settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥላሴ ምን ያስተምራል?

መልስ፤


ክርስቲያን ስለ ሥላሴ ባለው ሀሳብ በጣም አስቸጋሪው ነገር እሱን በበቂ ሁኔታ ማብራራት የሚቻልበት መንገድ የለም፡፡ የሥላሴን ሀሳብ እንኳን ማብራራት ማንኛውም ሰው በሙላት መረዳት አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ያለ ወሰን ከእኛ ይበልጣል፤ስለዚህ በሙላት እሱን መረዳት መቻልን ልንጠብቅ አይገባም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አብም፤ኢየሱስም፤ እና መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር እንደሆኑ ያስተምራል፡፡ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ብቻ እንዳለ ያስተምራል፡፡ ምንም እንኳን በሥላሴ የተለያዩ ስብዕናዎች እርስ በራሱ መሐከል ያለውን የግንኙነት የተወሰኑ እውነታዎች መረዳት ብንችልም በመጨረሻው ከሰው አዕምሮ የላቀ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህ ሥላሴ እውነት አይደለም ወይም ያ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርቶች አልተመሰረተም ማለት አይደለም፡፡

ሥላሴ ሦስት ስብዕናዎች ያሉት አንድ አምላክ ነው፡፡ ይኸ በማንኛውም መንገድ ሦስት አማልክትን ማሳሰብ እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ ይህንን ጉዳይ በምታጠናበት ጊዜ “ሥላሴ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ውስጥ እንደማይገኝ አስተውል፡፡ ይኸ በመለኮት አንድ በስብዕና ሦስት የሆነውን፤ እግዚአብሔር የሆነው ዘላለማዊ ስብዕናውን ለመግለጽ ጥረት ለማድረግ ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ነው፡፡ በእውነት ጠቃሚ ከሆነው ነገር “ሥላሴ” በሚለው የተወከለው ሀሳብ በመጽሐፍ ውስጥ አለ፡፡ የሚከተለው የእግዚአብሔር ቃል ስለ ሥላሴ የሚለው ነገር ነው፤

1ኛ) አንድ እግዚአብሔር አለ (ኦሪት ዘዳግም 6፤4፤1ኛ ቆሮንቶስ 8፤4፤ወደ ገላቲያ ሰዎች 3፤20፤1ኛ ጢሞቴዎስ 2፤5)

2ኛ) ሥላሴ ሦስት ስብዕናዎች ይዟል፤(ኦሪት ዘፍጥረት 1፤1,26;3፤22; 11፤7፤ትንቢተ ኢሳይያስ 6፤8; 48፤16; 61፤1፤የማቴዎስ ወንጌል 3፤16-17; 28፤19፤2ኛ ቆሮንቶስ 13፤14):: በኦሪት ዘፍጥረት 1፤1 የዕብራይስጥ ብዙ ቃል የሆነው ስም ሄሎይም ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት 1፤26፤3፤22፤11፤7 እና በትንቢተ ኢሳይያስ 6፤8 “እኛ” ብዙ የሆነው ተውላጤ ስም ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ሄሎይም የሚለው ቃል እና “እኛ” የሚለው ተውላጤ ስም የብዙ ቁጥሮች፤ በዕብራይስጥ ቋንቋ ያለ ጥርጥር ከሁለት ወደሚበልጡ እያመለከተ ነው፡፡ ምንም እንኳን ይኸ ለሥላሴ ግልጽ የሆነ መከራከሪያ ባይሆንም በእግዚአብሔር የብዙ ቁጥሮችን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ለእግዚአብሔር የሆነው ሄሎይም የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ያለ ጥርጥር ለሥላሴም ይሆናል፡፡

በትንቢተ ኢሳይያስ 48፤16 እና 61፤1; ልጁ አብን እና መንፈስ ቅዱስን እያመለከተ እየተናገረ ነው፡፡ ልጁ እየተናገረ እንዳለ ለማየት ትንቢተ ኢሳይያስ 61፤1ን ከሉቃስ ወንጌል 4፤14-19 ካላው ጋር አነጻጽር፡፡ የማቴዎስ ወንጌል 3፤16-17 የኢየሱስን የጥምቀት ክስተቶችን ይገልጻል፡፡ በዚህ ምንባብ ውስጥ እንደሚታየው እግዚአብሔር የሆነው መንፈስ ቅዱስ ልጅ በሆነው በእግዚአብሔር ላይ ሲወርድ ደግሞም አብ የሆነው እግዚአብሔር በልጁ ደስታውን እንዳወጀ ይገልጻል፡፡ የማቴዎስ ወንጌል 28፤19 እና 2ኛ ቆሮንቶስ 13፤14 በሥላሴ የሦስት የተለያዩ ስብዕናዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

3ኛ) በተለያዩ ምንባቦች ውስጥ የሥላሴ አካላት አንዳቸው ከአንዳቸው ተለይተዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን “እግዚአብሔር” ከእግዚአብሔር ተለይቷል (ኦሪት ዘፍጥረት 19፤24፤ ትንቢተ ሆሴዕ 1፤4)፡፡ እግዚአብሔር ልጅ አለው (መዝሙረ ዳዊት 2፤7,12፤መጽሐፈ ምሳሌ 30፤2-4)፡፡ መንፈስ ከ “እግዚአብሔር” (ኦሪት ዘኁልቁ 27፤18) እና መንፈስ ከ “እግዚአብሔር” (መዝሙረ ዳዊት 51፤10-12) ተለይቷል፡፡ እግዚአብሔር ልጅ ከእግዚአብሔር አብ ተለይቷል (መዝሙረ ዳዊት 45፤6-7፤ወደ ዕብራውያን ሰዎች 1፤8-9)፡፡ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ረዳት የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ስለመላክ ለአብ ይናገራል (የዮሐንስ ወንጌል 14፤16-17)፡፡ ይኸ ኢየሱስ እንደ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ ራሱን አለመመልከቱን ያሳያል፡፡ በተጨማሪ በወንጌላት ውስጥ ኢየሱስ ለአብ የተናገረበትን ሌሎች ጊዜያቶችን ሁሉ ተመልከት፡፡ ለራሱ እየተናገረ ነበርን? አይደለም፡፡ በሥላሴ ውስጥ የተናገረው ለሌላ ስብዕና እሱም ለአብ ነበር፡፡

4ኛ) እያንዳንዱ የሥላሴ አካል እግዚአብሔር ነው፡፡ አብ እግዚአብሔር ነው (የዮሐንስ ወንጌል 6፤27፤ወደ ሮሜ ሰዎች 1፤7፤1ኛ ጴጥሮስ 1፤2)፡፡ ልጁም እግዚአብሔር ነው (የዮሐንስ ወንጌል 1፤1;14፤ወደ ሮሜ ሰዎች 9፤5፤ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፤9፤ወደ ዕብራውያን ሰዎች 1፤8፤1ኛ ዮሐንስ 5፤20)፡፡ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው (የሐዋሪያት ሥራ 5፤3-4፤1ኛ ቆሮንቶስ 3፤16)፡፡

5ኛ) በሥላሴ ውስጥ የሥልጣን ተዋረድ አለ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለአብ እና ለልጅ እንዲሁም ልጅ ለአብ እንደሚታዘዙ መጽሐፍ ያሳያል፡፡ ይኸ ውስጣዊ ግንኙነት ነው እናም የየትኛውንም የሥላሴ አምላክነት አይክድም፡፡ ወሰን የሌለውን አምላክን በተመለከተ ይኸ በቀላሉ ውስን የሆነው አዕምሮአችን ሊገነዘበው የማይችለው ጉዳይ ነው፡፡ ልጅን በተመለከተ የሉቃስ ወንጌል 22፤42፤የዮሐንስ ወንጌል 5፤36፤የዮሐንስ ወንጌል 20፤21 እና 1ኛ ዮሐንስ 4፤14ን ተመልከት፡፡ መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ የዮሐንስ ወንጌል 14፤16;14፤26;15፤26;16፤7 እና በተለይም የዮሐንስ ወንጌል 16፤13-14ን ተመልከት፡፡

6ኛ) እያንዳንዱ የሥላሴ አካላት የተለያዩ ሥራዎች አሏቸው፡፡ አብ የነገር ሁሉ ምንጭ ወይም የዓለማት (1ኛ ቆሮንቶስ 8፤6፤የዮሐንስ ራዕይ 4፤11)፤የመለኮታዊ ራዕይ (የዮሐንስ ራዕይ 1፤1)፤የድነት (የዮሐንስ ወንጌል 3፤16-17)፤ እና የኢየሱስ ሰዋዊ ሥራዎች (የዮሐንስ ወንጌል 5፤17;14፤10) ምክንያት ነው፡፡ አብ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይጀምራል፡፡

ልጁ አብ የሚከተሉትን ሥራዎች በእርሱ በኩል የሚሠራበት ወኪል ነው፤ የዓለማትን ፍጥረት እና ጥበቃ (1ኛ ቆሮንቶስ 8፤6፤የዮሐንስ ወንጌል 1፤3፤ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፤16-17)፤ መለኮታዊ ራዕይ (የዮሐንስ ወንጌል 1፤1;16፤12-15፤የማቴዎስ ወንጌል 11፤27፤የዮሐንስ ራዕይ 1፤1) እና ድነትን (2ኛ ቆሮንቶስ 5፤19፤የማቴዎስ ወንጌል 1፤21፤የዮሐንስ ወንጌል 4፤42):: አብ እነዚህን ሁሉ ነገሮች እንደ ወኪሉ በሚሠራው በልጁ በኩል ያደርጋል፡፡

መንፈስ ቅዱስ አብ በእርሱ የሚከተሉትን ሥራዎች የሚሠራበት ነው፤የዓለማትን ፍጥረት እና ጥበቃ (ኦሪት ዘፍጥረት1፤2፤መጽሐፈ ኢዮብ 26፤13፤መዝሙረ ዳዊት 104፤30)፤ መለኮታዊ ራዕይ (የዮሐንስ ወንጌል 16፤12-15፤ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፤5፤2ኛ ጴጥሮስ 1፤21)፤የድነት (የዮሐንስ ወንጌል 3፤6፤ወደ ቲቶ 3፤5፤1ኛ ጴጥሮስ 1፤2)፤እና የኢየሱስን ሥራዎች (ትንቢተ ኢሳይያስ 61፤1፤የሐዋሪያት ሥራ 10፤38)፡፡ ስለዚህ አብ እነዚህን ሁሉ ነገሮች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይሠራል፡፡

የሥላሴን ገለጻ ለማዳበር ብዙ ጥረቶች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በጣም ከታወቁቱ ገለጻዎች ሙሉ በሙሉ አንዳቸውም ትክክለኞች አይደሉም፡፡ ልክ እንደ ቆዳ፤ሥጋ እና ፖሙ ሳይሆን የፖም ፍሬዎች ያው የራሱ ድርሻ እንደሆኑ የእንቁላል ቅርፊቱ የሆነው፤ ነጩ እና አስኳሉ፤ የእንቁላል ክፍሎች ናቸው እንጂ በራሳቸው ውስጥ ያለው እንቁላል አይደለም፡፡ አብ ፤ወልድ፤ እና መንፈስ ቅዱስ የአምላክ ተምሳሌቶች አይደሉም፤እያንዳንዱ አምላክ ነው፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ምናልባት ይህ ገለጻ የሥላሴን ምስል ቢሰጠንም፤ምስሉ ሙሉ በሙሉ ትክክል አይደለም፡፡ ወሰን የሌለው አምላክ ውስን በሆነ ገለጻ በሙላት ሊገለጽ አይችልም፡፡

በጠቅላላው የቤተክርስቲያን ታሪክ ሁሉ የሥላሴ አስተምህሮ አከራካሪ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም እንኳን የሥላሴ አቢይ ጉዳዮች በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በግልጽ ቢቀርብም አንድንድ ተያያዥ ጉዳዮች ግን እንደተጠበቀው ግልጽ አይደሉም፡፡ አብም እግዚአብሔር ነው፤ልጅም እግዚአብሔር ነው፤ እና መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር ነው፤ነገር ግን አንድ አምላክ ብቻ አለ፡፡ ያ የሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈ በተወሰነ መልኩ ጉዳዮቹ አከራካሪ እና አላስፈላጊ ናቸው፡፡ በእኛ በተወሰነ የሰው አዕምሮ በሙላት ሥላሴን ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅ በእግዚአብሔር ትልቅነቱ እና በእርሱ በልተወሰነ ከፍ ባለ ተፈጥሮው ላይ ትኩረት አድርገን ብንገለገል የተሻለ ይሆናል፡፡ “የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው?” (ወደ ሮሜ ሰዎች 11፤33-34)

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥላሴ ምን ያስተምራል?
© Copyright Got Questions Ministries