settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የተለያዩ ዘሮች መነሻ ምንድነው?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ “ዘሮችን” ወይም የሰዎችን የቆዳ ቀለም መነሻ በተብራራ መልኩ አይሰጠንም። በርግጠኝነት አንድ ዘር ብቻ አለ— የሰው ዘር። በሰው ዘር ውስጥ የቆዳ ቀለም እና የሌሎች አካላዊ ባሕርያት ብዝኃነት አለ። አንዳንዶች የሚገምቱት፣ እግዚአብሔር በባብኤል ግንብ ቋንቋዎችን በደበላለቀ ጊዜ (ዘፍጥረት 11፡1-9)፣ እሱ ደግሞ የዘር ብዝኃነትን ፈጥሯል። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ጀነቲካዊ ለውጥ አድርጓል ማለት ይቻላል፣ የሰው ልጆች በተለያዩ ሥነ-ምኅዳሮች በተሻለ ይኖሩ ዘንድ፣ ለምሳሌ የአፍሪካውያን ጥቁር ቀለም ከጀነቲክ አኳያ በአፍሪካ ሙቀታማ ስፍራዎች ተቋቁሞ መኖር ይችላል። በዚህ እይታ መሠረት፣ እግዚአብሔር ቋንቋዎችን ደበላለቀ፣ ይህም ሰዎችን ከቋንቋ አኳያ ለመከፋፈል፣ ከዚያም ጀነቲካዊ የዘር ልዩነቶችን ፈጠረ፣ እያንዳንዱ ዘር ወገን በሰፈረበት አካባቢ ላይ በመመሥረት። ሊሆን ቢችልም ለዚህ አተያይ የተለየ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለም። የሰዎች ዘሮች/የቆዳ ቀለሞች የትም ቦታ አልተጠቀሱም ከባብኤል ግንብ ጋር በተያያዘ።

ከጥፋት ውኃ በኋላ የተለያዩ ቋንቋዎች መፈጠር ሲጀምሩ፣ አንድ ቋንቋ የሚናገሩ ወገኖች ከሌሎች ከተመሳሳይ ቋንቋ ተናጋሪዎች ጋር መንቀሳቀስ ጀመሩ። ይህን በማድረግም ለአንድ የተወሰነ ወገን ያለው ጀነቲካዊ ምድብ ባስገራሚ ሁኔታ ማሽቆልቆል ጀመረ፣ ቡድኑ ከዚያም በኋላ ይደበላለቅ ዘንድ ሙሉው የሰው ዘር አይኖረውም። የቀረበ የዘር ርቢ ስፍራውን ያዘ፣ እናም በጊዜ ውስጥ የሚሆኑ ገጽታዎች በእነዚህ የተለያዩ ቡድኖች እየተጋነኑ መጡ (ሁሉም በጀነቲክ መለያ ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉበት አጋጣሚ አለ)። በትውልድ ውስጥ ተጨማሪ ዝርያ ሲፈጠር የዘር ምድቡ እያነሰ እያነሰ መጣ፣ የአንድ ቋንቋ ቤተሰብ ሰዎች ሁሉ ተመሳሳይ ገጽታ እስኪኖራቸው ድረስ።

ሌላው ማብራሪያ የሚሆነው አዳምና ሔዋን የወረሱት ጂን ጥቁር፣ ጠይም፣ እና ነጭ ልጆችን እንዲወልዱ የሚያደርግ ነው (ሌላው ነገር ሁሉ በዚህ መካከል ነው)። ይህም ተመሳሳይነት አለው፣ ድብልቅ ዘሮች የሆኑ ጥንዶች አንዳንዴ በቀለም የተለዩ ልጆች ይኖራቸዋል። እግዚአብሔር በግልጽ የሰው ልጆች በገጽታቸው የተለያዩ እንዲሆኑ እስከፈለገ ድረስ፣ ትርጉም ያለው ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔር፣ አዳምና ሔዋን የተለያዩ የቆዳ ቀለም ያላቸው እንዲወልዱ እንደሰጣቸው ነው። ኋላ ላይ ከጥፋት ውኃ ብቸኞቹ ተራፊዎች ኖኅና ሚስቱ፣ የኖኅ ሦስት ልጆችና የእነሱ ሚስቶች ነበሩ — ስምንት ሰዎች ናቸው ባጠቃላይ (ዘፍጥረት 7፡13)። ምናልባት የኖኅ ምራቶች ዘራቸው የተለየ ሊሆን ይችላል። ሌላም ሊሆን የሚችለው የኖኅ ሚስት ከኖኅ የተለየች ዘር ትሆናለች። ምናልባት ስምንቱም ሁሉ ድብልቅ ዘር ሊሆኑ ይችላሉ። ማብራሪያው ምንም ይሁን ምን፣ የዚህ ጥያቄ በጣም ጠቃሚው ገጽታ ሁላችንም ተመሳሳይ ዘር መሆናችን ነው፣ ሁላችንም በአንድ አምላክ የተፈጠርን፣ ሁላችንም ለአንድ ዓላማ የተፈጠርን—እሱን ለማክበር።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የተለያዩ ዘሮች መነሻ ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries