settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፈውስ ምን ይላል? በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት ውስጥ ፈውስ አለ?

መልስ፤


ኢሳ 53፡5 በድጋሜ በ1ጴጥ 2፡24 የተጠቀሰው በፈውስ ጉዳይ ቁልፍ ጥቅስ ነው፤ ነገር ግን በአብዛኛው ጊዜ በተሳሳተ መረዳት ያለቦታው ነው ተግባር ላይ የሚውለው፡፡ ‹‹ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።›› ‹‹ተፈውሳችኋል›› የሚለው ቃል ትርጉም መንፈሳዊ ወይንም አካላዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን የኢሳ 53 እና 1ጴጥ 2፡24 ግልጽ የሚያደርግልን መንፈሳዊ ፈውስ እንደሆነ ነው፡፡ ‹‹ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።›› ጥቅሱ የሚናገረው ስለ ኃጢያት እና ጽድቅ ነው እንጂ ስለ በሽታና ህመም አይደለም፡፡ ስለዚህ ‹‹ተፈወሳችሁ›› በሁለቱም ክፍሎች የሚናገረው ይቅር ስለመባልና ስለመዳን ነው እንጂ ስለ አካላዊ ፈውስ አይደለም፡፡

ሌላው መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ አካላዊ ፈውስና ከመንፈሳዊ ፈውስ ጋር አያስተሳስርም፡፡ አንድ አንድ ጊዜ ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ ሲያምኑ አካላዊ ፈውስን ይቀበላሉ፤ ይህ ግን ሁል ጊዜ ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለመፈወስ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሆናል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ላይሆን ይችላል፡፡ ሐዋሪያው ዮሐንስ ትክክለኛውን ቅድመ ተከተል ያስቀምጥልናል፤ ‹‹ በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን።››(1 ዮሐ 5:14-15). እግዚአብሔር ዛሬም ተአምራትን ያደርጋል፤ ዛሬም ሰዎች ይፈወሳሉ፡፡ በሽታ ስቃይ ህመም በዚህ አለም ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ኢየሱስ ተመልሶ እስካልመጣ ድረስ በዚህ ምድር ያሉ ይሞታሉ ከሚሞቱትም ውሰጥ አብዛኛዎቹ ክርስቲያኖችን ጨምሮ በአካለቸው ላይ በሚፈጠር ችግር ነው (ህመም ስቃይ ቁስል)፡፡ አካላዊ ፈውስን ለእኛ ማድረግ ሁል ጊዜ የእግዘአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡

በመጨረሻ የእኛ ሙሉ የሆነ አካላዊ ፈውስ በሰማይ እየጠበቀን ነው፡፡ በሰማይ በዚያ ህመም የለም በሽታ ስቃይ ጉስቁልና ሞት የለም (ራዕ 21)፡፡ ሁላችንም በዚህ አለም በስጋዊ አካላዊ ሁኔታዎች ይልቅ ለመንፈሳዊ ህይወታችን የበለጠ ልንጨነቅ ያስፈልጋል (ሮሜ 1፡1-2)፡፡ የልባችንን ትኩረታችንን በሰማይ ባለው በማድረግ በምድር ላለው አንጨነቅ፡፡ ራዕ 21፡4 እውነተኛ የሆነ ሁላችንም ልንናፍቀው ስለሚገባ ፈውስ ይነግረናል፡- ‹‹እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።››

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፈውስ ምን ይላል? በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት ውስጥ ፈውስ አለ? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries