settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር ስለ ብሔር-ተኮር ጋብቻ ምን ይላል?

መልስ፤


የብሉይ ኪዳን ህግ በብሔር-ተኮር ጋብቻ ውስጥ እንዳይሳተፉ እስራኤላውያንን አዟቸዋል (ኦሪት ዘዳግም 7፤3-4)፡፡ ሆኖም ግን ለዚህ ምክንያቱ በዋናነት ብሔር-ነክ አልነበረም፡፡ ይልቅ ሃይማኖታዊ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ብሔር-ተኮር ጋብቻ ላይ ትዕዛዝን የሰጠበት ምክንያት የሌላ ብሔር ሰዎች ጣዖትትን እና የውሸት አማልክት አምላኪዎች ነበሩ፡፡ እስራኤላውያን ከጣዖት አምላኪዎች፤አረማዊ ወይም አረመኔያዊ ከሆኑት ጋር ቢጋቡ ከእግዚአብሔር የተለዩ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን በጣም በተለየ መጠን በአዲስ ኪዳን ውስጥ ተመሳሳይ መርሆ ተቀምጧል፤ “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?” (2ኛ ቆሮንቶስ 6፤14)፡፡ ልክ እስራኤላውያን (በአንድ እውነተኛ እግዚአብሔር የሚያምኑ) ጣዖት አምላኪዎችን እንዳያገቡ እንደታዘዙ እንዲሁ ክርስቲያኖችም (በአንድ እውነተኛ እግዚአብሔር የሚያምኑ) ያላመኑትን እንዳያገቡ ታዘዋል፡፡ ይህንን ጥያቄ ለይቶ ለመመለስ፤አይደለም፤መጽሐፍ ቅዱስ ብሔር- ተኮር ጋብቻ ስህተት ነው አይልም፡፡

ንጉሥ ማርቲን ሉተር አንድ ሰው በቆዳ ቀለሙ ሳይሆን በእሱ ወይም በእሷ ባህርይ መፈረጅ እንዳለበት አሳስቧል፡፡ በክርስቲያን ህይወት ውስጥ ዘርን መሠረት በማድረግ ለአድልዎ ሥፍራ የለም፡፡ (የያዕቆብ መልዕክት 2፤1-10)፡፡ ጓደኛ በሚመረጥበት ጊዜ የታሰበው የትዳር አጋር በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ዳግመኛ የተወለደ እንደሆነ ክርስቲያን በመጀመሪያ ማወቅ አለበት(የዮሐንስ ወንጌል 3፤3-5)፡፡ የቆዳ ቀለም ሳይሆን በክርስቶስ የሆነ እምነት የትዳር ጓደኛን በመምረጡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ደረጃ ነው፡፡ ብሔር-ተኮር ጋብቻ ልክ የመሆን እና ያለመሆን ጉዳይ አይደለም ነገር ግን የጥበብ፤ የመለየት እና የመጸለይ ጉዳይ ነው፡፡

ብሔር-ተኮር ጋብቻ በጣም በጥንቃቄ መታየት ያለበት ብቸኛው ምክንያት ቅይጥ-ዘር ጥንዶችን በሌሎች እነሱን በመቀበሉ አስቸጋሪውን ጊዜ በሚያሳልፉት ምክንያት ምናልባት በሚገጥማቸው ችግሮች ነው፡፡ ብዙ ብሔር-ተኮር ጥንዶች፤እንዲያውም አንዳንድ ጊዜም ከቤተሰባቸው መገለል እና ነቀፋ ይገጥማቸዋል፡፡ አንዳንድ ብሔር-ተኮር ጥንዶች ልጆቻቸው ከወላጆች እና/ወይም ወንድማማቾች ወይም እህትማማቾች የተለዩ የቆዳ ዓይነቶች ሲኖራቸው ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ ብሔር-ተኮር ጥንዶች እነዚህን ነገሮች ከግምት ውስጥ ሊያስገቡ እና ለማግባትም ከወሰኑም ሊዘጋጁባቸው ይገባል፡፡ እንደገና ምንም እንኳን ክርስቲያን ማንን ማግባት ባለበት ላይ የተቀመጠ ብቸኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ገደብ ሌላኛው ሰው የክርስቶስ አካል አባል መሆኑ ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር ስለ ብሔር-ተኮር ጋብቻ ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries