settings icon
share icon
ጥያቄ፤

አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት እነማን ነበሩ/ የኢየሱስ ክርስቶስ ሃዋሪያት ነበሩ?

መልስ፤


ደቀመዝሙር›› የሚለው ቃል ተማሪ ወይም ተከታይ የሚለውን ያመለክታል፡፡ ‹‹ሐዋሪያ›› የሚለው ቃል የተላከ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት አስራ ሁለቱ የእርሱ ተከታዮች ደቀመዝሙር ይባሉ ነበር፡፡ አስራ ሁለት ደቀመዛሙርት ኢየሱስ ክርስቶስን ተከተሉት ከእርሱ ተማሩ በእርሱም የሰለጠኑ ነበሩ፡፡ ከኢየሱስ ትንሳኤ እና እርገት በኋላ ኢየሱስ ምስክር እንዲሆኑ ደቀመዛሙርቱን ላካቸው(ማቲ 28:18-20; ሥራ 1:8)፡፡ አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ተብለው ተጠቀሱ፡፡ ሆኖም ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በነበረበት ጊዜ ‹‹ደቀመዝሙር›› የሚለውና ‹‹ሐዋሪያ›› የሚለው ቃል በመለዋወጥ ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡

ትክክለኛ አስራሁለቱ ደቀመዛሙርት ወይም ሐዋሪያት በማቲ 10፡ 2-4 ተጠቅሰዋል ‹‹የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።›› መጽሐፍ ቅዱስ በተጨማሪ ማር 3:16-19 አና ሉቃ 6:13-16 ጠቅሶአቸዋል፡፡የሶስቱ ክፍሎች ንጽጽር የተወሰኑ ልዩነቶችን ያመለክታል፡፡ እንድሪያስ ‹‹ይሁዳ፤ የያዕቆብ ልጅ›› ተብሎ የሚታወቅም ይመስላል” (ሉቃ 6:16) እና በርተሎሚዎስ (ማቲ 10:3).

ስሞኦን ቀናተኛውም እንዲሁ ከነዓናዊው ስምኦን (ማር 3:18). ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ አስቆሮቱ በማቲያስ የተተካው(በተጨመሪ ሥራ 1፡20-26) ተመልከቱ፡፡ አንዳንድ አስተማሪዎችን ማቲዎስን ባለመቀበል ጳውሎስ ከአስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ውስጥ በእግዚአብሔር ጥሪ ሆኖአል ብለው ያምናሉ፡፡

አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ወይም ሐዋሪያት ተራ ሰዎች ነበሩ እግዚአብሔር ግን በተለየ ባልተለመደ ሁኔታ ተጠቀመባቸው፡፡ ከነርሱ መካከል አሳ አጥማጆች ቀረጥ ሰብሳቢዎች እና አመጸኞች ሰዎች ነበሩ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእንዚህን ኢየሱስ ክርስቶስን የተከተሉ አስራ ሁለት ሰዎች ውድቀት ተግል እና ጥርጣሬ አስቀምጦልናል፡፡ ከኢየሱስ ትንሳኤና እርገት ምስክርነት በኋላ መንፈስ ቅዱስ እንዚህን ሰዎች ኃይለኛ

አድርጎ ለወጣቸው ይህንን አልም ገለባባጡ (ሥራ 17፡6)፡፡ ለውጡ ምን ነበር; አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ‹‹ከኢየሱስ ጋር ነበሩ›› (ሥራ 4፡13). ለእኛም እንደዚሁ ይባልልን!

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት እነማን ነበሩ/ የኢየሱስ ክርስቶስ ሃዋሪያት ነበሩ? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries