settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ስለ አንድ ነገር ደጋግሞ መጸለይ ተቀባይነት አለውን፣ ወይስ መጸለይ ያለብን አንድ ጊዜ ብቻ ነው?

መልስ፤


ሉቃስ 18፡1-7 ላይ፣ ኢየሱስ በምሳሌ አስረድቷል፣ በጸሎት ትዕግሥት አስፈላጊ ስለመሆኑ። እሱም ስለ አንዲት መበለት ታሪክ ነግሮናል፣ በባላጋራዋ ላይ ፍትሕን ፍለጋ ወደ ዐመጸኛው ዳኛ የመጣችው። ከጽኑ ልመናዋ የተነሣ፣ ዳኛው ለዘበ። የኢየሱስ ነጥብ፣ አንድ ዐመጸኛ ዳኛ የአንዲቱን ልመና ከሰማ፣ ፍትሕን የመፈለግ ጥያቄ፣ የሚወደን እግዚአብሔርማ እንዴታ—“ምርጦቹን” (ቁ. 7)—ጸሎታችንን ይመልሳል፣ በጸሎታችን ከቀጠልንበት? ምሳሌው በስሕተት እንደሚታሰበው የሚያስተምር አይደለም፣ ማለትም ስለ አንድ ነገር ደግመን ደጋግመን ከጸለይን እግዚአብሔር እሱን ሊሰጠን ይገደዳል በሚል። ይልቁንም እግዚአብሔር በራሱ እንደሚበቀል ተስፋ ሰጥቷል፣ ሊከላከልላቸው፣ ስሕተታቸውን ሊያርም፣ ጻድቅ ሊያደርጋቸው፣ ከባለጋራዎቻቸው ሊታደጋቸው። ይሄንን የሚያደርገው ከፍትሐዊነቱ፣ ከቅድስናው፣ እና ኃጢአትን ከመጥላቱ የተነሣ ነው፤ ጸሎትን ስለመመለስ፣ እሱ ቃሉን ይጠብቃል ኃይሉንም ይገልጻል።

ኢየሱስ ስለ ጸሎት ሌላ መግለጫ ሰጥቷል፣ ሉቃስ 11፡5-12 ላይ። እንደ ዐመጸኛው ዳኛ ምሳሌ ተመሳሳይ የሆነ፣ የኢየሱስ መልእክት በዚህ ምንባብ ላይ፣ አንድ ሰው ለተቸገረ ባልንጀራው ለመስጠት ፍላጎት ከሌለው፣ እግዚአብሔር በተሻለ መልኩ ለፍላጎታችን ይሰጠናል፣ ምንም ዓይነት ጥያቄ ለእሱ የማይስማማ ሆኖ ሳለ። እዚህ ደግሞ፣ ተስፋው የምንቀበለው አይደለም፣ በፈለገው መልኩ ብንለምንና በልመናችን ብንቀጥል። የእግዚአብሔር ተስፋ ለልጆቹ፣ ለፍላጎታችን የሚሆን ተስፋ ነው፣ ለመሻታችን አይደለም። እሱም ፍላጎታችንን ያውቃል፣ ከእኛ ይልቅ። ተመሳሳይ ተስፋ ማቴዎስ 7:7-11 እና ሉቃስ 11:13 ላይ ተደግሟል፣ “መልካሙ ስጦታ” መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ተስፋፍቶ የተብራራበት።

እነዚህ ሁለቱም ምንባቦች እንድንጸልይና በጸሎት እንድንቀጥል ያበረታቱናል። ስለ አንድ ነገር ደጋግሞ መለመን ችግር የለውም። የምትጸልየው በእግዚአብሔር ፍቃድ ውስጥ እስከ ሆነ ድረስ (1 ዮሐንስ 5፡14-15)፣ በጸሎትህ ቀጥል፣ እግዚአብሔር ጥያቄህን እስኪመልስ ድረስ ወይም መሻትህን ከልብህ እስኪወስድ ድረስ። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ለጸሎታችን ምላሽ ከመስጠት እንድንጠብቅ ሊያስገድደን ይችላል፣ ትዕግሥትና ጽናትን ሊያስተምረን። አንዳንድ ጊዜ ስለ አንድ ነገር እንለምናለን፣ የእግዚአብሔር ሰዓት በሕይወታችን እንዳልሆነ እየተረጋገጠ። አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ፍቃድ በሕይወታችን ያልሆነውን እንለምናለን፣ እሱም “አይሆንም” ይላል። ጸሎት ለእግዚአብሔር ጥያቄያችንን የምናቀርብበት ብቻ አይደለም፤ እሱ፣ እግዚአብሔር ፍቃዱን በልባችን የሚያኖርበት ነው። መለመናችሁን ቀጥሉ፣ ማንኳኳታችሁን ቀጥሉ፣ መፈለጋችሁንም ቀጥሉ፣ እግዚአብሔር ጥያቄያችሁን እስኪመልስ ድረስ ወይም ልመናችሁ ለእናንተ የእሱ ፍቃድ አለመሆኑን እስኪያስረዳችሁ ድረስ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ስለ አንድ ነገር ደጋግሞ መጸለይ ተቀባይነት አለውን፣ ወይስ መጸለይ ያለብን አንድ ጊዜ ብቻ ነው?
© Copyright Got Questions Ministries