settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የመጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳን ጽሑፎች እንዴትና መቼ አንድ ላይ ተደረጉ?

መልስ፤


“ቅዱሳን ጽሑፎች” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው በመለኮታዊ ተመስጦ የሆኑትን መጻሕፍት ለመግለጽ ሲሆን፣ እና ስለዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቅዱሳን ጽሑፎችን ለመወሰን ያለው ችግር የሚሆነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚካተቱትን መጻሕፍት ዝርዝር ስለማይሰጠን ነው። ቅዱሳን ጽሑፎችን የመወሰን ተግባር ሂደት ሲሆን በቅድሚያም የተከናወነው በአይሁድ መምህራንና ሊቃውንት ነበር፣ ቆይቶም በጥንት ክርስቲያኖች። እጅግ በተሻለ፣ የትኞቹ መጻሕፍት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ቅዱሳን መጻሕፍት እንዲካተቱ የወሰነው እግዚአብሔር ነበር። የቅዱስ ቃሉ መጽሐፍ በቅዱሳን መጻሕፍት የሚካተቱት እግዚአብሔር ጽሑፉን ተመስጧዊ ካደረገው ቅጽበት አንሥቶ ነው። እሱ የእግዚአብሔር የማሳመን ጉዳይ ነው፣ የሰው ተከታዮቹን፣ የትኛው መጽሐፍ በቅዱስ ጽሑፉ እንደሚካተት።

ከአዲስ ኪዳን ጋር ሲነጻጸር፣ ጥቂት ውዝግብ ነበር፣ የብሉይ ኪዳንን ቅዱሳን ጽሑፎችን በተመለከተ። የዕብራውያን አማኞች ለእግዚአብሔር መልእክተኞች እውቅና ነበራቸው፣ እናም የእነሱን ጽሑፎችም የእግዚአብሔር ተመስጦአዊ እንደሆኑ ተቀብለው ነበር። የማይካድ ጥቂት ክርክር የብሉይ ኪዳንን ቅዱሳን ጽሑፎች በተመለከተ እንደነበር ይታወቃል፣ በ250 ዓ.ም ባመዛኙ ዓለም-አቀፍ ስምምነት ነበር፣ የዕብራውያን ቅዱስ ጽሑፎችን በተመለከተ። የቀረው ብቸኛ ጉዳይ የተጓዳኙ ሃይማኖታዊ መጻሕፍት ነበር፣ እስከ አሁን ድረስ በዘለቀ ክርክርና ውይይት። እጅግ አብዛኞቹ የዕብራውያን ሊቃውንት ተጓዳኞቹን የሃይማኖት መጻሕፍት የሚመለከቷቸው እንደ መልካም ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ሰነዶች ነው፣ ነገር ግን እንደ ዕብራውያን ቅዱሳን መጻሕፍት ተመሳሳይ ደረጃ አይሰጧቸውም።

ስለ አዲስ ኪዳን፣ እውቅና የመስጠትና የማሰባሰብ ሂደት የተጀመረው በክርስቲያን ቤተ-ክርስቲያን በአንደኛው ክፍለ-ዘመን ነው። እጅግ ቀደም ብሎ፣ አንዳንድ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት እውቅና አግኝተው ነበር። ጳውሎስ የሉቃስ ጽሑፎች እንደ ብሉይ ኪዳን ሥልጣናዊ እንደነበሩ እውቅና ሰጥቷል (1 ጢሞቴዎስ 5፡18፤ ዘዳግም 25፡4 ተመልከት፣ እንዲሁም ሉቃስ 10፡7)። ጴጥሮስ የጳውሎስ ጽሑፎችን እንደ ቅዱስ ቃሉ እውቅና ሰጥቷል (2 ጴጥሮስ 3:15-16)። አንዳንዶቹ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በቤተ-ክርስቲያናት መሐል ይዘዋወሩ ነበር (ቆላስያስ 4:16፤ 1 ተሰሎንቄ 5:27)። የሮሜው ክሌመንት ቢያንስ ስምንት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ጠቅሷል (95 ዓ.ም)። የአንቲሆቹ ኢግናተስ ለ7 ያህል መጻሕፍት እውቅና ሰጥቷል (115 ዓ.ም)። ፖሊካርፕ፣ የሐዋርያው ዮሐንስ ደቀ-መዝሙር፣ ለ15 መጻሕፍት እውቅና ሰጥቷል (108 ዓ.ም)። ኋላም ኢሪኔዩስ 21 መጻሕፍት ጠቅሷል (185 ዓ.ም)። ሂፖሊተስ ለ22 መጻሕፍት እውቅና ሰጥቷል (170-235 ዓ.ም)። እጅግ ውዝግብ ያስነሡት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ዕብራውያን፣ ያዕቆብ፣ 2 ጴጥሮስ፣ 2 ዮሐንስ፣ እና 3 ዮሐንስ ናቸው።

የመጀመሪያው “ቅዱሳን ጽሑፍ” የሙራቶሪያን ቅዱሳን ጽሑፎች ነበር፣ እሱም በ170 ዓ.ም የተጠናቀረ። የሙራቶሪያን ቅዱሳን ጽሑፍ ሁሉንም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ያካተተ ነበር፣ ከዕብራውያን፣ ከያዕቆብ፣ እና 3 ዮሐንስ በቀር። በ363 ዓ.ም የሎዶቅያ ጉባኤ ብሉይ ኪዳን ብቻ (ተጓዳኝ መጻሕፍትን ጨምሮ) እንዲሁም የአዲስ ኪዳን 27 መጻሕፍት በአብያተ- ክርስቲያናት እንዲነበቡ ወሰነ። የሂጶ ጉባኤ (393 ዓ.ም) እና የካርቴጅ ጉባኤ (397 ዓ.ም) ደግሞ 27 የሚሆኑ መጻሕፍት ሥልጣናዊ እንደሆኑ አጸኑ።

ጉባኤዎቹ ተመሳሳይ የሆነ ነገር ተከትለዋል፣ በቀጣዮቹ መርሖዎች፣ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ በርግጥ በመንፈስ ቅዱስ ተመስጧዊ ለመሆኑ፡ 1) ደራሲው ሐዋርያ ነበርን ወይስ ከሐዋርያ ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበረውን? 2) መጽሐፉ በክርስቶስ አካል በሙላት ተቀባይነት አግኝቷልን? 3) መጽሐፉ የመሠረተ-እምነት (ዶክትሪን) እና ቀጥተኛ ትምህርት በጽናት ይዟልን? 4) መጽሐፉ የላቀ የሞራልና መንፈሳዊ እሴት ለመያዙ ማስረጃ አለውን፣ ያም የመንፈስ ቅዱስ ሥራ መሆኑን የሚያንጸባርቅ? እንደገናም፣ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱሳን ጽሑፎቹን አለመወሰኗን ማስታወስ ዋነኛ ነገር ነው። የትኛውም የቀደምት ቤተ-ክርስቲያን ጉባኤ በቅዱሳን ጽሑፎቹ ላይ አልወሰነም። እግዚአብሔር ነበር፣ እግዚአብሔር ብቻ፣ የትኞቹ መጻሕፍት በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲካተቱ የወሰነው። እግዚአብሔር ቀድሞ የወሰነውን ለተከታዮቹ የማስተላለፍ ጉዳይ ነበር የተከናወነው። የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን የማሰባሰብ የሰዎች ሂደት ፍጹም ባይሆንም፣ እግዚአብሔር ግን፣ በሉዓላዊነቱ፣ ከእኛም አላዋቂነትና እምቢተኝነት በመለስ፣ ቀደምት ቤተ-ክርስቲያንን እሱ ተመስጧዊ ላደረጋቸው መጻሕፍት እውቅና እንድትሰጥ አደረገ።

Englishወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የመጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳን ጽሑፎች እንዴትና መቼ አንድ ላይ ተደረጉ?
© Copyright Got Questions Ministries