settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የክርስቲያን ጥምቀት ጥቅም ምንድነው?

መልስ፤


በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የክርስቲያን ጥምቀት በአማኞች በውስጥ ህይወት የሆነውን ነገር በውጫዊው መመስከር ነው፡፡ የክርስቲያን ጥምቀት የክርስቲያኖችን ከክርስቶስ ሞት፤መቀበር እና መነሳት ጋር መተባበርን ይገልጻል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።” እያለ ያውጃል (ወደ ሮሜ ሰዎች 6፤3-4)፡፡ በክርስቲያን ጥምቀት በውሃ ውስጥ የመጥለቁ ድርጊት ከክርስቶስ ጋር መሞት እና መቀበርን ይወክላል፡፡ ከውሃ የመውጣቱ ድርጊት የክርስቶስን ትንሳኤ ይወክላል፡፡

በክርስቲያን ጥምቀት አንድ ሰው ከመጠመቁ በፊት ሁለት መሟላት ያለባቸው ነገሮች አሉ፤ 1ኛ) የሚጠመቀው ሰው እንደ አዳኙ በኢየሱስ ክርስቶስ መታመን አለበት፤ 2ኛ) ያ ሰው ጥምቀት ምን እንደሆነ ሊገነዘብ ይገባል፤ ግለሰቡ ጌታ ኢየሱስን እንደ አዳኙ ካወቀ፤ የክርስቲያን ጥምቀት በክርስቶስ ላይ ያለውን እምነት በአደባባይ ለማወጅ የመታዘዝ እርምጃ እንደሆነ ከተገነዘበ፤ እና ለመጠመቅ ፍላጎቱ ካለው አንድን አማኝ ከመጠመቅ የሚከለክል ምንም ምክንያት የለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የክርስቲያን ጥምቀት ጠቃሚ ነው ምክንያቱም የመታዘዝ እርምጃ ነው፤ በክርስቶስ ያለውን እምነት በአደባባይ የማወጅ እና ለእርሱ መሰጠት ከክርስቶስ ሞት፤መቀበር፤ እና ትንሳኤ ጋር መተባበር ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የክርስቲያን ጥምቀት ጥቅም ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries