settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ክርስቲያን የጋኔን ማደሪያ ሊሆን ይችላል? ክርስቲያን በአጋንንት ሊያዝ ይችላል?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ በትክክል አያስቀምጥም፣ ክርስቲያን በአጋንንት ስለመያዙ፣ ተዛማጅ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ሰፋ ባለ መልኩ በግልጽ አስቀምጠውታል፣ ክርስቲያን የአጋንንት ማደሪያ እንደማይሆን። ሰፋ ያለ ልዩነት አለ፣ የጋኔን ማደሪያ በመሆን መካከልና በጋኔን መጨቆን ወይም ተጽዕኖ ሥር መሆን። በጋኔን መያዝ፣ ጋኔን ቀጥተኛ/ፍጹም ቁጥጥር ሲኖረው ነው፣ የግለሰቡን ሐሳብ እና/ወይም ድርጊትን (ማቴዎስ 17:14-18፤ ሉቃስ 4:33-35፤ 8:27-33)። የጋኔን ጭቆና ወይም ተጽዕኖ የጋኔን ወይም የአጋንንትን ጥቃት ያካትታል፣ በመንፈሳዊነት ላይ እና/ወይም እሱን/እሷን የኃጢአት ባሕርይ እንዲኖራቸው ያበረታታል። በሁሉም የአዲስ ኪዳን ምንባቦች፣ መንፈሳዊ ውጊያን በተመለከተ፣ ጋኔን ከአማኝ የወጣበት አንድም ትእዛዝ አለመኖሩን ተገንዘቡ (ኤፌሶን 6፡10-18)። አማኞች ዲያብሎስን እንዲቃወሙ ተነግሯቸዋል (ያዕቆብ 4:7፤ 1 ጴጥሮስ 5:8-9)፣ እንዲያወጡት ሳይሆን።

ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናቸው (ሮሜ 8:9-11፤ 1 ቆሮንቶስ 3:16፤ 6:19)። በርግጥ መንፈስ ቅዱስ አይፈቅድለትም፣ የእሱ ማደሪያ የሆነውን ሰው ጋኔን እንዲያድርበት። እሱ የማይታሰብ ነው፣ እግዚአብሔር ከልጆቹ አንዱን፣ እሱም በክርስቶስ ደም የገዛውንና (1 ጴጥሮስ 1፡18-19) አዲስ ፍጥረት ያደረገውን (2 ቆሮንቶስ 5፡17)፣ በጋኔን እንዲያዝና ቁጥጥር ሥር እንዲሆን። ርግጥ፣ እንደ አማኞች ከሰይጣን እና ከአጋንንቱ ጋር ጦርነት ገጥመናል፣ ነገር ግን ከገዛ ራሳችን ጋር አይደለም። ሐዋርያው ጳውሎስ ያውጃል፣ “እናንተ፣ ውድ ልጆች፣ ከእግዚአብሔር ስለሆናችሁ እነሱን አሸንፋችኋል፣ በእናንተ ያለው በዓለም ካለው ስለሚበልጥ” (1 ዮሐንስ 4፡4)። በእኛ ውስጥ ያለው ማን ነው? መንፈስ ቅዱስ። በዓለም ያለው ማን ነው? ሰይጣንና አጋንንቱ። ስለዚህ፣ አማኝ የአጋንንትን ዓለም ድል አድርጓል፣ እናም አማኝ በጋኔን የመያዙ ጉዳይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።

ጠንከር ባለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ክርስቲያን የጋኔን ማደሪያ ሊሆን አይችልም በሚለው አተያይ፣ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን “አጋንንታዊነት” የሚል ቃል ይጠቀማሉ፣ ክርስቲያንን የተቆጣጠረውን ጋኔን ለመጥቀስ። አንዳንዶች ይከራከራሉ፣ ክርስቲያን ፈጽሞ የአጋንንት ማደሪያ እንደማይሆን፣ ክርስቲያን አጋንንታዊ ሊሆን ይችላል በሚል። በአጠቃላይ፣ የአጋንንታዊነት ገለጻ የአጋንንት ማደሪያ መሆን ከሚለው ጋር ምንታዌነት አለው። ስለዚህ፣ ተመሳሳይ ውጤት ያለው ጉዳይ ነው። ቃሉን መቀየር ሐቁን ሊቀይረው አይችልም፣ ይኸውም፣ ጋኔን በክርስቲያን ላይ ሊያድር ወይም ሙሉ ቁጥጥር ሊያደርግ አይችልም የሚለውን። አጋንንታዊ ተጽዕኖ እና ጭቆና በክርስቲያን ላይ የሚደርሱ እውነታዎች ለመሆናቸው ጥርጥር የለም፣ ነገር ግን እንዲያው፣ ክርስቲያን በጋኔን ይያዛል ወይም አጋንንታዊ ይሆናል ማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።

አብዛኛው የአጋንንታዊነት ጽንሰ-ሐሳብ አስተሳሰብ ግለሰባዊ ልምድ ነው፣ አንዱን “ሙሉ ለሙሉ” ክርስቲያን የነበረና በጋኔንን ቁጥጥር ሥር ለመሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠን በማየት ነው። በወሳኝ መልኩ ጠቃሚ የሚሆነው፣ ግለሰባዊ ልምዶቻችን ቃሉን በመተርጎም ላይ ተጽዕኖ እንዳያደርጉብን ነው። ይልቁን የግል ልምምዶቻችንን በቃሉ እውነት በኩል የግድ ማጣራት ይኖርብናል (2 ጢሞቴዎስ 3፡16-17)። ክርስቲያን ይሆናል ያልነውን አንዱን የአጋንንታዊ ባሕርይ ሲያንጸባርቅ ብናይ የእሱን/እሷን እምነት እውነተኝነት ጥያቄ ሊፈጥርብን ይችላል። እሱ አስተሳሰባችንን ሊያስቀይር አይገባም፣ ክርስቲያን የአጋንንት ማደሪያ/አጋንንታዊ ይሆናል በሚል። ምናልባት ግለሰቡ በርግጥ ክርስቲያን ሊሆን ይችላል፣ በከፋ መልኩ ጋኔን ያደረበት እና/ወይም በከፋ ሥነ-ልቦናዊ ችግሮች የሚሣቀይ። ግን በድጋሚ፣ ልምዳችን መግጠም ያለበት ከቃሉ ጋር በመፈተን ነው እንጂ በተገላቢጦሽ መሆን አይኖርበትም።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ክርስቲያን የጋኔን ማደሪያ ሊሆን ይችላል? ክርስቲያን በአጋንንት ሊያዝ ይችላል?
© Copyright Got Questions Ministries