settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የክርስቲያን ራስን የማጥፋት እይታው ምንድነው? መጽሐፍ ቅዱስ ራስን ስለ ማጥፋት ምን ይላል?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ራሳቸውን ያጠፉ ስድስት የተለዩ ሰዎችን ይጠቅሳል፤አቤሜሌክ (መጽሐፈ መሳፍንት 9፤54)፤ ሳዖል (1ኛ ሳሙኤል 31፤4)፤ የሳዖል ጋሻ ጃግሬ (1ኛ ሳሙኤል 31፤4-6)፤ አኪጦፌል (2ኛ ሳሙኤል 17፤23)፤ ዘምሪ (1ኛ ነገሥት 16፤18) እና ይሁዳ (የማቴዎስ ወንጌል 27፤5)፡፡ አምስቶቹ ሰዎች ክፉዎች፤ በኃጥአት የተሞሉ ነበሩ፤ (የሳዖልን ጋሻ ጃግሬ በተመለከተ ስለ ባህርይው ለመፍረድ በቂ ነገር አልተባለም)፡፡ የተወሰኑቱ ሳምሶንን ራስን የማጥፋት ምሳሌ ያደርጉታል (መጽሐፈ መሳፍንት 16፤26-31) ነገር ግን የሳምሶን ግቡ የነበረው ራሱን ሳይሆን ፍልስጥኤማውያንን መግደል ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ራስን ማጥፋት ነፍስ ከመግደል ጋር እኩል ያደርገዋል ያም ራስን መግደል የሆነው ነው፡፡ መቼ እና እንዴት አንድ ሰው መሞት እንዳለበት ለመወሰን ብቸኛው እግዚአብሔር ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ራስን ማጥፋት እንድ ሰው ወደ መንግሥተ-ሰማይ መግቢያ የማግኘቱን ነገር የሚወስን ነገር አይደለም፡፡ ያላመነ ሰው ራሱን ቢያጠፋ ወደ ገሃነም የሚገባበትን ጉዞ አፈጠነ እንጂ ምንም ነገር አላደረገም፡፡ ሆኖም ግን ያ ራሱን ያጠፋው ሰው ራሱን በማጥፋቱ ምክንያ ሳይሆን በክርስቶስ በኩል የሆነውን ድነት ባለመቀበሉ በመጨረሻው በገሃነም ይሆናል፡፡ ራሱን ስለሚያጠፋው ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? በእውነት በክርስቶስ ካመንበት ጊዜ ጀምሮ የዘላለምን ህይወት ዋስትና እንዳገኘን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል (የዮሐንስ ወንጌል 3፤16)፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ክርስቲያኖች ከማንኛውም ጥርጣሬ ባለፈ የዘላለም ህይወት እንዳላቸው ማወቅ ይችላሉ (1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 5፤13)፡፡ ክርስቲያንን ከእግዚአብሔር ፍቅር ምንም ነገር መለየት አይችልም (ወደ ሮሜ ሰዎች 8፤38-39)፡፡ ምንም “የተፈጠረ ነገር” ክርስቲያንን ከእግዚአብሔር ፍቅር መለየት ካልቻለ እና እንዲያውም ራሱን የሚያጠፋ ክርስቲያን “የተፈጠረ ነገር” ነው፤ከዚያ ራስን ማጥፋ እንዲያውም ክርስቲያንን ከእግዚአብሔር ፍቅር መለየት አይችልም፡፡ ኢየሱስ ለኃጥአቶቻችን በሙሉ ሞቷል እናም እውነተኛ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ጥቃት እና ድካም ጊዜ ራሱን ቢያጠፋ አሁንም ያ በክርስቶስ ደም የተሸፈነ ኃጥአት ይሆናል፡፡

ራስን ማጥፋት አሁንም ድረስ በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ ኃይለኛ ኃጥአት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ራስን ማጥፋ ነፍስን መግደል ነው፤ሁልጊዜም ስህተት ነው፡፡ ማንም ክርስቲያን ነኝ የሚል ሰው ነገር ግን ደግሞ ራሱን ስላጠፋው ስለ እምነቱ እውነተኛነት ኃይለኛ ጥርጣሬ ይነሳል፡፡ አንድን ሰው በተለይ ስለራሱ/ስለራሷ ህይወት የሚናገር በተለይ ክርስቲያንን ሊያጸድቅ የሚችል ምንም ሁኔታ የለም፡፡ ክርስቲያኖች ህይወታቸውን ለእግዚአብሔር ለመኖር ተጠርተዋል፤እናም የሚሞትበት ጊዜ ውሳኔ የእግዚአብሔር እና የእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ምንም እንኳን ራስ ማጥፋትን የሚገልጽ ባይሆንም 1ኛ ቆሮንቶስ 3፤15 ራሱን በሚያጠፋ ክርስቲያን ላይ ሊሆን ያለውን ነገር ምናልባት ጥሩ መግለጫ ይሆናል፤ “እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል።”

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የክርስቲያን ራስን የማጥፋት እይታው ምንድነው? መጽሐፍ ቅዱስ ራስን ስለ ማጥፋት ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries