settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግብረ-ሰዶማዊነት ምን ይላል? ግብረ-ሰዶማዊነት ኃጥአት ነውን?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ በተከታታይ ግብረ-ሰዶማዊ ተግባር ኃጥአት እንደሆነ ይነግረናል (ኦሪት ዘፍጥረት 19፤1-13፣ ኦሪት ዘሌዋውያን 18፤22፣ ወደ ሮሜ ሰዎች 1፤26-27፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፤9)፡፡ በተለይ ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡26-27 ግብረሰዶማዊነት እግዚአብሔርን የመካድና ያለመታዘዝ ውጤት እንደሆነ ያስተምረናል፡፡ ሰዎች በኃጥአትና በአለማመን በሚቀጥሉበት ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ የተለየ የከንቱነትንና የተስፋ-ቢስነትን ህይወት ለማሳየት አብዝቶ ለከፋ እና ነውር “አሳልፎ ይሰጣቸዋል”፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፤9 ግብረ-ሰዶምን የሚያደርጉ “ዓመፀኞች” የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ ያውጃል፡፡

እግዚአብሔር ግብረ-ሰዶማዊነት ፍላጎቶች ያለውን ሰው አልፈጠረም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ወደ ግብረ-ሰዶማዊ የሚሆኑት በኃጢአት ምክንያት (ወደ ሮሜ ሰዎች 1፤24-27) እና በመጨረሻም በገዛ ምርጫቸው እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ልክ የተወሰኑ ሰዎች ለአመፀኝነት እና ሌሎች ኃጥአቶች ዝንባሌ ጋር እንደተወለዱ ምናልባት አንድ ሰው ለግብረሰዶማዊነት አደጋ ከትልቅ ተጋላጭነት ጋር አብሮ የተወለደ ሊሆን ይችላል፡፡ ያ ሰውየው ኃጥአት በተሞላበት ፍላጎት ለኃጥአቱ ባደረገው ምርጫ በቂ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ አንድ ሰው ለቁጣ/ለንዴት ትልቅ ተጋላጭነት ጋር አብሮ ቢወለድ ለእነዚያ ፍላጎቶች መሰጠቱ ያ ትክክል ያደርገዋል? በእርግጥ አይደለም! ግብረ-ሰዶማዊነትም እንደዚያው ነው፡፡

ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ-ሰዶማዊነትን ከሌላው ከማንኛውም ነገር ይልቅ እንደ “ታላቅ” ኃጥአት አይገልጽም፡፡ ለእግዚአብሔር ሁሉም ኃጥአት አጸያፊ ነው፡፡ በ1ኛ ቆሮንቶስ 6፡9-10 ውስጥ ከተዘረዘሩት ሰውን ከእግዚአብሔር መንግስት ከሚያስቀሩት ብዙ ነገሮች አንዱ ግብረ-ሰዶማዊነት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የእግዚአብሔር ምህረት ልክ ለአመንዝራነት፣ ለጣዖት አምላኪዎች፣ ለነፍሰ-ገዳዮች፣ ለሌቦች ወ.ዘ.ተ እንዳለ ሁሉ ለግብረ-ሰዶማዊነትም አለ፡፡ እግዚአብሔር ፤ግብረ-ሰዶማዊነትንም ጨምሮ፤ ለድነታቸው በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ በኃጥአት ላይ ድል ለመቀዳጀት ጥንካሬን ሊሰጣቸው በተጨማሪ ቃል ይገባል (1ኛ ቆሮንቶስ 6፡11፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17፣ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡13)፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግብረ-ሰዶማዊነት ምን ይላል? ግብረ-ሰዶማዊነት ኃጥአት ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries