settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፤


ኢየሱስ እንደ ሰው አግባብ በሆነ አባትና ልጅነት የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም። እግዚአብሔር አላገባም ልጅም የለውም። እግዚአብሔር ከማርያም ጋር ተጎዳጅቶ፣ ከእሷም ጋር ሆኖ ልጅ አልወለደም። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ሲባል በሰው መልክ የተገለጠ አምላክ ማለት ነው (ዮሐንስ 1፡1፣14)። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፣ እሱም በመንፈስ ቅዱስ በማርያም የተፀነሰ። ሉቃስ 1፡35 እንዲህ ይላል፤ “መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።”

በአይሁድ መሪዎች ፊት በነበረበት ክስ ላይ፣ ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስን እንዲህ ጠይቆታል፤ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ አለው።” (ማቴዎስ 26፡63)። “ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው።” (ማቴዎስ 26፡64)። የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን እንደተሳደበ ቆጥረው ከሰሱት (ማቴዎስ 26፡65-66)። ቆይቶም፣ በጴንጤናዊው ጲላጦስ ፊት፣ “አይሁድም መልሰው፣ እኛ ሕግ አለን፥ እንደ ሕጋችንም ሊሞት ይገባዋል፥ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎአልና አሉት” (ዮሐንስ 19፡7)። እሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መግለጡ ለምን እንደ ስድብ ተቆጥሮበት የሞት ፍርድ አስፈረደበት? የአይሁድ መሪዎች፣ ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ያለው ምን ማለት እንደሆነ በትክክል ገብቷቸዋል። የእግዚአብሔር ልጅ መሆን የእግዚአብሔር ባሕርይ ዓይነት መሆን ነው። የእግዚአብሔር ልጅ “የእግዚአብሔር ነው።” እንደ እግዚአብሔር ያለ ባሕርይ አለኝ ማለት፣ እግዚአብሔርን በመሆኑ፣ ለአይሁድ መሪዎች ስድብ ነው፤ ስለሆነም፣ የኢየሱስን ሞት ጠየቁ፣ ከሌዋውያን 24፡15 ጋር አያይዘው። ዕብራውያን 1፡3 ይሄንን በግልጽ ያሳያል፣ “እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።”

ሌለኛው ምሳሌ የሚገኘው በዮሐንስ 17፡12 ሲሆን፣ እሱም ይሁዳ “የጥፋት ልጅ “ ተብሎ የተገለጠው ነው። ዮሐንስ 6፡71 የሚነግረን ይሁዳ የስምዖን ልጅ መሆኑን ነው። የሐንስ 17፡12 ይሁዳን “የጥፋት ልጅ” ሲል ለምን ገለጠው? ጥፋት የሚለው ቃል “ውድመት፣ ብልሽት፣ ጥፋት” ማለት ነው። ይሁዳ በጥሬው የ“ውድመት፣ ብልሽት፣ እና ጥፋት” ልጅ አይደለም፤ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች የይሁዳ ሕይወት መገለጫዎች ናቸው። ይሁዳ የጥፋት መገለጫ ነው። በዚሁ ተመሳሳይ መንገድ፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ነው። ኢየሱስ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው (ዮሐንስ 1፡1፣ 14)።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries