settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ በሞቱና በትንሣኤው መሐል ገሃነም ሄዶ ነበርን?

መልስ፤


ይሄንን ጥያቄ በተመለከተ በርከት ያለ ውዥንብር አለ። ጽንሰ-ሐሳቡ የሚመጣው በቅድሚያ ከሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ ነው፣ እንዲህ ከሚለው፣ “ወደ ገሃነም የወረደ።” እንዲሁም ጥቂት መጻሕፍት የተተረጎሙበትን በመንተራስ፣ የኢየሱስን ወደ “ገሃነም” መውረድ ይገልጻሉ። ይህን ጉዳይ በማጥናት ረገድ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሙታን መገኛ የሚለውን በቅድሚያ መረዳቱ ጠቃሚ ነው።

በዕብራውያን መጻሕፍት፣ የሙታንን ማኖርያ ስፍራ ለመግለጽ የተጠቀሙበት ቃል ሲኦል ነው። ይህም ባጭሩ “የሙታን ስፍራ” ወይም (የተለዩ ነፍሳት/መናፍስት ስፍራ) ማለት ነው። የአዲስ ኪዳን ግሪክ ቃል ለገሃነም የተቀመጠው “ሃዳስ፣” ሲሆን ይህም የሚያመለክተው “የሙታን ስፍራ” ነው። ሌሎች ጽሑፎች በአዲስ ኪዳን የሚያመለክቱት ሲኦል/ሃዳስ ሙታን እስከ የመጨረሻው የትንሣኤና የፍርድ ቀን ድረስ የሚጠበቁበት ጊዜያዊ ስፍራ ነው። ራዕይ 20፡11-15 በሁለቱ መሐል ግልጽ ልዩነቶችን ያስቀምጣል። ገሃነም (የእሳት ባሕር) ለጠፉት የሚሆን ቋሚና የመጨረሻ የፍርድ ስፍራ ነው። ሲኦል ጊዜያዊ ስፍራ ነው። ስለዚህ፣ አይሆንም፣ ኢየሱስ ወደ ገሃነም አልሄደም፣ ምክንያቱም ገሃነም የወደፊት ስፍራ ነው፣ እሱም ከታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ በኋላ ተግባራዊ የሚደረግ (ራዕይ 20፡11-15)።

ሲኦል/ሃዳስ ስፍራ ነው በሁለት ምድቦች (ማቴዎስ 11፡23፣ 16፡18፤ ሉቃስ10፡15፣ 16፡23፤ ሐዋርያት ሥራ 2፡27-31)፣ የዳኑትና የጠፉት ማቆያ። የዳኑት ማቆያ “ገነት” ሲባል፣ እሱም “የአብርሃም እቅፍ” ነው። የዳኑትና የጠፉት መኖርያ የተለየው “በታላቅ ገደል” ነው (ሉቃስ 16፡26)። ኢየሱስ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ፣ የገነትን ነዋሪዎች (አማኞች) ከእሱ ጋር ወስዷቸዋል (ኤፌሶን 4፡8-10)። የጠፉት የሲኦል/ሃዳስ አኳያ ሳይለወጥ ይቆያል። ሁሉም የማያምኑ ሙታን እዛው ሆነው በቀጣይ የሚሆነውን የመጨረሻ ፍርዳቸውን ይጠብቃሉ። ኢየሱስ ወደ ሲኦል/ሃዳስ ሄዶ ነበርን? አዎን፣ እንደ ኤፌሶን 4፡8-10 እና 1ኛ ጴጥሮስ 3፡18-20 መሠረት።

አንዳንድ የሚነሡት ይሄንን ከመሳሰሉ አንቀጾች ነው፣ ለአብነትም መዝሙር 16፡10-11 በኪንግ ጀምስ ቅጅ እንደተተረጎመው፣ “ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፣ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም… የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ።” “ገሃነም” የዚህ ቁጥር ትክክለኛ ትርጉም አይደለም። ትክክለኛው ንባብ የሚሆነው “መቃብር” ወይም “ሲኦል” ነው። ኢየሱስ በጎኑ ለነበረው ወንበዴ፣ “ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” ብሎታል (ሉቃስ 23፡43)። የኢየሱስ ሥጋ በመቃብር ነበር፤ ነፍሱ/መንፈሱ ወደ “ገነት” የሲኦል/ሃዳስ አኳያ ሄዷል። እሱም ጻድቅ ሙታንን ከገነት አንሥቶ ከእሱ ጋር ወደ መንግሥተ ሰማያት ወስዷቸዋል። አለመታደል ሆኖ፣ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች፣ ተርጓሚዎች ቋሚ፣ ወይም ትክክለኛ በሆነ መልክ የዕብራይስጥና የግሪክ ቃላት “ሲኦል” “ሃዳስ” እና “ገሃነም” ን አልተረጎሟቸውም።

አንዳንዶች ኢየሱስ ወደ “ገሃነም” ሄዷል የሚል አመለካከት አላቸው፣ ወይም የሲኦል/ሃዳስ የማሣቀያ ስፍራ ለእኛ ኃጢአት ሲል ተጨማሪ ቅጣት ለመቀበል። ይህ ሐሳብ ፈጽሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። የኢየሱስ የመስቀል ሞት እና በእኛ ምትክ መከራ መቀበሉ ለደኅንነታችን በበቂነት የተሰጠ ነው። የፈሰሰ ደሙ ነው ከኃጢአታችን መንጻትን ያስገኘልን (1ኛ ዮሐንስ 1፡7-9)። በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እያለ፣ የሁሉም የሰው ልጆችን የኃጢአት ሸክም በራሱ ላይ ወሰደ። ስለ እኛ ኃጢአት ሆነ፡ “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21)። ይህ የኃጢአት ዋጋ የክርስቶስን በበጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ያደረገውን ትግል፣ ይህም በመስቀል ላይ በላዩ የፈሰሰውን የኃጢአት ጽዋ እንድንገነዘበው ይረዳናል።

ኢየሱስ በመስቀል ላይ፣ “አባት ሆይ፣ ለምን ተውከኝ?” ብሎ በጮኸ ጊዜ (ማቴዎስ 27፡46)፣ ይህም በላዩ ከወረደው ኃጢአት ምክንያት ከአብ ጋር በመለያየቱ ነው። ነፍሱን በሰጠ ጊዜ፣ “አባት፣ ነፍሴን በእጅህ አኖራለሁ” ብሏል፣ (ሉቃስ 23፡46)። በእኛ ምትክ የተቀበለው መከራ ተፈጸመ። ነፍሱ/መንፈሱ የገነት ክፍል ወደ ሆነው ሃዳስ ሄደ። ኢየሱስ ወደ ገሃነም አልሄደም። የኢየሱስ መከራ በሞተበት ጊዜ አብቅቷል። የኃጢአት ዋጋ ተከፍሏል። እሱ ከዚያ ወዲያ የጠበቀው የሥጋውን መነሣትና በዕርገት ወደ ክብሩ መመለሱን ነው። ኢየሱስ ወደ ገሃነም ሄዷልን? አይደለም። ኢየሱስ ወደ ሲኦል/ሃዳስ ሄዷልን? አዎን።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ በሞቱና በትንሣኤው መሐል ገሃነም ሄዶ ነበርን?
© Copyright Got Questions Ministries