settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ለክርስቲያን፣ ክርስቲያን ያልሆነ የፍቅር ጓደኛ መያዝ ወይም ማግባት ልክ ነው?

መልስ፤


ለክርስቲያን፣ ክርስቲያን ያልሆነ የፍቅር ጓደኛ መያዝ ብልህነት አይደለም፣ እንዲሁም ማግባት አማራጭ አይደለም። ሁለተኛ ቆሮንቶስ 6፡14 (ኪጀት) ይነግረናል “ያለአቻችን እንዳንጠመድ” ከማያምን ጋር። ምስያው ሁለት የማይመጣጠኑ በሬዎች ተመሳሳይ ቀንበር መሸከማቸው ነው። ሸክሙን አንድ ላይ እየሳቡ በመሥራት ፈንታ፣ እርስ በርሳቸው በመቃረን ይሠራሉ። ይህ ምንባብ በቀጥታ ጋብቻን ለይቶ ባይጠቅስም፣ እሱ በርግጥ ለጋብቻ አንድምታ አለው። ምንባቡ በመቀጠል በክርስቶስና በቢልሆር (ሰይጣን) መካከል ኅብረት እንደሌለ ይገልጻል። ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ኅብረት በጋብቻ ውስጥ በክርስቲያንና ክርስቲያን ባልሆነ መካከል አይኖርም። ጳውሎስ ይቀጥላል፣ አማኞችን ማሳሰቡን፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ስፍራ መሆናቸውን፣ ልባቸውን ለደኅነት ማደሪያ የሆነ (2 ቆሮንቶስ 6፡15-17)። በዛ ምክንያት ከዓለም እንዲለዩ ነው— በዓለም ላይ፣ ነገር ግን ከዓለም ሳይሆን—እናም እጅግ ጠቃሚ የሆነ የትም ስፍራ አይገኝም፣ በሕይወት እጅግ ከቀረበ ግንኙነት በቀር— ከጋብቻ።

መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ይላል፣ “አትሳቱ፡ ‘ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል’ (1 ቆሮንቶስ 15፡33)። ከማያምን ጋር ማንኛውም ዓይነት የቅርብ ግንኙነት ማድረግ፣ ከክርስቶስ ጋር ያላችሁን ርምጃ ወደሚጎትት ነገር በፍጥነት ሊቀይር ይችላል። የተጠራነው ለጠፉት ወንጌልን ለመስበክ ነው እንጂ ከእነርሱ ጋር የቅርብ ጓደኛ እንድንሆን አይደለም። ከማያምኑት ጋር የተሻለ ወዳጅነት መፍጠር ምንም ነውር የለውም፣ ነገር ግን ያ በጊዜው የሚቀር ነው። ከማያምን ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምረህ ከሆነ፣ በቅንነት ቀዳሚ የሚሆንብህ፣ ፍቅር ማድረግ ነው ወይስ ነፍስን ለክርስቶስ ማሸነፍ? ከማያምን ጋር ከተጋባህ፣ ሁለታችሁ እንዴት አድርጋችሁ በጋብቻችሁ ውስጥ መንፈሳዊ ወዳጅነትን ልትገነቡ ትችላላችሁ? ጥራት ያለው ጋብቻ እንዴት ሊገነባና ሊዳብር ይችላል፣ በዩኒቨርስ ላይ ባለው ዋነኛ ነገር ሳትስማሙ— በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ?

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ለክርስቲያን፣ ክርስቲያን ያልሆነ የፍቅር ጓደኛ መያዝ ወይም ማግባት ልክ ነው?
© Copyright Got Questions Ministries