱ እግዚአብሔር በነነዌ ላይ ሊፈርድ ነበር፤ ሆኖም ነነዌ ንስሐ በመግባት መንገዶቹን ቀየረች፡፡ በውጤቱም እግዚአብሔር በቅዱስነቱ በነነዌ ላይ ምህረትን አደረገላቸው፡፡ ይህ "የአመለካከት ለውጥ" ከባህሪው ጋር ሙሉ በሙሉ አስተማማኝነት ነው፡፡ ቅድስናው በአንዲት ቃል እንኳ አላጠፋም፡፡

እግዚአብሔር በምርጫዎቻችን ላይ እግዚአብሔር በእኛ ላይ የሚያደርገው የእርሱን ባሕርይ የሚለውጡበት ሁኔታ ከእርሱ ባሕርይ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ በመሠረቱ እግዚአብሔር የማይለወጥ በመሆኑ ጻድቁን ከሌሎች ጻድቅ ካልሆነው በተለየ እንዲመለከተው ያደርገዋል፡፡ አንድ ሰው በመለስ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይቅር ይላል፤ አንድ ሰው ለመመለስ እንቢ ቢል እግዚአብሔር ፈጽሞ ይፈርዳል፡፡ እግዚአብሔር በማንነቱ አይለወጥም፤ በእቅዱ በባሕሪ፡፡ አንድ ቀን ባደረገው ነገር ተደስቶ በሌላ ቀን አይቆጣም፡፡ ይህ ደግሞ ተለዋዋጭ እና የማይታመን ያደርገዋል፡፡ እግዚአብሔር ለነነዌ ሲናገር ‹‹እፈርድባችኋለው ›› ብሎ ከዛ (ከተመለሱ በኋላ) ፍርዱ ይተዋል ይህም የተቀየረ ሊመስል ይችላል፡፡ በትክክለኛው እግዚአብሔር እንደ ሁልጊዜው በባሕሪው እውነተኛ ሆኖ ነው ያለው፡፡ እርሱ የሚመለሰውን ምህረት ማድረግ እና ይቅር ማለትን ይወዳል፡፡ ‹‹እግዚአብሔርስ ሞገሱን ረሳን? በቍጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን?›› (መዝ 77፡9)፡፡

በአንድ ወቅትሁላችንም በኃጢያታችነ ምክንያተ የእግዚአብሔረ ጠላቶች ነበርን (ሮሜ 8፡7)፡፡ እግዚአብሔር ስለ ኃጢያት ዋጋ እንድንመለስ አስጠነቀቀን (ሮሜ 6፡23)፡፡ ስንመለስና ክርስቶስን ስለ ድኅነታችን ስናምን ‹‹እግዚአብሔር ሃሳቡን ለወጠ›› እኛ አሁን ጠላቶች ሳንሆን የእርሱ የፍቅር ልጆች ነን (ዮሐ 1፡12)፡፡ በኃጠያታችነ ቀጥለን በሆን እና እግዚአብሔር ባይቀጣን እና ከኃጢያታችን ተመለሰንም ቢቀጣን ከማንነቱ ጋር ይጋጭ ነበር፡፡ ያ ማለት የእኛ የልብ ለውጥ እግዚአብሔርን ለውጦታል ማለትነው፡፡አይደለም መዳናችን በእግዚአብሔር አለመለወጥ ሃሳብ ተይዞ በሆን ከኢየሱስ ክርስቶስ አንጻር አያድነንም ነበር ምክንያቱም እርሱ ከባሕሪው በመቃረን አይሰራም፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር ሐሳቡን ይለውጠዋል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries