settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ምን ይላል?

መልስ፤


መላእክት ግላዊ መንፈሳዊ ሕላዌ ናቸው፣ የሚያስቡ፣ ስሜት ያላቸው፣ እና ፍቃድ ያላቸው። ይህም ለሁለቱም የሚሠራ ነው፣ ለመልካሞቹና ለክፉዎቹ መላእክት (አጋንንት)። መላእክት ማሰብ ይችላሉ (ማቴዎስ 8:29፤ 2 ቆሮንቶስ 11:3፤ 1ጴጥሮስ 1:12)፣ ስሜታቸውን ይገልጻሉ (ሉቃስ 2:13፤ ያዕቆብ 2:19፤ ራዕይ 12:17)፣ ፍቃዳቸውን ይፈጽማሉ (ሉቃስ 8:28-31፤ 2 ጢሞቴዎስ 2:26፤ ይሁዳ 6)። መላእክት መንፈሳዊ ሕላዌ ናቸው (ዕብራውያን 1:14) በሥጋዊ አካል ያልሆኑ። ምንም እንኳ ሥጋዊ አካል ባይኖራቸውም፣ አካል ናቸው።

የተፈጠሩ ሕላዌዎች ከመሆናቸው የተነሣ፣ እውቀታቸው ውስን ነው። ማለትም፣ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ሁሉ አያውቁም (ማቴዎስ 24፡36)። ከሰው የላቀ እውቀት ያላቸው ይመስላሉ፣ ምናልባትም ከሦስት ነገሮች የተነሣ። አንደኛ፣ መላእክት የተፈጠሩት ከፍጥረታት ተርታ ከሰው በላጭ ሆነው ነው። ስለዚህ፣ ከፍጥረታቸው ከፍ ያለ እውቀትን ወርሰዋል። ሁለተኛ፣ መላእክት መጽሐፍ ቅዱስንና ዓለምን አጥንተዋል፣ እጅግ ጠለቅ ባለ መልኩ፣ ከሰዎች ይልቅ፣ እናም ከእሱ እውቀትን አካብተዋል (ያዕቆብ 2፡19፤ ራዕይ 12፡12)። ሦስተኛ፣ መላእክት እውቀትን አካብተዋል፣ ከተራዘመ የሰው ልጆችን ተግባር ከማስተዋላቸው አኳያ። ከሰው በተለየ መልኩ መላእክት ያለፈውን ማጥናት አይጠበቅባቸውም፣ ስላለፉበት። ስለዚህ፣ ሌሎች እንዴት እንደሚተገብሩና ሁኔታዎችን እንዴት እንደሚረዱ ያውቃሉ፣ በተመሳሳይ ሁኔታዎች እንዴት ያለውን ምላሽ እንደምንሰጥ ስለሚያውቁ ከፍ ባለ ደረጃ መጪውን በትክክል ሊተነብዩ ይችላሉ።

ፍቃድ ቢኖራቸውም፣ መላእክት እንደ ሌሎቹ ፍጡራን፣ ለእግዚአብሔር ፍቃድ የተገዙ ናቸው። መልካም መላእክት አማኞችን ለመርዳት በእግዚአብሔር ይላካሉ (ዕብራውያን 1፡14)። መጽሐፍ ቅዱስ የገለጣቸው አንዳንድ የመላእክት ተግባራት እነሆ፡ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ (መዝሙር 148:1-2፤ ኢሳይያስ 6:3)። እግዚአብሔርን ያመልካሉ (ዕብራውያን 1:6፤ ራዕይ 5:8-13)። እግዚአብሔር ባደረገው ይደሰታሉ (ኢዮብ 38:6-7)። እግዚአብሔርን ያገለግላሉ (መዝሙር 103:20፤ ራዕይ 22:9)። በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ (ኢዮብ 1:6፤ 2:1)። የእግዚአብሔር ፍርድ መሣርያዎች ናቸው (ራዕይ 7:1፤ 8:2)። የጸሎትን መልስ ይዘው ይመጣሉ (ሐዋርያት ሥራ 12:5-10)። ሰዎችን በክርስቶስ ለማሸነፍ ያግዛሉ (ሐዋርያት ሥራ 8:26፤ 10:3)። የክርስቲያንን ትዕዛዝ፣ ሥራ፣ እና ሥቅይት ያስተውላሉ (1 ቆሮንቶስ 4:9፤ 11:10፤ ኤፌሶን 3:10፤ 1 ጴጥሮስ 1:12)። በአደጋ ጊዜ ያበረታታሉ (ሐዋርያት ሥራ 27:23-24)። በሞት ሰዓት ለጻድቁ ክብካቤ ያደርጋሉ (ሉቃስ 16:22)።

መላእክት ባጠቃላይ ከሰዎች የተለዩ ሕላዌ ደረጃ ናቸው። የሰው ልጆች ከሞቱ በኋላ መላእክት አይሆኑም። መላእክት ፈጽሞ የሰው ልጅ አይሆኑም፣ አልነበሩምም። እግዚአብሔር መላእክትን ፈጠረ፣ ሰዎችን እንደፈጠረ ሁሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የትም ቦታ፣ መላእክት በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጠሩ አይልም፣ ሰዎች እንደሆኑት (ዘፍጥረት 1፡26)። መላእክት መንፈሳዊ ሕላዌ ናቸው፣ ያም በተወሰነ ደረጃ ሥጋዊ ቅርጽ መያዝ የሚችሉ። ሰዎች ከመጀመሪያውም ሥጋዊ አካል ናቸው፣ ግን በመንፈሳዊ ገጽታ። ከቅዱሳን መላእክት የምንማረው ታላቁ ነገር ለእግዚአብሔር ትእዛዝ ፍጥነታቸው፣ ጥያቄ-የለሽ ታዛዥነታቸውን ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries