settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በሰማይ ያሉ ሰዎች ቁልቁል ይመለከታሉን፣ እኛንስ ገና በምድር ላይ ያለነውን ይመለከቱናልን?

መልስ፤


ዕብራውያን 12፡1 እንደሚያስቀምጠው፣ “ስለዚህ፣ እንደ ታላቅ ደመና በሚያህሉ ምስክሮች ስለተከበብን…” አንዳንዶች “እንደ ደመና የሚያህሉ ምስክሮችን” የሚረዱት፣ ከሰማይ ሆነው እኛን ቁልቁል እንደሚመለከቱ ሰዎች ነው። ያ ትክክለኛ ትርጉም አይደለም። ዕብራውያን 11 የመዘገበው እግዚአብሔር በእምነታቸው ምክንያት የጠቀሳቸውን ብዙ ሰዎች ነው። እነዚህ ሰዎች ናቸው “እንደ ደመና የሚያህሉ ምስክሮች።” እነርሱ “ምስክሮች” ናቸው፣ እኛን የሚመለከቱ ሳይሆኑ ግን ይልቁንም ለእኛ ምሳሌ የሚሆኑ እንጂ። እነርሱ የክርስቶስ እና የእግዚአብሔር እና የእውነት ምስክሮች ናቸው። ዕብራውያን 12፡1 ይቀጥላል፣ “…እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ።” ከእኛ ቀድመው የሄዱትን ክርስቲያኖች እምነትና ቁርጠኝነት ተመልክተን፣ የእነሱን ምሳሌ ለመከተል መሰጠት አለብን።

መጽሐፍ ቅዱስ ለይቶ ምንም አይልም፣ በሰማይ ያሉት ሰዎች እኛን ቁልቁል እንደሚመለከቱን፣ አሁን በምድር ላይ ያለነውን። እንደሚችሉ ፈጽሞ አይመስልም። ለምን? አንደኛ፣ አንዳንዴ እንዲያዝኑ ወይም እንዲሣቀዩ የሚያደርጋቸውን ሊያዩ ስለሚችሉ፣ እነዚህም የኃጢአትና የክፉውን ድርጊት። በሰማይ ኀዘን፣ ዕንባ፣ ወይም የማያስደስት ነገር ባለመኖሩ (ራዕይ 21፡4)፣ በምድር ላይ ያሉትን ሁነቶች ማስተዋል የሚቻል አይመስልም። ሁለተኛ፣ በሰማይ ያሉ ሰዎች እግዚአብሔርን በማምለክና የሰማያዊ ክብርን ደስታ በመካፈል ስለሚጠመዱ፣ እዚህ በምድር ላይ ስለሚሆነው ነገር ያን ያህል ፍላጎት የሚኖራቸው አይመስልም። ከኃጢአት ነጻ የመሆናቸው ሐቅና የእግዚአብሔርን መገኘት በሰማይ መካፈላቸው ቀልባቸውን ለመማረክ በርግጥ ከበቂ በላይ ነው። እግዚአብሔር በሰማይ ላሉት ሰዎች የሚወዷቸውን ቁልቁል እንዲመለከቱ መፍቀድ ቢችልም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ይህ እንደሚሆን እንድናምን ምንም ምክንያት አይሰጠንም።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በሰማይ ያሉ ሰዎች ቁልቁል ይመለከታሉን፣ እኛንስ ገና በምድር ላይ ያለነውን ይመለከቱናልን?
© Copyright Got Questions Ministries