settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ሴት መጋቢዎች/ ሰባኪዎች? መጽሐፍ ቅዱስ በአገልግሎት ውስጥ ስለ ሴቶች ምን ይላል?

መልስ፤


ምናልባት ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሴቶች እንደ መጋቢዎች/ሰባኪዎች የማገልገላቸውን ጉዳይ የበለጠ ሞቅ ያለ አከራካሪ ጉዳይ ሌላ የለም፡፡ ስለሆነም ይህን ጉዳይ ልክ ወንዶችን ከሴቶች ጋር እንደ ማወዳደሩ አለማየቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ሴቶች እንደ መጋቢዎች ማገልገል እንደሌለባቸው እና መጽሐፍ ቅዱስ በሴቶች አገልግሎት ላይ ገደቦችን እንዳስቀመጠ ያን የሚያምኑ ሴቶች አሉ፤ እና ሴቶች እንደ ሰባኪዎች ማገልገል እንደሚችሉ የሚያምኑ እና በአገልግሎት ውስጥ በሴቶች ላይ ገደቦች እንደሌሉ ያን የሚያምኑ ወንዶች አሉ፡፡ ይሄ የመድልዎ ወይም የማግለል ጉዳይ አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ ጉዳይ ነው፡፡

“ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፤ ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም።” እያለ የእግዚአብሔር ቃል ያውጃል (1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11-12)፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔር የተለያዩ ኃላፊነቶችን ለወንዶችና ለሴቶች ሰጥቷል፡፡ ይህ የሰው ዘር የተፈጠረበት መንገድ እና ኃጥአት ወደ ዓለም የገባበት መንገድ ውጤት ነው (1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡13-14)፡፡ እግዚአብሔር በሐዋሪያው ጳውሎስ በኩል ሴቶችን በማስተማሩ ኃላፊነት ከማገልገል እና/ወይም በእነርሱ ላይ መንፈሳዊ ሥልጣን እንዳይኖራቸው ይገድባል፡፡ ይህ ሴቶችን እንደ መጋቢነት ፤ በትክክል መስበክን፣ ማስተማርን እና በወንዶች ላይ መንፈሳዊ ሥልጣን ማግኘትን የሚያጠቃልለውን እንዳያገለግሉ ይከለክላል፡፡

በዚህ አገልግሎት ውስጥ ሴቶችን በተመለከተ ብዙ ተቃውሞዎች አሉ፡፡ የተለመደው ጳውሎስ ሴቶችን ከማስተማር ይገድባል፤ ምክንያቱም በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ሴቶች ያልተማሩ ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን በ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11-14 የትምህርት ደረጃን በየትም ስፍራ አልጠቀሰም፡፡ ትምህርት ለአገልግሎት መስፈርት ቢሆን ኖሮ ብዙኃኖቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ብቁ ባልሆኑ ነበር፡፡ ሁለተኛው የጋራ ተቃውሞ ጳውሎስ ከማስተማር ያገደው የኤፌሶንን ሴቶች ብቻ ነው (1ኛ ጢሞቴዎስ የተጻፈው በኤፌሶን ለነበረች ቤተክርስቲያን መጋቢ ለነበረው ለጢሞቴዎስ ነበር)፡፡ የኤፌሶን ከተማ የግሪክ/ሮማ የሀሰት አማልክቶች በአርጤምስ ቤተ-መቅደስ ይታወቅ ነበር፡፡ ሴቶች አርጤምስን በማምለኩ ሥልጣን ነበራቸው፡፡ ሆኖም ግን የ1ኛ ጢሞቴዎስ መጽሐፍም ሆነ ጳውሎስ በየትም ሥፍራ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11-12 ውስጥ የአርጤምስን አምልኮ ለገደቡ እንደ ምክንያ አልተጠቀሰም፡፡

የተለመደው ሦስተኛው ተቃውሞ ጳውሎስ በአጠቃላይ ለወንዶች እና ለሴቶች ሳይሆን ባሎችንና ሚስቶችን ብቻ እያመለከተ ነው፡፡ በምንባቡ ውስጥ ያሉት የግሪኩ ቃላቶች ባሎችንና ሚስቶችን ሊያመለክት ይችላል፤ ሆኖም ግን የቃላቶቹ መሠረታዊ ትርጉም ወንዶችና ሴቶችን ያመለክታል፡፡ በተጨማሪ ተመሳሳይ የግሪክ ቃላቶች በቁጥር 8-10 ውስጥ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ያለ ቍጣና ያለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆቻቸውን እያነሱ የሚጸልዩት ወንዶች ብቻ ናቸው? (ቁጥር 8)፤ እንደሚገባ የሚለብሱት፣ መልካምን ሥራን በማድረግ እግዚአብሔርን የሚያመልኩት ሚስቶች ብቻ ናቸው? (ቁጥር 9-10)፤ በእርግጥ አይደለም፡፡ ቁጥር 8-10 በግልጽ ባሎችና ሚስቶችን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ወንዶችና ሴቶችን ያመለክታል፡፡ በቁጥር 11-14 በአገባቡ ውስጥ ወደ ባሎችና ሚስቶች መሸጋገርን የሚያመለክት ምንም ነገር የለም፡፡

አሁንም ለዚህ ሴቶችን በአገልግሎት ውስጥ በተመለከተ ለሚሰጠው ትርጓሜ ሌላው ተደጋጋሚ ተቃመውሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመሪነትን ቦታ ይዘው ከነበሩ ሴቶች ጋር በሚገናኝ መልኩ ነው፤ በተለይ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ማሪያም፣ ዲቦራ እና ሕልዳና ናቸው፡፡ ይህ ተቃውሞ ጥቂት ዋና ጉዳዮችን ሳያካትት ቀርቷል፡፡ በመጀመሪያ ዲቦራ ከ13 ወንድ ፈራጆች መካከል ብቸኛዋ ሴት ፈራጅ ነበረች፡፡ ሕልዳና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰው ከነበሩ ብዙ ወንድ ነብያቶች መካከል ብቸኛዋ ነብይት ነበረች፡፡ የማሪያም ከመሪነት ጋር የተገናኘው ብቸኛው መንገድ የሙሴ እና አሮን እህት መሆኗ ነበር፡፡ በነገሥታት ዘመን ሁለት በጣም ስመ-ጥር ሴቶች፤ጎቶልያ እና ኤልዛቤል፤ ከእግዚአብሔር የሆኑ የሴት መሪዎች ምሳሌዎች አልነበሩም፡፡ ምንም እንኳን በብሉይ ኪዳን የነበረው የሴቶች ስልጣን በጣም በዋናነት ከጉዳዩ ጋር ባይገናኝም፡፡ የ1ኛ ጢሞቴዎስ መጽሐፍ እና ሌሎች የመጋቢው መልእክቶች የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለቤተክርስቲያን አዲስ ምሳሌዎችን ያቀርባል እና ያ ምሳሌ ለእስራኤል ህዝብ ወይም ሌላ የብሉይ ኪዳን አካል ሳይሆን ለቤተክርስቲያን የስልጣን መዋቅርን ያካትታል፡፡

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ጵርስቅላን እና ፎኤብን በመጠቀም ተመሳሳይ ክርክር ተደርጓል፡፡ በሐዋሪያት ሥራ 18 ውስጥ ጵርስቅላ እና አቂላ እንደ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋዮች እንደሆኑ ቀርቧል፡፡ ምናልባት ከባሏ ይልቅ በአገልግሎት የበለጠ “ስመ-ጥር” እንደነበረች በሚያመለክት የጵርስቅላ ስም በመጀመሪያ ተጠቅሷል፡፡ ሆኖም ግን ከ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፤11-14 ጋር በተቃራኒ ጵርስቅላ በየትም ስፍራ በአገልግሎት ሥራ ውስጥ ስትሳተፍ አይገልጽም፡፡ ጵርስቅላ እና አቂላ አጵሎስን ወደ ቤታቸው አምጥተው የእግዚአብሔርን ቃል በበለጠ በትክክል እያብራሩ ሁለቱም ደቀ-መዝሙር አደረጉት፡፡(የሐዋሪያት ሥራ 18፤26)

ወደ ሮሜ ሰዎች 16፡1 ውስጥ ፌበን ከ”አገልጋይነት” ፈንታ እንደ “ዲያቆን” ብትታሰብም እንኳ ያ ፌበን በቤተክርስቲያን ውስጥ አስተማሪ እንደነበረች አያመለክትም፡፡ “ማስተማር መቻል” ለመሪዎች እንደብቃት መለኪያ ተሰጠ እንጂ ለዲያቆናት አይደለም (1ኛ ጢሞቴዎስ 3፤1-13፣ ወደ ቲቶ 1፤6-9)፡፡ መሪዎች ወይም ጳጳሳት ወይም ዲያቆናት “የአንዲት ሚስት ባል”፣ “ልጆቻቸው ያመኑ” እና “የተከበሩ ሰዎች” እንደሆኑ ተገልፆአል፡፡ ሀሳቡ በግልጽ እነዚህ ብቃቶች ወንዶችን ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም በ1ኛ ጢሞቴዎስ 3፤1-13 እና ወደ ቲቶ 1፤6-9 ውስጥ መሪዎችን/ጳጳሳትን/ዲያቆናትን ለማመልከት ሙሉ ለሙሉ የተባዕታይ ጾታ ተውላጠ-ስም ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

የ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11-14 አገላለጽ “ምክንያቱን” በደንብ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ ቁጥር 13 በ “ለ” ይጀምርና ለጳውሎ ዐረፍተ ነገር በ11-12 ቁጥሮች ውስጥ “መንስኤ” ይሰጣል፡፡ ሴቶች ወንዶችን ማስተማር ወይም በእነርሱ ላይ ስልጣን ማግኘት የሌለባቸው ለምንድነው? ምክንያቱም “አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ ከዚያም ሔዋን። የተታለለውም አዳም አልነበረም፥ የተታለለችው ሴቲቱ ነበረች፡፡” እግዚአብሔር መጀመሪያ አዳምን ፈጠረ ከዚያም ለአዳም “ረዳት” እንድትሆነው ሔዋንን ደግሞ ፈጠረ፡፡ ይኸ የፍጥረት ተዋረድ በቤተሰብ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፤22-23) እና በቤተክርስቲያን ውስጥ በየትም የሚሆን ነው፡፡ በተጨማሪም ሔዋን የመታለሏ እውነታ ሴቶች እንደ መጋቢ እንዳያገለግሉ ወይም በወንዶች ላይ መንፈሳዊ ስልጣን እንዳይኖራቸው እንደምክንያት ተሰጥቷል፡፡ ይህ ጥቂቶችን ሴቶች በበለጠ በቀላሉ በመታለላቸው ምክንያ እነርሱ ማስተማር የለባቸውም የሚለውን ወደ ማመን ይመራቸዋል፡፡ ያ ሀሳብ አከራካሪ ነው ነገር ግን ሴቶች በበለጠ በቀላሉ የሚታሉ ቢሆኑ ልጆችን (በቀላሉ የሚታለሉትን) እና ሌሎች ሴቶችን (በጣም በቀላሉ ይታለላሉ የተባሉትን) እንዲያስተምሩ ለምን ይፈቀድላቸዋል? ምንባቡ የሚለው ነገር አይደለም፡፡ ሔዋን በመታለሏ ምክንያት ሴቶች ወንዶችን ማስተማር ወይም በወንዶች ላይ መንፈሳዊ ስልጣን ሊኖራቸው አይገባም፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ የመጀመሪያውን የማስተማር ሥልጣን ለወንዶች ሰጥቷል፡፡

ብዙ ሴቶች እንግዶችን በመቀበል ፤ በምህረት፤ በማስተማር እና በመርዳት ስጦታዎች ይልቃሉ፡፡ ብዙኃኑ የአጥቢያ ቤተክርስቲያናት አገልግሎት በሴቶች ላይ የተደገፈ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሴቶች በወንዶች ላይ ከመንፈሳዊ የማስተማር ሥልጣን ብቻ ተገድበዋል እንጂ በጉባኤ ከመፀለይ ወይም ትንቢትን ከመናገር አልተከለከሉም (1ኛ ቆሮንቶስ 11፡5)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሴቶች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች ከመለማመድ የከለከለበት የትም ሥፍራ የለም(1ኛ ቆሮንቶስ 12)፡፡ ሴቶች ልክ የወንዶችን ያህል ሌሎችን ለማገልገል፣ የመንፈስ ፍሬዎችን ለማሳየት (ወደ ገላቲያ ሰዎች 5፤22-23) እና ወንጌልን ለጠፉት ለማወጅ (የማቴዎስ ወንጌል 28፤18-20፣ የሐዋርያት ሥራ 1፤8፣ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15) ተጠርተዋል፡፡

እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ በመንፈሳዊ የማስተማር ኃላፊነቶች ቦታ ወንዶች ብቻ እንዲያገለግሉ አዟል፡፡ ይኸ ወንዶች የግድ የተሻሉ አስተማሪዎች ስለሆኑ ወይም ሴቶች የበታች ወይም ያነሰ ችሎታ ያላቸው በመሆናቸው ምክንያት አይደለም፡፡ በቀላሉ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን እንዴት እንድትሠራ ያበጀበት መንገድ ነው፡፡ ወንዶች በህይወቶቻቸው እና በቃሎቻቸው በመንፈሳዊ መሪነት ምሳሌን ማሳየት ይገባቸዋል፡፡ ሴቶች ዝቅተኛውን የሥልጣን ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባቸዋል፡፡ ሴቶች ሌሎች ሴቶችን እንዲያስተምሩ ይበረታታሉ (ወደ ቲቶ 2፤3-5)፡፡ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ሴቶች ልጆችን ከማስተማር አይከለክልም፡፡ ሴቶች የተከለከሉት ብቸኛው ተግባር ወንዶችን ከማስተማር ወይም በወንዶች ላይ ከሚኖራቸው መንፈሳዊ ሥልጣን ነው፡፡ ይኸ በተገቢው አስተሳሰብ ሴቶችን እንደ መጋቢ ወይም ሰባኪ እንዳያገለግሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ይኸ በማንኛውም መንገድ ሴቶችን የማይጠቅሙ አያደርግም ነገር ግን ይልቁን ከእግዚአብሔር ዕቅድ ጋር የበለጠ የሚስማማውን እና ለእነርሱ በሰጣቸው ስጦታዎች ላይ ትኩረት ያደረገውን አገልግሎት ይሰጣቸዋል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ሴት መጋቢዎች/ ሰባኪዎች? መጽሐፍ ቅዱስ በአገልግሎት ውስጥ ስለ ሴቶች ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries