settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ትክክለኛው መንገድ ምንድነው?

መልስ፤


የቅዱስ ቃሉን ትርጉም መወሰን አማኝ በዚህ ሕይወት ካሉት እጅግ ጠቃሚ ተግባራት መካከል አንደኛው ነው። እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን የግድ እንድናነብ አይነግረንም። እኛ የግድ ማጥናትና ባግባቡ መያዝ አለብን (2 ጢሞቴዎስ 2፡15)። ቅዱሳን መጻሕፍትን ማጥናት ከባድ ሥራ ነው። ቅዱስ ቃሉን በግልብ ወይም አጭር ቅኝት መመልከት አንዳንዴ በጣም የተሳሳተ ድምዳሜ ያመጣል። ስለዚህ፣ የቅዱስ ቃሉን ትክክለኛ ፍቺ ለመወሰን በርካታ መርሖዎችን መረዳት ወሳኝ ነው።

አንደኛ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ የግድ መጸለይና መንፈስ ቅዱስን መጠየቅ አለበት፣ መረዳትን እንዲሰጠው፣ ይህ አንደኛው ተግባሩ ስለሆነ። “ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል” (ዮሐንስ 16፡13)። መንፈስ ቅዱስ፣ ሐዋርያት አዲስ ኪዳንን ሲጽፉ እንደመራቸው ሁሉ፣ ቅዱስ ቃሉን አንድንረዳ ይመራናል። አስታውሱ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር መጽሐፍ ነው፣ እናም ምን ማለት አንደሆነ ልንጠይቀው ያስፈልጋል። ክርስቲያን ከሆናችሁ፣ የቅዱስ ቃሉ ደራሲ —መንፈስ ቅዱስ—በውስጣችሁ ያድራል፣ እናም እሱ የጻፈውን እንድትረዱለት ይሻል።

ሁለተኛ፣ የቅዱስ ቃሉን ቁጥሮች የከበቡትን መዘን ልናወጣና የቁጥሩን ፍች ከዐውደ-ጽሑፉ ውጭ ለመወሰን መሞከር አይገባንም። በዙሪያው ያሉትን ቁጥሮችና ምዕራፎች ዘወትር ማንበብ አለብን ዐውደ-ጽሑፉን ለመገንዘብ። ሁሉም ቅዱስ ቃል ከእግዚአብሔር ሲመጣ (2 ጢሞቴዎስ 3:16፤ 2 ጴጥሮስ 1:21)፣ እግዚአብሔር ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እሱን ይጽፉት ዘንድ። እነዚህ ሰዎች በአእምሯቸው ጭብጥ አለ፣ ለመጻፍም ዓላማ አላቸው፣ እንዲሁም የተወሰነ ጉዳይ የሚያስተላልፉት። የምናጠናውን የመጽሐፍ ቅዱስን መጽሐፍ ዳራ ማንበብ ይኖርብናል፣ ማን እንደ ጻፈው፣ ለማን እንደ ተጻፈ፣ መቼ እንደ ተጻፈ፣ እና ለምን እንደተጻፈ ለመረዳት። ደግሞም፣ ጽሑፉ ለራሱ እንዲናገር በመፍቀድ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። አንዳንዴ ሰዎች የገዛ ራሳቸውን ፍች ከቃሉ ጋር ያያይዛሉ፣ ራሳቸው የሚፈልጉትን ትርጓሜ ለማግኘት።

ሦስተኛ፣ እኛ ባጠቃላይ ነጻ ለመሆን መሞከር አይኖርብንም፣ በእኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ። ከሌሎች፣ ቅዱስ ቃሉን ለረዥም ጊዜ ካጠኑት ሰዎች በኩል መረዳትን ልናገኝ አንችልም ብሎ ማሰብ ትዕቢተኝነት ነው። አንዳንድ ሰዎች በስሕተት መጽሐፍ ቅዱስን የሚቀርቡት በመንፈስ ቅዱስ ላይ ብቻ ነው የምንጠጋው በሚል ሐሳብ ሁሉንም የተሸሸጉ የቅዱስ ቃሉን እውነቶች የደረሱበት ይመስላቸዋል። ክርስቶስ፣ መንፈስ ቅዱስን በመስጠት፣ ለሰዎች መንፈሳዊ ስጦታ ይሰጣቸዋል፣ ለክርስቶስ አካል። ከእነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች አንደኛው ማስተማር ነው (ኤፌሶን 4:11-12፤ 1 ቆሮንቶስ 12:28)። እነዚህ መምህራን የተሰጡን በጌታ ነው፣ ቅዱስ ቃሉን በትክክል እንድንገነዘብና እንድንታዘዝ እንዲረዱን። ዘወትር ከሌሎች አማኞች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ብልህነት ነው፣ የእግዚአብሔርን ቃል እውነት ለመረዳትና ለመተግበር እርስ በርስ ለመደጋገፍ።

ስለዚህ፣ በማጠቃለያ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ተገቢ የሆነው መንገድ ምንድነው? አንደኛ፣ በጸሎትና በትሕትና፣ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ልንታመን ይገባል፣ መረዳትን አንዲሰጠን። ሁለተኛ፣ ዘወትር ቅዱስ ቃሉን ማጥናት ያለብን በዐውደ-ጽሑፉ አኳያ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እንደሚገልጽ በመገንዘብ። ሦስተኛ፣ የሌሎችን ክርስቲያኖች ጥረት ልናከብር ይገባል፣ ያለፉትንም ሆነ ያሁኖቹን፣ እነሱም የመጽሐፍ ቅዱስን ተገቢ የሆነ የአጠናን ዘዴ ያመላከቱትን። አስታውሱ፣ እግዚአብሔር የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ ነው፣ እናም እሱ አንድንገነዘበው ይፈልጋል።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ትክክለኛው መንገድ ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries