settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ አምላክ ነውን? ኢየሱስ እኔ አምላክ ነኝ ብሎ ነበርን?

መልስ፤


በእርግጥ ኢየሱስ “እኔ አምላክ ነኝ” ብሎ በቀጥታ ስለመናገሩ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ የለም። ይሁን እንጂ ኢየሱስ አምላክ ስለመሆኑ ግን አላወጀም ማለት አይደለም። ለምሳሌ ያህል የኢየሱስ ቃል በዮሐንስ ፲፥፴ እነደተጻፈው እነዲህ ይላል፣ “እኔና አብ አንድ ነን።” ላዩን ሲታይ ይህ አምላክ አንነደሆነ ማወጁን ላያመለክት ይችላል። ቢሆንም፣ ለኢየሱስ ንግግር የአይሁድ አቀባበል ማየት በቂ ነው፤ “አይሁድም፣ ‘የምንወግርህ፣ ተራ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ በማድረግ፣ የስድብ ቃል ስለተናገርህ ነው እንጂ ከእነዚህ ስለ የትኛውም አይደለም’ ብለው መለሱለት” (ዮሐንስ ፲፥፴፫)። አይሁድ የኢየሱስን ንግግር የአምላክነቱን አዋጅ እንደሆነ ገባቸው። በእነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ አይሁድን “እኔ አምላክ አይደሁም” ብሎ አልገሠጻቸውም። ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስ አምላክነቱን በእርግጥ ማመኑን ነው፤ “እኔና አብ አንድ ነን” (ዮሐንስ ፲፥፴)። ሌላው ምሳሌ ደግሞ በዮሐንስ ፰፥፶፰ የተጻፈውን ነው፤ “ኢየሱስም፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ፣ እኔ ነኝ’ አላቸው።” ለዚህም መልስ አይሁድ ኢየሱስን ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ (ዮሐንስ ፰፥፶፱)። አምላክ ነኝ ብሎ መናገሩ እነደስድብ ባይቆጥሩት ኖሮ፣ አይሁድ ኢየሱስን በድንጋይ ሊወግሩት ባልተነሱ ነበር።

ዮሐንስ ፩፥፩ እነደሚለው፣ “…ቃልም እግዚአብሔር ነበር።” ዮሐንስ ፩፥፲፬ እንዲህ ይላል፣ “ቃልም ሥጋ ሆን።” ይህ በግልጽ እነደሚያሳየው ኢየሱስ ሥጋ የለበሰ አምላክ ነው። የሐዋሪያት ሥራ ፳፥፳፰ እነደሚነግረን፣ “…በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።” ማነው ቤተ ክርስቲያንን በደሙ የዋጃት? ኢየሱስ ክርሰቶስ። የሐዋሪያት ሥራ ፳፥፳፰ ላይ እነደተጻፈው፣ ቤተ ክርስቲያንን በገዛ ደሙ የዋጃት አምላክ ነው። ስለዚህም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው!

የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ቶማስ ኢየስሱን አስመልክቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “ጌታዬ፤ አምላኬም!” (ዮሐንስ ፳፥፳፰)። ለዚህ ንግግሩም ኢየሱስ ቶማስን ሲያርመው አይታይም። ቲቶ ፪፥፲፫ የጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት በርትተን እንድንጠብቅ ይመክረናል (በተጨማሪም ፪ኛ ጴጥሮስ ፩፥፩ ማየት ይቻላል)። በዕብራውያን ፩፥፰፣ አብ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ይላል፤ “ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤ ‘አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ ጽድቅም የመንግሥትህ በትር ይሆናል።”

በራእይ እንደተጻፈው፣ መልአክ ሐዋሪያው ዮሐንስን እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አዘዘው (ራእይ ፲፱፥፲)። በወንጌል እነደሚነበበው፣ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ አምልኮ ይቀበል ነበር (ማቴዎስ ፪፥፲፩፤ ፲፬፥፴፫፤ ፳፰፥፱፣ ፲፯፤ ሉቃስ ፳፬፥፶፪፤ ፲፱፥፲)። ሰዎች ሲያመልኩትም አልገሠጻቸውም። ኢየሱስ አምላክ ባይሆን ኖሮ ግን፣ እኔን አታምልኩ ባለ ነበር፤ ልክ መልአኩ ሐዋሪያው ዮሐንስን እነዳዘዘው። ስለ ኢየሱስ አምላክነት የሚመሰክሩ ጥቅሶችና የወንጌል ገጸ ንባቦች ብዙ ናቸው።

ከሁሉም የላቀ ምክኒያት ግን አለን። ይኸውም ኢየሱስ አምላክ ባይሆን ኖሮ፣ በሞቱ የምድርን ሐጢአት ቅጣት መቀበል ባልቻለ ነበር (፩ኛ ዮሐንስ ፪፥፪)። አምላክ ብቻ ነው ለዚህ መጨረሻ ለሌለው ቅጣት ለመቀበል (፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፥ ፳፩)፣ ለመሞትና ከሙታን በመነሳትም ሞትንና ሐጢአትን ማቸነፍ የሚችለው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ አምላክ ነውን? ኢየሱስ እኔ አምላክ ነኝ ብሎ ነበርን?
© Copyright Got Questions Ministries