settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ግድፈቶችን፣ ተቃርኖዎችን፣ ወይም ልዩነቶችን ይዟልን?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስን ዝም ብለን ብናነበው፣ ስሕተቶች ለመፈለግ ቀድሞ በታሰበበት የተዛባ እይታ ሳይሆን፣ ኅብር ያለው፣ የጸና፣ እና በአንጻራዊነት በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው መጽሐፍ ነው። ርግጥ ነው፣ አስቸጋሪ አንቀጾች ይኖሩታል። ርግጥ ነው፣ እርስ በርሳቸው በመቃረን የሚከሰቱ ቁጥሮች ይኖሩታል። የግድ ማስታወስ የሚኖርብን፣ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በግምት 40 በሚሆኑ የተለያዩ ደራሲዎች፣ በግምት በ1500 ዓመት ውስጥ ነው። እያንዳንዱ ደራሲ በተለየ ስልት ነው የጻፈው፣ ከተለየ አመለካከት፣ ወደ ተለያየ ታዳሚ፣ ለተለያየ ዓላማ። የተወሰኑ አነስተኛ ልዩነቶች እንደሚኖሩ እንጠብቃለን። ሆኖም፣ ልዩነት የቃርኖ አይደለም። እንደ ግድፈት ተደርጎ ብቻ ነው የሚወሰደው፣ ምንም እንኳ ፈጽሞ የሚታሰብበት መንገድ ባይኖርም፣ ቁጥሮች ወይም ምንባቦች ሊመሳከሩ የሚችሉበት። ምንም እንኳ መልስ አሁኑኑ ባይገኝም፣ ያ ማለት መልስ አይኖርም ማለት አይደለም። ብዙዎች ግድፈት ሊሆኑ የሚችሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ አግኝተዋል፣ ከታሪክና ከመልክዓ ምድር ጋር በተያያዘ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ልክ ነው አንድ ተጨማሪ የጥንታዊ ቅርስ ማስረጃ ከተገኘ ለማለት።

እኛ ዘወትር ጥያቄዎችን እንቀበላለን፣ በየመስመሮቹ ላይ፣ “እነዚህ ቁጥሮች እንዴት እንደማይቃረኑ አብራራ!” ወይም “ተመልከት፣ እዚህጋ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ!” የሚሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ሰዎች የሚያመጧቸውን አንዳንዱ ነገሮች ለመመለስ አዳጋች ናቸው። ሆኖም፣ እሱ የእኛ ክርክር ነው፣ የሚያረካና በእውቀት ተአማኒ የሆነ መልስ ለእያንዳንዱ ታሳቢ የመጽሐፍ ቅዱስ ተቃርኖዎች እና ግድፈቶች ይኖራል። መጻሕፍትና ድረ-ገጾች ይገኛሉ፣ “የመጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም ግድፈቶች” የሚል ዝርዝር የያዙ። አብዛኞቹ ሰዎች በቀላሉ የማጥቂያ መረጃቸውን የሚያገኙት ከእነዚህ ስፍራዎች ነው፤ የራሳቸውን ታሳቢ ግድፈት አይፈልጉም። ደግሞም መጻሕፍትና ድረ-ገጾች ይገኛሉ፣ እነዚህን ታሳቢ ግድፈቶች የሚከራከሩ። አሳዛኙ ነገር፣ አብዛኞቹ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያጠቁ ሰዎች፣ ለመልሶቹ ከልባቸው ፍላጎት የሌላቸው መሆናቸው ነው። አብዛኞቹ “መጽሐፍ ቅዱስ አጥቂዎች” እነዚህን መልሶች ያውቋቸዋል፣ ነገር ግን ተመሳሳይ የሆኑትን ያረጁ ጠባብ ጥቃቶች ደግመው ደጋግመው መጠቀማቸውን ይቀጥላሉ።

ስለዚህ፣ አንዱ በዚህ አጠራጣሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ግድፈት ሲያቀርብልን ምን ማድረግ ይኖርብናል? 1) ቅዱስ ቃሉን በጸሎት ማንበብና ቀላል መፍትሔ እንዳለ መመልከት። 2) መጠነኛ ጥናት ማካሄድ፣ መልካም የመጽሐፍ ቅዱስ ሐተታዎችን በመጠቀም፣ “የመጽሐፍ ቅዱስ መከላከያ” መጻሕፍት፣ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ የምርምር ድረ-ገጾች። 3) ፓስተሮችን/የቤተ-ክርስቲያን መሪዎችን መጠየቅ፣ መፍትሔ ያገኙለት እንደሁ ለመመልከት። 4) ከደረጃ 1)፣ 2)፣ እና 3) በኋላ ግልጽ የሆነ ምላሽ ካልተገኘ፣ እግዚአብሔርን እናምናለን፣ ቃሉ እውነት መሆኑን፣ እናም መፍትሔ ይኖራል፣ አሁን በቀላሉ ልንረዳው ያልቻልነው (2 ጢሞቴዎስ 2:15፣ 3:16-17)።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ግድፈቶችን፣ ተቃርኖዎችን፣ ወይም ልዩነቶችን ይዟልን?
© Copyright Got Questions Ministries