settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያን ስለሆን አባቶች ምን ይላል?

መልስ፤


በመጽሐፍ ቅዱስ ትልቁ ቃል ይህ ነው ‹‹አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ።›› ዘዳ 6፡5 ወደ ቁጥር 2 ተመልሰን ስናነብ አንተ ‹‹ልጅህም የልጅ ልጅህም በዕድሜአችሁ ሁሉ ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉአት ዘንድ፥ አምላክህን እግዚአብሔርን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዛት ትእዛዝና ሥርዓት ፍርድም ይህች ናት።›› ከ6፡5 ቀጥሎ ‹‹እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ።ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው።›› ቁ 6-7

በእስራኤል ታሪክ እንደምንረዳው አባቶች ልጆቻቸውን በመንፈሳዊ ህይወታቸው ዕድገት ለደህንነታቸው እና እንደ እግዚአብሔር ቃል በትክክል ለመምራት ትጉ መሆን አለበቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የሚታዘዝ አባት የሚያደርገው ይህንን ነው፡፡ ይህ ሃሳብ ወደዚህ ክፍል ይወስደናል ምሳ 22:6, ‹‹ ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።›› ‹‹መምራት›› የሚለው ቃል አንድ እናት እና አባት ለልጃቸው ማድረግ የሚገባቸወን የመጀመሪያ ነገር ያመለክተናል ያም የልጁ የልጅነት ጊዜ ትምህርት፡፡ መምራት ልጆች አንዲኖሩበት የታቀደወን ጸባይ ግልጽ ለማድረግ የታለመ ነው፡፡ ለጅን በልጅነቱ በትክክለኛው መንገድ መምራት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ኤፌ 6፡4 በአዎንታዊና በአሉታዊ መልኩ አጭር መግለጫ ተቀምጦአል፡፡ ‹፣ እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው።›› ይህ ክፍል በአሉታዊ መልኩ የሚያመለክተው አባት ስልጣንን በማይገባ መልኩ ተጠቅሞ ልጆቹን በኃይል ፍትህ በጎደለው መልኩ በአድሎ በአሉታዊ መልኩ እንዲነሳሱ እንዲማረሩ መድረግ የለበትም፡፡ በመጠፎ በማይመች አሳማኝ ባልሆነ መልኩ ከልጆች ጋር የሚደረግ ግንኙነት ክፉ ነገር በልባቸው እንዲያድግ ብቻ ነው የሚያደርገው፡፡ “provoke” ‹‹አታስቆጦአቸው›› የሚለው ቃል ‹‹ እንዲመረሩ በጣም ማበሳጨት በተሳሳተ መንገድ መነካካት ወይም ማነሳሳት›› ነው፡፡ ይህ በተሳሳተ መንፈስና መንገድ በኃይል አሳማኝ ባልሆነ ጥብቅና ኃይለኛ የማይመች ከባድ ትዕዛዝ አላስፈላጊ መመሪያ በራስ ወዳድነት በመነሳሳት አንባገነን በሆነ ስላጣን የሚደረግ ነው፡፡ አንደዚህ አይነት ክፉ መነሳሳት የተቃውሞ ምላሽ የሚፈጥር የልጅነት ፍቅርን የሚገድል ለተቀደሰ ህይወት የሚኖራቸውን ፍላጎት እንዲቀንስ እና ወላጆቻቸውን ማስደሰት እችላለው ብለው እንዳይሰማቸው የሚያደርግ ነው፡፡ ጠቢብ የሆኑ ቤተሰቦች መታዘዝ ተፈላጊና ሊሳካ የሚችል በፍቅር እና በጨዋነት የሚደረግ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡

የኤፌ 6፡4 አዎንታዊ መልኩ አንድ አቅጣጫን ያመለክታል የእግዚአአብሔር በሆነ ምክርና ትግሳጽ አስተምሩአቸው አሳድጓአቸው፡፡ ይህም የማስተማር በመቅጣት የማሳደግ ህይወት ሂደት ነው፡፡ “ተግሳጽ” የሚለው ቃል ልጆች የሚሰሩትን ስህተት እነርሱን በሚገነባ መልኩ የማረም ሃላፊነት የሚመለከት ሃሳብ የያዘ ነው፡፡

ክርስቲያን አባት በእግዚአብሔር እጅ ያለ መሳሪያ ነው፡፡ የሚደረገወ የትኛውም ተግሳጽ ሆነ ምክር እግዚአበሔር እንዳዘዘው እንደሰጠው መመሪያ መሆን አለበት ይህ ሲሆን በልጆቹ ህሊና ውስጥ ቀድሞ በቀጥታ የሚመጣው የእግዚአብሔር ሥልጣን ይሆናል፡፡ ስጋዊ አባት እውነተኛውንና መደረግ የሚኖርባቸውን ነገሮች ለመወሰን የመጨረሻው ባለስልጣን አድርጎ ራሱን ማቅረብ አይኖርበትም፡፡ እግዘአበሔርን ብቻ አስተማሪ እና በሁልም ሥልጣን ስር የሚደረግ ስራ ሁሉ ላይ የበላይ መሪ እንደሆነ ማሳወቅ አንድ የተሳካ ማስተማር ሂደት የሚያሳካው ነው፡፡

ማርቲን ሉተር እንደዚህ በሎአል፡- ‹‹ የአፕል ፍሬውን ለጁ መልካም ሲያደርግ ለመስጠት እንድትችል በመንዱ አጠገብ አድርገው›› ብሎአል፡፡ ቅጣት የስነስርዓት እርምጃ ሲደረግ ከአይናችን ጥበቃ ሳናርቅ ሁልጊዜ በማለማመድ በብዙ ጸሎት መሆን አለበት፡፡ አካላዊ ቅጣት የስነስርዓት እርምጃ ቅጣት እና በእግዚአብሔር ቃል መሰረት መምከር ተግሳጽ እና ማበረታታትን ሆለቱንም መስጠት የተግሳጽ ማዕከላዊ ነገር ነው፡፡ በክርስቲያን ልምምድ ትምህርት ቤት ውስጥ ከእግዚአብሔር የሚወጣ ተግሳጽ በወላጆች የሚደረግ በመጀመሪያ በአባት አንዱሁም በእርሱ አመራር በእናት የሚከናወን ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ቅጣት አንድ ልጅ እግዚአብሔርን በመፍራት እንዲያድግ ቤተሰባዊ ስልጣን እንዲያከብር የክርስትናን ምንነት ደረጃ እንዲያውቅ ራስን የመግዛት ባህሪን እንዲኖረው ላማስቻል እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

‹‹የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። ›› (2 ጢሞ 3:16-17). አንድ አባት ለልጁ ያለው ቀዳሚ ኃላፊነት የእግዚአብሔርነ ቃል መግለጽ ነው፡፡ የቃሉን እውነት ለማስተማር የሚጠቀምበት መንገድ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ አባት በታማኝነት መልካም ምሳሌ በሆነ መጠን ልጆች ስለእግዚአብሔር በተማሩት በምድር ህይወታቸው ኑሮ ሆሉ ምንም ቢሰሩ የትም ቢሄዱ መልካም ትክክለኛ አቋም እንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል፡፡

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያን ስለሆን አባቶች ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries