settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዴት መቀበል እችላለሁ?

መልስ፤


የሐዋርያት ሥራ ፲፫፥፴፰ እነደሚያውጀው፣ “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ የኀጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል መሆኑ እንደ ተሰበከላችሁ ዕወቁ።”

ምሕረት ምን ድነው? ለምንስ ያስፈልገናል?

“መማር” የሚለው ቃል ማስተሰርይ ወይም ዕዳን መሰረዝ ማለት ነው። አንድን ሰው ስንበድል፣ ያጣነውን ወዳጅነት ለማስተካከል ይቅርታ እንጠይቃለን። ምሕረት የሚሰጠው ግን በዳዩ ስለሚገባው አይደለም። ይቅርታ የሚገባው ግን ማንም የለም። ምሕረት የፍቅር፣ የርህራሄና የጸጋ ተግባር ነው። ምሕረት ስንል ምን ያህል በደል ቢደርስብንም በዳዩ ላይ ቂም አለመያዝ ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም የእግዚአብሔር ምሕረት እንደሚያስፈልገን ይነግረናል። ሁላችንም ኀጢአት ሠርተናል። መክብብ ፯፥፳ እነደሚያውጀው፣ “ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ፣ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም።” ፩ኛ ዮሐንስ ፩፥፰ እነደሚለን፣ “ኀጢአት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፤ እውነትም በኛ ውስጥ የለም።” ኀጢአት ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ የሚፈጸም ዐምፃ ነው (መዝሙር ፶፩፥፬). ስለዚህም የእግዚአብሔር ምሕረት በጣምኑ ያሰፈልገናል። ኀጢአታችንን ካለተስረየልን ግን የኀጢአታችን ፍሬ ለዘለዓለሙ ሲያማቅቀን ይኖራል (ማቴዎስ ፳፭፥፵፮፤ ዮሐንስ ፫፥፴፮)።

እንዴት ምሕርትን ማግኘት እንችላለን?

ምስጋና ይድረሰውና እግዚአብሔር መሀሪና አፍቃሪ ስለሆነ፣ ኀጢአታችንን ሊያስተሰርይልን ጉጉ ነው! ፪ኛ ጴጥሮስ ፫፥፱ እንደሚነግረን፣ “…ነግር ግን ማንም እንዳይጠፋ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንት ይታገሣል።” እግዚአብሔር ሊምረን ስለሚፈልግ፣ ምሕረት የምናገኝበትን መንገድ አመቻቸልን።

ለኀጢአት ተገቢ ቅጣት ሞት ብቻ ነው። ለዚህ ድጋፍ ሮሜ ፮፥፳፫ እንዲህ ያውጃል፣ “የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና…።” የኀጢአታችን ዋጋ የዘለዓለም ሞት ነው። እግዚአብሔር ፍጹም በሆነ ጥበቡ ሰው የሆነው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን ላከልን (ዮሐንስ ፩፥፩፣ ፲፬)። የኀጢአታችን ደመወዝ የሆነው ሞትንም ኢየሱስ በመስቀል ሞቶ ተቀበለልን! ፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፥፳፩ እነደሚያስተምረን፣ “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንዲሆን፣ ኀጢአት የሌለበት እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።” በአምላክነቱም የኢየሱስ ሞት የምድርን ሁሉ ኀጢአት አስተሰረየ። ፩ኛ ዮሐንስ ፪፥፪ እነዲህ ያውጃል፣ “እርሱም የኀጢአታችን ማስተስረያ ነው። ይኸውም ለዓለም ሁሉ ኀጢአት እንጂ ለእኛ ብቻ አይደለም።” ኢየሱስ ኀጢአትንና ሞትን አሸንፎ ከሙታን ተነሣ (፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፭፥፩-፳፰)። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና መነሣት፣ በሮሜ ፮፥፳፫ የተባለው እውነት ሆነ፤ “…የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘለዓለም ሕይወት ነው።”

ኀጢአትህ እንዲሰረይልህ ትሻለህ? የጥፋተኝነት ሰሜትንስ ሁሌ ይነዘንዘሃል? የኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምነኽ ከተቀበልክ፣ ምሕረትን ታገኛህ። ኤፌሶን ፩፥፯ እነደሚለው፣ “በእርሱም እነደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገ ቤዛነት፣ የኀጢአትን ይቅርታ አገኘን።” ይቅርታን እናገኝ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ዕዳችንን ከፈለልን። ስለዚህም፣ ምሕረትን ለማግኘት በኢየሱስ አዳኝነት አምነን እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብን። እግዚአብሔርም ይምረናል። ዮሐንስ ፫፥ ፲፮-፲፯ ይህንን ግሩም የሆነ መልእክት ይዟል፣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው።”

ምሕረት ማግኘት እንዲህ ቀላል ነውን?

አዎን በጣም ቀላል ነው! ምሕረትን በሥራህ ከእግዚአብሔር ልታገኝ አትችልም። ከእግዚአብሔር ለምታገኘው ምሕረትንም ዋጋ መክፈል አትችልም። የኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና የእግዚአብሔርንም ምሕረት መቀበል ስትፈልግ የሚከተለውን ጸሎት መጸለይ ትችላለህ። ይህንን ወይንም ሌላ ጸሎት መድገም በራሱ አያድንህም። ኀጢአትህ ይቅር የሚባልልህ በኢየሱስ ክርስቶስ ካመንክ ብቻ ነው። ይህ ጸሎት በእግዚአብሔር ያለህን እምነት ለመግለጽና ስለ ምሕረቱንም ምስጋና ለማቅረብ ብቻ ነው የሚረዳህ። “እግዚአብሔር ሆይ፤ ባነተ ላይ ኀጢአት መሥራቴንና ለኀጢአቴም ዋጋ ቅጣት እንደሚገባኝ አውቃለሁ። ይሁን እንጂ እኔ እድን ዘንድ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅጣቴን ተቀብሎልኛል። ከኀጢአቴም በመራቅ እምነቴ በምሕረተህ አኖራለሁ። ድነቅ ለሆነው ጸጋህንና ይቅር ባይነትህን አመሰግንሃለሁ! አሜን!”

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዴት መቀበል እችላለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries