settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ምን ማለት ነው?

መልስ፤


“መንፈስ ቅዱስን መሳደብ” የሚለው ጽንሰ ሐሳብ የተጠቀሰው በማርቆስ 3፡22-30 እና ማቴዎስ 12፡22-32 ላይ ነው። ስድብ የሚለው ቃል ባጠቃላይ ሲገለጥ እንደ “ክብረ ነክ” ነው። ቃሉ ጥቅም ላይ የሚውለው እግዚአብሔርን የመራገም ኃጢአት ወይም ከእግዚአብሔር ጋር የተያያዙትን ነገሮች በገዛ ፍቃድ ክብራቸውን ዝቅ ማድረግ ነው። እንዲሁም ደግሞ በእግዚአብሔር ላይ ክፉ መናገር፣ ወይም ስለሱ መሆን ያለበትን መልካም ነገር መካድ ማለት ነው። ይህ የስድብ ጉዳይ፣ ሆኖም፣ የተለየ ዓይነት ነው፣ የሚጠራውም በማቴዎስ 12፡31 እንዳለው “መንፈስ ቅዱስን መሳደብ” በሚል ነው። በማቴዎስ 12፡31-32፣ ፈሪሳውያን፣ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተአምራት ማድረጉን ሊካድ በማይችል ምስክር እየተረዱ፣ በተቃራኒው ጌታ “ብኤልዜቡል’ በሚባለው አጋንንት መያዙን ይናገሩ ነበር (ማቴዎስ 12፡24)። አሁም እንግዲህ ልብ በል፣ በማርቆስ 3፡30 ኢየሱስ፣ እነሱ ለፈጸሙት በጣም ለይቶ ገልጾ ነበር፣ “መንፈስ ቅዱስን መሳደብ” ለሚለው።

ይህ ስድብ የሚደረገውም ማንም ኢየሱስ ክርስቶስን መንፈስ ቅዱስ የተሞላ ከማለት ፈንታ አጋንንት ያደረበት በማለት የርግማን ቃል ሲናገር ነው። በውጤቱም፣ ይህ በተለይ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተደረገ ስድብ ዛሬ ሊራባ አይችልም። ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር አይደለም— እሱ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል። ማንም ቢሆን ኢየሱስ ከርስቶስ ተአምራትን ፈጽሟል፣ ያንንም ያደረገው በሰይጣን ኃይል ነው፣ ከመንፈስ ቅዱስ ይልቅ ብሎ ሊመሰክር አይችልም። ዛሬ የተቀራረበ ምሳሌ ሊሆን የሚችለው በተዋጀ ሰው ላይ የተደረገውን የተለወጠ ሕይወት ተአምር ለሰይጣን ኃይል መስጠት ነው፣ ከሚያድረው ከመንፈስ ቅዱስ ሥራ አድርጎ ከመውሰድ ይልቅ።

ዛሬ መንፈስ ቅዱስን መሳደብ የሚሆነው፣ እሱም ከማይሰረየው ኃጢአት ጋር ተመሳሳይ የሚሆነው፣ ቀጣይነት ባለው መልኩ ያለማመን አቋም ነው። ባለ ማመን የሞተ ሰው ይቅርታ የለውም። የመንፈስ ቅዱስን ጉትጎታ፣ እሱም በኢየሱስ ክርስቶስ ለማመን በተከታታይ መናቅ፣ በእሱ ላይ የተደረገ የማይሰረይ ስድብ ነው። በዮሐንስ 3፡16 ላይ የሰፈረውን አስታውሱ፡ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” በተጨማሪም በዚሁ ምዕራፍ ይሄ ቁጥር አለ፡ “በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም” (ዮሐንስ 3፡36)። ማንም ቢሆን ምንም ዓይነት ይቅርታ የማያገኝበት ሁኔታ፣ “በእሱ የሚያምን ሁሉ፣” ከሚባሉት መሐል ሳይሆን ቀርቶ፣ “በልጁ ያማምን” ከሚሉት ሲሆን ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries