settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር ዛሬም ህልምን ለሰዎች ይሰጣል?

መልስ፤


እግዚአብሔር ዛሬም ህልምን ለሰዎች ይሰጣል? አዎን! እግዚአብሔር ዛሬም ራዕይን ለሰዎች ይሰጣል? ሊሆን ይችላል:: ራዕይን ተራ ክስተት ነው ብለን ልንጠብቅ እንችላለን? አይደለም በእግዚአብሔር ቃል እንደተጻፈው እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ በራዕይ ለህዝቡ ተናግሮአል፡፡ ለምሳሌ የሴፍ የያዕቆብ ልጅ፤ የሴፍ የማሪያም እጮኛ፤ ሰለሞን፤ ኢሳያስ፤ እዝቄል፤ ዳንኤል፤ ጴጥሮስና ጳውሎስ፡፡ ነብዩ ኢዩኤል ስለ ራዕይ መሰጠት ተንብዮ ነበር ይህን ጴጥሮስ በሐዋሪያት ሥራ ምዕራፍ 2 መስክሮአል፡፡ በህልምና በራዕይ መካከል ያለውን ልዩነት ማስተዋል አስፈላጊ ነው፡፡ ራዕይ አንድ ሰው ነቅቶ ሳለ የሚሰጥ ሲሆን ህልም ግን ያ ሰው ተኝቶ ሳለ የሚሰጥ ነው፡፡

በአለም ላይ በቡዙ ቦታዎች እግዚአብሔር በስፋት ራዕይን እና ህልምን ሳይጠቀም አይቀርም፡፡ በጣም ትንሽ ወይንም ምንም የወንጌል መልዕክት በሌለባቸው ስፍራዎች፤ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ በማያገኙባቸው ቦታዎች፤ እግዚአብሔር መልእክቱን በቀጥታ በህልምና በራዕይ ይናገራል፡፡ በአጠቃላይ ሁልጊዜም እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናያቸው ምሳሌዎች እግዚአብሔር ራዕይን የእርሱን እውነት ለማስተላለፍ መቀደመው የክርስትና ዘመን ሁልጊዜም ተጠቀሞበታል፡፡ እግዚአብሔር መለዕክቱን ለአንድ ሰው ማስተላለፍ ከፈለገ ያገኘውን ሁሉ ይጠቀማል፤ መልዕክተኛ ሚሽነሪ፤ መልአክ፤ ባለራዕይ ወይም ህልመኛ፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር የወንጌል መልዕክት ተዘጋጅቶ በሚቀርብበት ባለበትም ቦታ ራዕይን ሊሰጥ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ለሚሰራው ነገር ምንም አይነት ገደብ የለም፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ራዕይና ራዕይን ወደ መተርጎም ስንመጣ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ በአምሮአች ማስቀመጥ ያለብን መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ አልቆአል፤ ልናውቀው የሚገባንን ሁሉ ይነግረናል፡፡ ቁልፉ እውነታ እግዚአብሔረ ከሆነ ህልምን የሰጠው እግዚአብሔር እርሱ ራሱ በቃሉ ካስቀመጠው ጋር ይስማማል፡፡ ራዕይ ፈጽሞ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስተካከል ወይንም የሚበልጥ ስፍራ ሊሰጠው አይችልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በክርስቲያናዊ ልምምድ ወስጥ የሚጨረሻው ባለስልጣን ነው፡፡ አማኞች ከሆንን ራዕይ ሊኖረን ተቀብለንም ከሆነ መጸለይ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማማ መሆን አለበት፡፡ በጸሎት እግዚአብሔር ለራዕዩ እንድንሰጥ የሚፍልገውን ምላሽ ማወቅ አለብን (ያዕ 1፡5)፡፡ እግዚአብሔር ህልምን ሰጥቶ የህልሙን ፍቺ አይደብቅም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ማንም ባለራዕ የራዕዩን ፍቺ ቢጠይቅ እግዚአብሔር በእርግጠኝነት የገልጽለታል (ዳን1፡15-18)፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር ዛሬም ህልምን ለሰዎች ይሰጣል? ክርስቲያኖች ራዕይ ክርስቲያናዊ ልምምድ ነው ብለው ማመን አለባቸው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries